• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አብዲ ኢሌ ባስቸኳይ ተነስቶ ለፍርድ ካልቀረበ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተጠያቂ መሆኑ አይቀርም

August 6, 2018 02:24 am by Editor 2 Comments

በበርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂ የሆነው የህወሓት ሹመኛው የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ የጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በቁጥጥር ሥር አውሎት ለፍርድ ካላቀረበው በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት ሊጠየቅ እንደሚችል ጎልጉል ጥቆማ ደርሶታል።

ሰሞኑን ከህወሓት ጀነራሎች የተሰጠውን የሥራ ተግባር ሲወጣ የነበረው አብዲ ከሥልጣኑ የሚለቅበትና እጁን የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ሰኞ እንደሚሆን አንዳንድ የሶማሊ አክቲቪስቶችና የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች ሲገልጹ ቆይተዋል። በርካታዎች ጤንነቱን የሚጠራጠሩትና ከዕውቀት የጸዳው አብዲ በምክትል ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን ለተመራው ቡድን ሥልጣኑን እንደሚለቅ ቃል ገብቷል የሚለው በስፋት እየተወራ ነው። ሆኖም አረፋፍዶ ይህንኑ ሊቀለብስና በፈለገው አቅጣጫ ሊሄድ ይችላል የሚለውም ከውሳኔው ጋር አብሮ ከግምት ውስጥ የገባ ነው።

የአብዲ ኢሌይ መጨረሻ ሲጀምር በሚል ርዕስ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሒውማን ራይትስ ዎች “We are Like the Dead’: Torture and other Human Rights Abuses in Jail Ogaden, Somali Regional State, Ethiopia” በሚል ርዕስ ያወጣውን የ88 ገጽ ዘገባ በመንተራስ በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ማለቱ ይታወሳል።

“ይህ የግፍ ቁልል የተከማቸበት ዘገባ፤ በኦጋዴን እስር ቤት ግፍና ስቅየት በመፈጸምና በማስፈጸም ተዋናኝ የሆኑትን የፌዴራሉ መንግሥት የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌንና ሌሎች ከፍተኛ የሶማሊ ክልል ባለሥልጣናትን ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ የሚያደርግ ነው”።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአብዲ ኢሌ ላይ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ የግፉ ገፈት ቀማሾችና የሶማሊ ክልል ወገኖች እየወተወቱ ነው። ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉ ጎልጉል ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ አብዲ ኢሌ በአገር ውስጥ ለፍርድ ቢቀርብ የተሻለ ይሆናል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የዐቢይ አስተዳደር ቸልተኝነት ካሳየ ወይም የፖለቲካ አካሄዱን መስመር ለማስያዝ በሚል በሌላ አቅጣጫ ከሄደ አብዲ ኢሌ በውጭ አገር ለፍርድ እንዲቀርብ ዓለምአቀፍ የእስር ማዘዣ ሊወጣበት ይችል ይሆናል። ይህንንም ለመተግበር የቆረጡ ወገኖች እንዳሉ መረጃው ያመለክታል። የዛሬው ውሎና ውሳኔ ወደ ዓለምአቀፉ መድረክ የመሄድ ወይም አለመሄድ ሁኔታን ይወስነዋል ተብሏል።

ይህንን ዘገባ እያዘጋጀን ባለበት ወቅት ጅጅጋ ውስጥ አብዲ ኢሌን ከሥልጣኑ ለማውረድ ስብሰባ መጀመሩንና አብዲ ሲወርድ በቦታው ይተካል ተብሎ የታሰበው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚ/ር አህመድ ሺዴ በስብሰባው ላይ የሚገኝ መሆኑ በተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ እየተዘገበ ይገኛል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: abdi illey, Full Width Top, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Amanuel ze Ambo says

    August 6, 2018 05:40 pm at 5:40 pm

    ሴረኛዋ እና በየበታችነት ስሜት የምትሰቃየው ለታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ በማይመጥን ስብዕና የተከሰተችውና መቼም መች መጥበብ እንጂ መስፋትን፣ መበጥበጥ እንጂ መርጋትን ፣ሁከት እንጂ ሰላምን፣ ጠባብ አዕምሮዋ የማይቀበልላት ሁከተኛዋንና አናሳዋን ቡድን ህወሀትን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አርቀን ካልቀበርናት ውላ ባደረች ቁጥር በምትሰራቸው የክፋት እና የተንኮል ስራዋ መብሰክሰኩ ብቻ አላዋጣም ።

