አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።
መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር። ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ። ትናንት እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ። ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ። ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር — የሚል ነበር። (ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ – ለአሰራር በሚያመች መልኩ ርዕሱን ቀይረነዋል)
ከዚህ በታች የሚገኙትን አስፈንጣሪዎች በመጫን ዝርዝሩን ይመልከቱ
በሌላ በኩል ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ የሚከተለውን ብሏል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን በድል እና ስቃይ ለመቃወም አዲስ አበባ በተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሶች አሰቃቂ ድብደባና እሰር መፈፀማቸው ቀደም ተብሎ መገለፁ የሚታወቅ ነው፡፡
ቀደም ብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት እስረኞች በአሁኑ ሰዓት ሁለት ቦታ የተከፈሉ ሲሆን ከዚህ በታች ያሉት ፒያሳ ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሲሆን
1ኛ. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀ/መ
2ኛ. አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ም/ት ሊቀ/መ
3ኛ. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አላፊ
4ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ አላፊ
5ኛ. ወጣት አቤል ኤፍሬም አባል
6ኛ. ሰለሞን ወዳጄ አባል
7ኛ እመቤት ግርማ አባል
8ኛ. ዳዊት ፀጋዬ ደራሲና ጻሃፊ (በግል)
9ኛ. እየሩስ ተስፋ አባል
የተቀሩት እዛው መስቀል ፍላወር አካባቢየሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ
1ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ የፓርቲው የፋይናስ ጉዳይ አላፊ
2ኛ. አቶ ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ አላፊ
3ኛ. አቶ አብታሙ ደመቀ የብሔራዊ ም/ቤት አባል
4ኛ. አቶ ዮናስ ከድር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
5ኛ. ዮሴፍ ተሻገር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
6ኛ. ፋሲካ ቦንገር አባል
7ኛ. መርከብ ሀይሌ አባል
8ኛ. አስራት አብርሃም ደራሲና ጻአፊ (በግል)
9ኛ. ንግስት ወንድይፍራው አባል
ezra says
ያሳዝናል! እርገጥ ነው ዜጎቻችንን የሚሽጠው ወያኔ/ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ የወያኔው ዉጭ ጉዳይ ሚነስተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ለማስመሰል፡ ያህል እንኳ “የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው እርምጃ አናዶኛል” ያሉት ሳይደረቅ መልሶ ራሱ ወያኔ በአደባባይ ሲያፈርሰው የሚያሳይ እርምጃ ነው በአዲስ አበባ ሠልፈኞች ላይ የፈፀመው ወንጀል። ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ነው የሚለዉን እዉነታ ሁላችንም ባለመቀበላችን ነው ይሄ ሁሉ ችግር እና ግፍ እየተቀበልን ያልነው። ኢሕኣዴግ የሚባል ነገር የለም ወያኔ የሚባል የ መንደር ወንበዴ እንጅ
በለው! says
>>ከሳውዲ አረቢያ እሰከ ኢትዮጵያ የተዘረጋው የሰው ልጅ በቁሙ የመሸጥ የአቀባይ ተቀባይና የአከፋፋይ ጥቅም ሲነካ.. የህወአት ሙስና ሻንጣ ተሸካሚው የብሄር ብሔረሰብ አቶ ሽመልስ ከማል “ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል።” በአዲስአባባ ከተማ የታየው ድብደባና ፖስተር ነጠቃ ከአረብ ሀገር ጥቃት የቀጠለ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ሆኖ በተመሳሳይም በንፁሕ ኢትዮጵያውያን ላይ መርዝ ጭስ በሀገራቸው ለተጠቀመው ለግራዚያኒ ሀውልት መቆም በተቃወሙ ዜጎች ላይም ተመሳሳይ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ይታወቃል።
*ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ያለቀሰለት ራዕይ ውጤቱ ይህ ነው።
፩) በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ፤ አስፋዉ ሚካኤል መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
-በጥቅም የተሳሰሩ በሸክ አላሙዲን አማካኝነት ገንዘብ የሚቀብሩበት ጥሬ ሀበት ሚዘርፉበትን ሀገር መሳደብና ማንቃሸሽ ደግ ነውን ?”ውሻ በበላበት ይጮሃል”በለው!
-የውጭ ጉዳይ፣ የኢፈርት ዋና ኅላፊውና የኤርትራው በኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ ተቦጭቆለት ለምልካም የሥም ጥበቃና ባለሥልጣናትን መደለያ ምንም ችግር የለም ፖሊስና ወታደር አሰማራ ተባለ። እጅ ነስቶ ተበርክኮ አልቅሶ አባካችሁ መጥታችሁ መሬትም፣ ወርቅም፣ ሰውም እናቀርባለን ግዙ ብሎ ሳይነግድ ለባንክ የምትሆን አትፎ ከተፍ አለ በለው!
