በበርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂ የሆነው የህወሓት ሹመኛው የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ የጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በቁጥጥር ሥር አውሎት ለፍርድ ካላቀረበው በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት ሊጠየቅ እንደሚችል ጎልጉል ጥቆማ ደርሶታል። ሰሞኑን ከህወሓት ጀነራሎች የተሰጠውን የሥራ ተግባር ሲወጣ የነበረው አብዲ ከሥልጣኑ የሚለቅበትና እጁን የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ሰኞ እንደሚሆን አንዳንድ የሶማሊ አክቲቪስቶችና የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች ሲገልጹ ቆይተዋል። በርካታዎች ጤንነቱን የሚጠራጠሩትና ከዕውቀት የጸዳው አብዲ በምክትል ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን ለተመራው ቡድን ሥልጣኑን እንደሚለቅ ቃል ገብቷል የሚለው በስፋት እየተወራ ነው። ሆኖም አረፋፍዶ ይህንኑ ሊቀለብስና በፈለገው አቅጣጫ ሊሄድ ይችላል የሚለውም ከውሳኔው ጋር አብሮ ከግምት ውስጥ የገባ ነው። የአብዲ ኢሌይ … [Read more...] about አብዲ ኢሌ ባስቸኳይ ተነስቶ ለፍርድ ካልቀረበ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተጠያቂ መሆኑ አይቀርም
Archives for August 2018
በክልሎች ጉዳይ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብነት እስከምን ድረስ ነው?
በኢትዮ-ሶማሌ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና መፈናቀል በክልሉ አስተዳደር በኩል መፍትሔ ተሰጥቶት እንዲስተካከል በፌዴራል መንግሥት በኩል የተለያዩ ጫናዎችና የሽምግልና መድረኮች ላይ የእርቅ ስምምነቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ሲብስበት እንጂ ሲቀንስ አልታየም፤ በዚህ ጊዜ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ነገሮችን በቸልታ እንዳያይ የሚያደርገውና ጫን ያለ እርምጃ እንዲወስድ የሚያስችለው የህግ ማዕቀፍ አለው። ይኸውም የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/2003 (95) ሲሆን በዚህ አዋጅ መሠረት የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ወሰኑ እስከምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ ተደንግጓል። የፌደራል መንግሥት በክልሎች የሚፈፀሙ ህገመንግሥታዊም ሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰተቶች … [Read more...] about በክልሎች ጉዳይ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብነት እስከምን ድረስ ነው?
ታላቋ ኢትዮጵያ በተግባር
ባለፈው ቅዳሜ በባሌ ዞን ግንድር ወረዳ፣ ዳሎ ሰብሮ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተ ክርስቲያን እያስመረቁ በነበሩበት ወቅት ሙስሊም ወንድሞቻቸዉ የኦሮሞን ህዝብ የባህል ምግቦች በመያዝ ቤተ ክርስቲያኒቷ ድረስ በመውሰድ አብረው በአንድነትና በፍቅር አስመርቀዋል። ከዚህ ሌላ 11,500ብር በመሰብሰብም ገቢ አድርገዋል። ታላቋ ኢትዮጵያ ማለት ይህች ናት፤ ኢትዮጵያዊነት በተግባር ሲገለጽ እንደዚህ ፍቅር ነው። (ምንጭ፤ Mereja.com የፌስቡክ ገጽ) … [Read more...] about ታላቋ ኢትዮጵያ በተግባር