ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ግምባር ሲገዛ የኖረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የተከፈተውን የተማሪዎች ሰላማዊ ተቃውሞ “የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ” በማለት በኢትዮጵያ ስም በተሰየመው የቴሌቪዥን ፕሮግራም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በ1997 ምርጫ ሽንፈት ለመቀበል ጥቂት የቀረው ህወሃት ሞት በወሰዳቸው መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ አማካኝነት የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ሥር ይሆናል በማለት በቀጥታ የህወሃት ታዛዥ በማድረግ በ197 ንጹኃን ዜጎች ላይ በአልሞ ተኳሾች ደረትና ግምባራቸውን በማለት እንደገደለ አሁንም “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት በተማሪና ነዋሪዎች ላይ ለመውሰድ ያቀደውን ፍጹም ኢሰብዓዊ እርምጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከህወሃት የጭከና ታሪክ አንጻር የመግለጫው ትርጉም ለመቀጣጫ እንዲሆን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የመግደያው ጊዜ አሁን ነው በሚል እንደሚወሰድ ብዙዎች የሚስማሙበት ነው፡፡
ለዚህ ሲባል ይመስላል እርምጃውን በሚወስድበት ጊዜ ሊወጡ የሚችሉ የፎቶና የቪዲዮ ምስሎችን ለማገድ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እንደሚነገረው በአገሪቷ ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቀንስ ሲቻልም እንዲቆም እንደሚደረግ ተወስቷል፡፡
ነጻ አወጣዋለሁ ለሚለው የትግራይ ሕዝብ እንኳን ፍጹም ጨካኝነት በተሞላበት ሁኔታ ሲያሸብር የኖረው ህወሃት ሰሞኑን በተመሳሳይ መልኩ በአንዳንድ ቦታዎች ሆን ተብሎ የዘር ግጭቶች እንዲነሱና የርስበርስ ዕልቂት እንዲከሰት እና በዚያ አጋጣሚ የሕዝቡን የተቃውሞው እንቅስቃሴ በፈለገው ሁኔታ ለማስቆም በህወሃት ዘንድ መታሰቡን እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ተሞክሮ መክሸፉን ከተለያዩ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ጎልጉል)
Leave a Reply