፪) ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ “በአዲስ አባባ ከተማ ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ።
-ለመሆኑ ከ፳፫ ሺህ-፴ሲህ ከሚደርስ በሳውዲ ከሚሰቃዩና ከሚገደሉ ብሔር ብሄረሰብ ድሆች የአረብ ፣ቻይናና የህንድ ህዝቦች አይበልጡምን!በመሳሪያም በገንዘብም በእስትራቴጂም በእጅአዙር ዘርፈው የሚአዘርፉት የሚገድሉት ባህል፣ ሃይማኖት፣ ታሪክ፣የሀገር ሉዓላዊነትና አንድነት የሚበትኑት አብረው አደለምን!?
-ለመሆኑ ቻይና ኢትዮጵያውያንን እንደእባብ እየቀጠቀጠ፣ ልጅ እያስፈለፈለ፣ ዓረብ ሴት ልጆቻችንን ስሜት ማርኪያ ያደርገው፣ሕዝብ አፈናቅሎ ደን አቃጥሎ ለሀገሩ ህዝብ አምርቶ የሚጭነው በህወአት/ሻቢያ/ኦነግና አብነግ መልካም ትብብር አደለምን?ለምን ይዋሻል?አላህ ዋክበር ሜንጫ አብዮትና “የሰላቢው ማስታወሻ” ሁሉንም ይናገራሉ።አሁን በጥቅም ስለተለያዩ ለማስመሰል የሚደረግ የአዞ እንባ ፣የቁራ ጩኽት፣መፈክር ሁሉ ጉንጭ ማልፋት ነው።
፫) የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።
-ወያኔ/ህወአት ካሳ ተቀብሏል፤ከአሁኑ መጀመር ያለበት..በሀገር ውስጥ ባሉ ማናቸውም የንግድና የኢኮኖሚ ምንጭ ላይ ማዕቀብ ማድረግ… ሌላው ቀሪው ህዝብ ተሰባስቦ ሲያበቃ በህወአት እና በሌሎች ተቋማት ላይ ሕጋዊ ጥያቄዎችን ማከታተል ህጋዊና ተገቢም ነው። በአንዳንድ አካባቢ በተቃውሞ ሠልፍ አማካኝቶ የሚታይ የጉልበትና ኅይል መጠቀም ጉዳዩን ወደመጥፎ ደረጃ ያደርሳል በሌሎችም የአረብ ሀገራት ሁሉ አንዲዛመት ጭንቀትና የንፁሐንን ዜጎቻችንን ደም መፍሰስ መከራና ስቃይ ያበራክተዋል እንጂ መፍትሔ አይሆንም።
፬) ነብዩ ሲራክ እንደገለፀው ከዚህ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል።
-እዚህ የምንረዳው ብዙ በሽተኞችና መድረሻ ያጡ ወገኖች በቆንስላው እንደተደበቁ ችግሩ ከፋ እንደነበር ነው።መንግስት ወደ ሀገራቸው የመለሰው ቁጥር ከ፳፫ሺህ ፬፻፴፬ ብቻ ሲሆን ደፍረው የሚናገሩትን ሴቶችና ሕፃናት ደብቆ የተወሰኑ ወኔ ቢሶችን ሲያስለፈልፍ ይደመጣል”ሀገራችን ውርተን እንለወጣለን በሉ ኤምባሲውን አድንቁ ሲሏቸው ሀገር ጥለው ሲሄዱ ያልነበረ ሥራ አሁን ሥራ ከየት ይመጣል? ከልምድ እርግጠኛ በመሆን መናገር የሚቻለው ህወአት/ወያኔ በማጅራት መቺነት ያሰማራቸዋል። አሁን ከፍተኛ የግድያ፣ የንብረት ማጥፈት፣ በቀል፣ ቁርሾ፣ ታይቶ የማይታወቅ የማኅበራዊ ቀውስ ይፈጠራል።ከ፬-፮ ሚሊየን ህዝብ በላይ የሚኖርባት አዲስ አባባ ከተማ ለወገኑ ተቆርቁሮ በሀገር ሉዓላዊነትና በአልደፈሬነት ተቃውሞ የወጣው ህዝብ ብዛት ፬፻ ብቻ ነበር!?በለው! እውነትም ይህ ትውልድ ባክኗል፣ላሽቋል፤ቀዝኗል፣ ተንበቅብቋል፤ተሰልቧል መክኗል ክልል ከሀገር በልጧል!!
ነብዩ ሲራክና ግሩም ተክለሃይማኖት ለዘመናት የዜጎቻችንን ሰቆቃ በማለዳ ወግ አጋርተውናል ሀገሩ መንግስት አልባ እንደነበር ግን ጥሩ የሰው ንግድ ላይ የተሳተፈ ወሮ በላ ኪራይ ሰብሳቢ ቡድን እንደሆነም ታዝበናል። ለእነዚህና ለሌችም ጋዜጠኞች እግዝሐብሔር ይጠብቃቸው ምስጋናችንና አድናቆታችን ባሉበት ይድረስልን።
“ኢትዮጵያ እጆቻን ዘርግታ ቅን አሳቢ ልጆቿን ትሰበስባለች!” በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ
ታዛቢው says
የሳውድ አረቢያን መብት ተከላካዩ የወንበዴዎች አስተዳደር ሕዝቡን ሲጨፈጭፍ ዋለ!
ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ ወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራም በነስብሃት ነጋ የሚመራው አሻንጉሊቱ የአቶ ሃይለማርያም አስተዳደር ለአለቆቹ ለሳውዲ አረቢያ በመወገን በርካታ ኢትዮጵያውያንን ሲያንገላታ ዋለ
ላለፉት 22 አመታት ኢትዮጵያውንን ሲገድል, ሲያሰቃይ ሲያስር ሲፈታ የኖረው ፋሺስቱ የወያኔ አስተዳደር ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ለማዋረድ ታጥቆ የተነሳውን, ወገኖችን በየመንገዱ ሲገድሉ በግዳጅ ሲደፈሩ, ሲያሰቃዩ ያሉትን የሳውድ አረቢያን መንግስት በመደገፍ ኢትዮጵያንን ከሳውድ አረቢያ ባላነሰ ሁኔታ ምናልባትም በባሰ መንገድ ማሰቃየቱን ቀጥሎበታል።
በውጭ አገር ሰልፍ ተፈቅዶ በአሜሪካ, በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ሲሰለፉ በገዛ አገራቸው ግን ይህ መብት የለም፤ ለነገሩ የነበደኖን, የነአርባጉጉን ጭፍጨፋ ስናስብ በቅርቡ ካሳውዲ አረቢያው ባልተናነሰ መልኩ እንዲያውም ብዙ ስቃይ በታከለበት አማራውን ወደመጣበት ይመለስ በሚል ረራሶችን ሳይቀር ሲያፈናቅሉ የነበሩትን ጭራሽ በሚኒስትር ደረጃ ሹሞ ያለው ወንበዴ እንክዋን በሰው አገር በአገራችንም የኢትዮጵያዊ ነፍስ ከመጤፍ የማይቆጠር መንግስት አቅፈን ነው ያለነው።
ጥያቄው እራሱን እስከአሁን የትግራይ ነጻ አውጪ ብሎ የሚጠራው ከግራዚያኒ የማይለየውን ኢትዮጵያን ቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ያለውን የነስብሃት ነጋ ወንበዴ እስከ መቼ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታገሰው? እስከ መቼ ነው ሞት ስቃይ ተፈርቶ በራስ አገር ከአገር በቀሉ ቅኝ ገዢዎች ስር የሚተዳደረው? ይህ መንግስት ሰላማዊ ትግል የሚባለው የማይገባው የወንበዴዎችና የሆድ አደሮች ጥርቅም ነው። በኔ አመለካከት የወያኔው ፌዴራልና የሳውዲ አረቢያ ወታደሮች በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው በደል ልዩነት የለውም፤፤
የራሳችሁ መንግስት እንክዋን ሊቀበላችሁ ፈቃደኛ ስለአልሆነ በድላችሁ እዘኑ! እያሉ የሳውድ አረቢያ ወታደሮች ኢትዮጵያውያን ላይ ያላግጣሉ፦
እንዴትና በምን አይነት ሂሳብ ነው አንድ መንግስት የራሱን ሕዝብ የሰው አገር መንግስት ሕዝቡን ሲያሰቃይ, ሲገድል, ሲደፍር የነዚህን የሚሰቃዩ ወገኖች የአገራቸው ዜጎች ተቃውሞ ሲያሰሙ (መንግስት በራሱ አነሳሽነት ማንሳት ሲገባው) እንዴት ለባእድ በማገር ከባእዳን በመተባበር የራሱን ሕዝብ ይጨፈጭፋል?
ተቃዋሚ ተብዬውስ እርስ በርስ ከመጠላለፍ ከነዚህ የቀን ጅቦች ኢትዮጵያውያንን ለማላቀቅ ህብረት አይፈጥርም
የቀንና የግዜ ጉዳይ እንጂ እንዲህ እንዳሩብን አይቀርም፤ ግዜው እየደረስ እነሱም ሞታቸውን እያጣደፉት የዘረፉትን ብር ሳይበሉ ደም እንደሚተፉ ጥርጥር የለውም የዚህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም
Abegaz says
The soldiers I see are weak and poorly armed. Yet Ethiopian youngsters run like hell – like frieghtened tinchel. What kind of youth we have nowadays? If all the jobless youth sits in one place that weak police force has no place to stand. What this jobless youth does is still be retiree on the family income. This is how they fight injustice in Ethiopia. How can the country be free when we have this kind of youth? I think they need some movie training from palestine youth. This youth of ours is so much useless.