የመንጋ ፖለቲካ እና የመንጋ ፍትሕ የትም ሃገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። ተከስቶም ያውቃል። የዘርፉ ባለሙያዎች ዋነኛ ምክንያቱ "በተቋማት እና በመንግሥት የተቆጣ ሕዝብ፣ ከምሬት እና ከቁጭት የተነሳ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ በሥሜት የሚወስደው በቀል አዘል "የፍትሕ ጥያቄ" ነው" ይሉታል። በዚያ መልኩ ስንረዳው መፍትሔው ቀላል ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንጋ ፖለቲካውን እና የመንጋ ፍትሕን በዋነኛነት በሕዝብን ይሁኝታ (ለመልካም እሴት በመገዛት) እና የጸጥታ ኃይሉ በሚወስደው እርምጃ ብቻ ለመቆጣጠር ማሰባቸው ግን ሙሉ አይመስለኝም። ነፃነትል መሸከም አለመቻል አድርጎ መሳላቸውም አልተመቸኝም። ብዙ ትክክለኛ ጥያቄዎች "በመንጋው" ተነስተዋልና። ይልቁንስ ሕዝቡ በለውጡ ላይ ከፍተኛ ተስፋን በመጣሉ ዝቅተኛው ካድሬ እና የአስተዳደር አካል ሕዝቡ የሚፈልገውን ለማድረግ አለመቻሉ ነው። … [Read more...] about የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ
Archives for August 2018
“የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?
1. የአሜሪካ ሃያልነት ከጃፓን እስከ ቻይና ላለፉት አንድ መቶ አመታት አሜሪካ የዓለም ልዕለ-ሃያል ሀገር መሆኗ እርግጥ ነው። የአሜሪካ ሃያልነት ግን ያለ ተቀናቃኝ በብቸኝነት የዘለቀ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በየግዜው ከሚመጡ ተቀናቃኝ ሀገራትና ቡድኖች ጋር ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ስለዚህ የአሜሪካ ሃያልነት እነዚህን ጦርነቶች በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ ነው። ባለፉት መቶ አመታት ከአሜሪካን ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ከገቡት ሃይሎች መካከል የመጀመሪያው ከ1930ዎቹ ጀምሮ ከጃፓን ጋር የተደረገው ነው። በዘመኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደው ትንቅንቅ በመጨረሻ ጃፓንን ለኒኩለር ቦንብ ዳርጓታል። ይህን ተከትሎ ደግሞ አሜሪካ ከሶቬት ህብረት ሩሲያ ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ገባች። የሶቬት ህብረት ተቀናቃኝነት እ.አ.አ. በ1989 ዓ.ም … [Read more...] about “የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?
“እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
ትውስታችሁን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ካሁን በፊት እኔ የጻፍኳቸው፤ ጃዋር የተናገራቸውን ነጥቦች ላስታውሳችሁ። “ኦሮሞዎች ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ አገባድደውታል” ጌታቸው ረዳ (3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ- 2015) “በማሃይም አዝማሪዎች እና በደደብ ምሁራን ጭንቅላት እየተመራችሁ የምታሽቃብጡ ኢትዮጵያውያን ሁላ የኦነግ እና የሻዕቢያ ባንዴራ ይዛችሁ መዝለል እና ማሽቃበጣችሁን ተው” (ጌታቸው ረዳ “የግንቦት 7 ጀሌዎች የኦነግና የሻዕያ ባንዴራ ማውለብልብ ብርቅ ሆኖባቸዋል- 2015) አሁን ደግሞ ጃዋርን ላስታውሳችሁ፡ “ኦሮሚያ በአፍሪካ ውስጥ እንደ ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ብሔሮች የሚኖሩባት አካባቢ የለም። ምናልባት ጆሃንስ በርግ በስተቀር። ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ‘ብሔር’ ‘ብሄረሰብ’ የለም።ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about “እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
የምናውቀውን አብይ እንፈልጋለን!
