በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን መንግሥት ለመገልበጥ እሁድ ማታ ለሰኞ አጥቢያ ሙከራ ተደርጎ መክሸፉ ተሰማ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሙከራው መክሸፉንና መንግሥት ሁሉንም ነገር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን በመግለጽ ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ መግለጫ ሰጡ፡፡ በዋንኛው ጎሣ ዲንቃ እና ኑዌር ጎሣ መካከል የተከሰተው ፍጥጫ እስካሁን የለየለት መስመር አልያዘም፡፡ ከወራቶች በፊት የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ንቅናቄ (ኤስ.ፒ.ኤል.ኤም.) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ፓጋን አሙን የአመራር ብክነትና ሌሎች ችግሮች አሉባቸው በሚል እንዲገመገሙ ፕሬዚዳንቱ የመርማሪ ኮሚሽን አቋቁመው ነበር፡፡ ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊው የአመራር ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ ከሥልጣን እንዲነሱ የውሳኔ ሐሳብ ሰጥቷል በሚል ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዋና ጸሐፊውን ጨምሮ የአገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሬይክ ማቻር ከሥልጣናቸው ባለፈው ሐምሌ ወር … [Read more...] about በደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ
News
ዜና
ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ኢህአዴግ በብሔርና በክልል ደረጃ ከተደራጁ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱት ቅድሚያ በመስጠት ለመደራደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ላይ መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ለዚህ ተግባሩ ወዳጅ ጎረቤት አገሮችን፣ አንጋፋ የጎሳ መሪዎችንና ያፈገፈጉ የቀድሞ ተቃዋሚ መሪዎችን እየተጠቀመ ነው። ህወሃት አሁን በአገሪቱ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው የጠቆሙት የኢህአዴግ ሰው ድርጅቱ እርቅ ላይ ከመቼውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ስትራቴጂ መንደፉን አመልክተዋል። "ከውጥረት ለመውጣት ወይም ውጥረትን ለመቀነስ" በሚል ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ የጀመረው አዲሱ የ"ሰላም" መንገድ ህብረ ብሔር ድርጅቶችን ያላከተተበትን ምክንያት አልተብራራም። ይሁን እንጂ ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር … [Read more...] about ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኧን አጎታቸውንና በሰሜን ኮሪያ የሥልጣን እርከን ሁለተኛ የነበሩትን ጃንግ ሶንግ-ታዬክ አስገደሉ፡፡ ግድያውን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም የመንግሥት ሚዲያ እንዳለው ከሆነ አጎትየው ጃንግ “መንግሥት ለመገልበጥ ሙከራ በማድረግ አስጸያፊ ወንጀል ሰርተዋል” ብሏል፡፡ ሰሜን ኮሪያን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የነበሩትንና ሥልጣናቸውን ከመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ኤል ሱንግ የተረከቡት ኪም ጆንግ ኢል ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲሞቱ ወጣቱ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን መንበር ላይ ተቆናጠጡ፡፡ በወቅቱ በሃያዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ኧን ከልምድ ማነስ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ አባታቸው ኪም ጆንግ ኢል አስቀድመው ከጎናቸው የሚሆኑ ሞግዚትና አለማማጅ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ኪም ጆንግ ኢል የጤናቸው ሁኔታ … [Read more...] about ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!
እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
ዛሬ ታህሳስ 3ቀን የሚከበረው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 100ኛ የዕረፍት ዓመት “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
ማዲባ አረፉ!
ደቡብ አፍሪካን ከ1994 – 1999 (እኤአ) በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ ከረጅም ጊዜ ህመም በኋላ ህዳር 26፤ 2006ዓም በ95 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ በፕሬዚዳንትነት መንበር ላይ ከመቀመጣቸው በፊት ለ27 ዓመታት ታስረዋል፡፡ ለነጻነት በተደረገው ትግል እስከ 156 በሚደርሱ የተለያዩ “ወንጀሎች” ተከስሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ራሱ አሸባሪ የነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ “ወንጀለኛና አሸባሪ” በማለት ስም ከሰጣቸው በኋላ አሜሪካም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ “አሸባሪ” የሚለውን ስም ለጥፋባቸው ለረጅም ዓመታት ቆይታለች፡፡ ከዚህም አልፎ ማንዴላን ጨምሮ በርካታ የኤኤንሲ አመራሮችንና አባላትን በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ በማስገባት ለተለየ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር (ለተባበሩት መንግሥታት ዓይነት ስብሰባ) ወደ አሜሪካ የመግቢያ ቪዛ ሲከለከሉ ቆይቷል፡፡ ሁኔታው በዚህ … [Read more...] about ማዲባ አረፉ!
የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ
የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡ ስለቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣ የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንፀባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመሆኑ ዓለም አቀፍ … [Read more...] about የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ
Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence
(Beirut) – Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, in Saudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centers without adequate food or shelter. Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Four Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that the attacks began after November 4, 2013, when authorities resumed a … [Read more...] about Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence
ተዋርደን አንቀርም!!!
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡ መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና … [Read more...] about ተዋርደን አንቀርም!!!
ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው … [Read more...] about ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ
ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል። መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ … [Read more...] about ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!