    ይህች የጥፋት መልዕክተኛ እና ባንዳ ቡድን እርሷም እንደ አብዲ ኤሊ ያሉ ወፍራም ገለባዎችን በባንዳነት ቀጥራ ሀገር ለማመስና እንዲህ ልቡ እንዳበጠ ጥጋበኛ ጎረምሳ ለያዥ ለገራዥ ማስቸገሯ ተገቢ እና ተመጣጣኝ ቅጣትን ባለማግኘቷ የዜጎችን ታጋሽነት እና ሆደ ሰፊነት ከፍርሃት በመቁጠሯ ነው ። ስለዚህ ይህቺን ለአዛይ እንኳ የምታስቸግር ሙልጭልጭ ሞላጫ የጥፋት ቡድን ላትድን እና ላትለወጥ ማስታመሙ በሽታዋን ወደጤነኛው ከማስተላለፍ ውጭ አንዳችም ፋይዳ የሌለው በመሆኑ” ወያኔን ካዳነ ይልቅ የገደላት ጸደቀ” በሚል ዘመቻ የማያዳግም ርምጃ ወስዶ ሀገርን እና ሕዝባ ከዚህች ቆሻሻ ማጽዳት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት ።

    ባንዳዋ ቡድን መገንጠልን እንደ አይጥ መሞከሪያ ያደረገችው አብዲ ኤሊ በልኳ የተሰራ ከመሆኑ ጋር መጪውን እንዳያስብ ስብ የዘጋው ጠባብ አእምሮው ማስተዋልን ተነስቷል ፤ ዳሩ ከህወሃት ውሎ ጤነኛ ቢሆን እና የነገን ቢያስብ ነበር እጃችንን በበአፋችንአስጭኖ የሚያስገርመን!!
    ከማህጸኗ የተቀፈቀፉ (የተፈለፈሉ) አንዳንዶች ደግሞ ሊያዝጉን እና ሊያዘናጉን መሻታቸውም ይገርማል፤ ይህች የባንዳ ስብስብ ራሷ ለራሷ በሰየመችው ወያኔ በሚል ስሟ ስንጠራት እንዲህ አትበሏት ወያኔ የሚለው ስም ትግራዋይን ሁሉ ይጠቀልላልና ይሉናል ፣ ክፉ ግብሯን ገልጠን ህወሃት እንዲህ አደረገች ስንል ህወሃት ስትሉ ለውጥ ፈላጊውንም አብራችሁ እየጨፈለቃችሁ ነው እና አጥፊዋን ቡድን ህወሀት ብላችሁ አትጥሩ ይሉናል፤ ስለዚህ በእነርሱ ስሌት ይህችን ውሉደ እፉኝት ቡድን ደባዋን እና ጥፋቷን እያየን እርሷም ማጥፋቷን እያወቅን በስሟ ጠርተን እንዳናወግዛት እንዳንፋረዳትም በገደምዳሜ ጥብቅና ይቆሙላታል ።

    በእነርሱ ስሌት ይህችን ቡድን ማን ብለን እንጥራት ይሆን? ኦነግ? ግንቦት ሰባት? ምክንያቱም ከዚህ በፊት ርኩሰቷን በሙሉ በነዚህ ድርጅቶች ስም ስትሰራ ኖራለች የሚታለሉላትንም ስታታልልበት ኖራለች እንግዲህ ግላግልቶቿ እርሷ ባጠፋች ሌላው ላይ አላክኩልን ከማለት ውጭ ይሄ ሃሳባቸው በምን ይተረጎማል? እውነት እንነጋገር ከተባለ ከእባቧ እንቁላል (ከህወሀት) የርግብ እንቁላል አይጠበቅም፤ የምናየውም ይኼንኑ ነው ። ተለያይተናል ህወሃት ጸረሰላም ናት የበሰበሰች የገማች ናት እያሉ የተለዩዋት ሁሉ በቀብሯ ዋዜማ እየተጠራሩ ሊታደጓት ሲታትሩ እያየን ከዚህች እባብ እንቁላል እንዴት ርግብ እንጠብቅ???
    “”” ቢሆንም ከነፈሩት ከነኚህ መሃል ኢትዮጵያዊነትን ያልካዱ እንደነ ገ/መድህን አርዓያ እና አስገደ ገ/ሥላሴ ዓይነት እድለኞችን እንደ ብርቅ እናያለን ፤ “””