“ህልም በሥራ ብዛት ይታያል። እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል” “ብዙ ህልም ባለበት ዘንድ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ።” መፅሀፈ መክብብ ምዕ 5 ቁጥር 3 እና 7 አስቀድሞ ቃል ተነገረ፤ ቃሉም የአብይ ነበረ፤ ቃሉም ኢትዮጵያዊነትን ከወደቀበት ማንሳት ነበረ፤ ቃሉም በእኛ ዘንድ ህያው ሆነ፤ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን ከመሪዋ ጎን ቆመን ከፍ አደረግን፤ ከአፅናፍ አፅናፍ ሆ! ብለን ተነሳን፤ በያደባባዩ ተመምን፤ መሪያችንን አብይን እንደ ጨው በተበተንባት ምድር ሁሉ ስሙን ጠራን፤ እነሆ ኢትዮጵያ መሪዋን ሙሴን አገኘች ስንል ብሥራት ተናገርን፤ እርሱም አላሳፈረንም፤ ሙሴነቱን እጃችንን ይዞን አቅፎንና ስሞን እንባችንንም አብሶና ደሙንም ለግሶን አልቅሶና አንሰቅስቆን ከሰቆቃና ከግርፋት ከእስርና ከስደት ነፃ አውጥቶን ወደ ነገይቷ ኢትዮጵያ … [Read more...] about የምናውቀውን አብይ እንፈልጋለን!
An afternoon with a quiet revolutionary
I spent a Saturday afternoon in Los Angeles attending a “Thank You” tour by my hero Andargachew Tsige upon his release from TPLF Woyane Gulag. To remind you how he became a prisoner - he was abducted in broad daylight from an International airport by Woyane security in collaboration with Yemen. It is a brazen act that broke many laws and conventions and it can only be carried by a regime that believes it was answerable to no one. It took its lawlessness into the international arena. It is not … [Read more...] about An afternoon with a quiet revolutionary
ለምንገነባው የፍቅር ድልድይ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ
ሰው ማሰቡን የሚያቆመው ሲሞት ብቻ ነውና ሃሰቡን ለመሰሎቹ በማካፈሉ የሚወገዝበት ዘመን ማክተሙን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሥትራችን፣ ዶ/ር አብይ አህመድ ከቃል በላይ በተግባር ዕውን እነዲሆን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደሚሰሩ በማረጋገጣቸው በእጅጉ ተደስቻለሁ። "ለምን ታስባለህ? ሃሰብህንስ ለምን ታካፍላለህ ?" በማለት የሚገድበው ሳይኖር" ህዝብን ታነቃለህ፣ የግለሰብን ህሊና በማንቃትና የግንዛቤ እጥረቱንም በመቅረፍ፣ በድምርም ህዝብ እንከኔን እንዲያይ በማደረግ ህግ እና ህገመንግስት እኔ ራሴ ሆኜ ሳለ፣ ህገመንግስቱን ጥሰሃል፣ በሥልጣንም ያለአግባብ ባልገሃል፣ በማሰኘት እንደጠላ ታደርጋለህ። ... አንተ እኔ ህዝብን እንዳሻው እየመራው የምሰራው ሥራ የማይታይህ ፀረ-ልማትና ፀረ-ህዝብ ነህ፣ ፀረ ህገመንግስት ነህ፣ ወዘተ። በማለት ሰዎች በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው እነዳይጠቀሙ … [Read more...] about ለምንገነባው የፍቅር ድልድይ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝባቸው ጋር ሊገናኙ ይገባል!
ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ በተደጋጋሚ ከሕዝብ ጋር ቀጥተኛ ሲያደርጉ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝባቸው ጋር ግንኙነት ሳያደርጉ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የጠ/ሚ/ሩ ደጋፊዎችና መላው ሕዝባችን ሁኔታውን እንዲያውቅና አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲወስድ ይፋ ለማድረግ ተገድዷል። በእርግጥ ዶ/ር ዐቢይ በተቀነባበረ በሚመስል ስልት ሁለት ሦስት ጊዜ ያህል ለሕዝብ ዕይታ ቀርበዋል። ሆኖም ከወትሮው በተለየ መልኩ ለውጡን አጥብቀው የሚቃወሙና ለማክሸፍ የሚፈልጉ ኃይሎች ያቀነባበሩት በሚመስል የተከናወነው ከሚዲያ ፍጆታ የማያልፍና በጥያቄ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ለማርገብ የተሰራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህ ሕዝባችን መሪውን የማግኘትና የማነጋገር መብቱ ሊነፈግ አይገባም፤ ይህም ባጭር ጊዜ ውስጥ … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝባቸው ጋር ሊገናኙ ይገባል!
ኢሳያስ ከ“ጎረቤት” ትግራይ በፊት የአማራን ክልል ሊጎበኙ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሰላም ስምምነት ከፈፀሙና ሁለቱ መሪዎች በየአገራቱ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት ከመንግሥት አልፎ በሕዝብ ደረጃ በርካታ ለውጦችን አምጥቶዋል። ይህንን ተከትሎ ኢሳያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ የአማራን ብሔራዊ ክልልን እንደሚጎበኙ ተገልጾዋል። ኤርትራን ከትግራ ጋር እንድታብር ለሚመኛትና በኢሳያስ አጠራር የህወሓት “ጥምብ አንሣዎች” ይህ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራና ውርደት ነው ተብሏል። ፋና ባሰራጨው ዜና ላይ እንደተገለጸው “የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሚመሩት ልኡክ በአስመራ ይገኛል። በቆይታቸውም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ልዩ አማካሪ ከአቶ የማነ ገብረአብ ጋር የኤርትራውያንንና የኢትዮጵያውያንን የሕዝብ … [Read more...] about ኢሳያስ ከ“ጎረቤት” ትግራይ በፊት የአማራን ክልል ሊጎበኙ ነው
Open Letter to those Oromo Elites
If we can’t accept each other as our own kind, based on the common denominator that we are all the same human beings, it is easier for us to be inhumane and do inhumane things to each other. We are all guilty and we take responsibility for our actions and inactions. Now, we all start to see each other as ones created in the image of God. There is no better honor for us to be identified than being known as God’s image bearer. I write this letter to those Oromo elites who have difficulty … [Read more...] about Open Letter to those Oromo Elites
የህወሃትና ኦብነግ የትግል አጋርነት – በንጹሃን ደም ሲታተም አየን!!
በሚያዚያ 1999 አቦሌ በሚባለው የነዳጅ ጉደጓድ መቆፈሪያ ካምፕ 200 የሚጠጉ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ታጣቂዎች በድንገት የፈጸሙት ጥቃት አስደንጋጭና አረመኔነት የተሞላበት ነበር። በወቅቱ ዘጠኝ ቻይናዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰባ አራት ንጹሃን ህይወት አለፈ። በወቅቱ ጥቃቱ የተፈጸመው በሌሊት ሁሉም በተኙበት ሲሆን ግናብሩ ንጹሃንን ከጨፈጨፈ በኋላ ሰፊ መነጋገሪያ የነበረው ጉዳይ እንዴት ጥበቃው ላላ? እንዴት መከለከያና ደህንነት መረጃ አልባ ሆኑ? የሚለው ነበር። በዚህን ወቅት አሁን አገር የሚያተራምሰው ወሮበላ አብዲ ኢሌ የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ነበር። የሚገርመው ይህንን አረመኔነት የተመላበት ድርጊት የፈጸሙት አውሬዎች ተይዘው በክልሉ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባቸው ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ ተደርጎ ፍርዱ ሳይፈጸምባቸው ዓመታትን አስቆጠሩ። ምንጩ በውል በማይታወቅ ገንዘብ … [Read more...] about የህወሃትና ኦብነግ የትግል አጋርነት – በንጹሃን ደም ሲታተም አየን!!