    የሆነው ሆኖ ሕወሃት መቀመቅ መውረዷ አይቀሬ ነው ይህን እርሷም በደምብ ታውቀዋለች መፈራገጧም ከመላላጥ ውጭ ምንም እንደማይፈይድላት በደምብ ታውቃለች ግብዝ ግን ስለሆነች የጀግና ሞት መሞት ያምራታል ህወሃት አህያም ናትና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ዓይነት ብሂል አላት ፤ ህወሃት እድሜ ዘመኗን ጀግና መሆን ሳትችል እንደበረገገች እና እንደሰጋች ስለኖረች በፈሪ በትሯ ብዙዎችን አቁስላለች ገዳድላለች ፍርሃቷ ጥግ ስለሌለውም ያጠቃኛል ብላ ያሰበችው ሰው በሕዝብ መካከል ቢታይ ሕዝቡን በጅምላ ጨርሳ የምትፈልገውን ሰው አስከሬን ከፈጀቻቸው ሰዎች መሀል የምትፈልግ ጉደኛ እና ቦቅባቃ ቡድን ናት እንዲህ የኖረችው ይህች አናሳ ቡድን ሞቷን የጀግና ሞት ለማስመሰል ትደክማለች እንጂ የሞቷ ዋዜማ ላይ መሆኗን እንኳን እኛ እርሷም በደምብ ታውቀዋለች ።

    ጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ለሃጥአኑ እና ለቀን ጅቦቹ በመጣው መቅሰፍት እንዳይጎዳ በተደጋጋሚ ተመክሯል ተዘክሯል ግን የሰማ አይመስልም ይህ በመሆኑ ዓለም በስስት የሚመለከተውን እና ከጎንህ ነን እያለ የሚያበረታውን የህዝብ ልጅ ዶር አብይን ለማስገደል የሄደበት መንገድ ቢከሽፍበትም ለጊዜውም ቢሆን መቀሌ ላይ መሽጎ ከህግ ዓይን ለመሰወር የሚያደርገው መፍጨርጨር የት እንደሚያደርሰው ጊዜ ያሳየናል፤ ይኸው አናሳው እና ፈሪው የጥፋት ቡድን መቀሌ ላይ መሽጎ ጅጅጋን በውክልና እየበጠበጠም ይገኛል አዎን ለጊዜው የፈሪ በትሩን መዝዞ ዜጎችን በጠራራ ፀሐይ ገድላል ቤተክርስቲያን አቃጥሏል አገልጋይ ካህናቶቿን ገድሏል በዚህም ፈሪው ቡድን በመግደሉ መሸነፉን በሚገባ እያረጋገጠልን ነው ። ያልገባው ግን ላፈሰሰው ደም ሁሉ በእጥፍ እደሚከፍል አለመረዳቱ ነው ።

    በመሆኑም ነገር ሲድን እና ሲሞት ያለውን ሁኔታ በውል ላልተረዳ ደናቁርት ስብስብ አናሳ ቡድን የእጁን መክፈል ተገቢ እና ብቸኛም አማራጭ ነው ፤ ከዚህ በኋላ ይህን አናሳ ቡድን ለማዳን የሚታትር እርሱ የህዝብ ጠላት እንጂ ወዳጅ ሊሆን አይችልም ሰፊ እድሉን ያልተጠቀመና የበሰበሰ ቅርፊቱን መሸለት ካልፈለገ እና መቼም መች ጥፋት እንጂ ልማት የማይገኝበትን ይህን የጥፋት ቡድን ማስታመም በታላቋ ሀገር ላይ በማላገጥ ቡድኑም መምሰል እና ማከል ነው ፤ በመሆኑም ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ አጥፊውን ለማጥፋት ሁሉም ይነሳ!!!

    አሳድደህ በለው ያንን አመጸኛ ተገንጣይ ወንበዴ
    መድረሻ አሳጣው ግረፈው አሳድደህ አስኪደው በዳዴ
    ማረኝ አይለምደኝም በቃኝ ብሎ ካላመነ እንዳትለቀው
    ያንተን ማንነት ይረዳ እስኪገባው ልክህን ይወቀው
    ሲል ጥላሁን ገሰሰ እንዳዜመ ያንኑ ማድረግ ተገቢ ነው!

    ዋዜማ ላይ ያለው ድል ዕለቱን ናፍቋልና ያን ለማየት ሁሉም ይበርታ ሞት ለጠባቦች ድል ለኢትዮጵያውያን!!

    Reply
  2. Lusif says

    August 8, 2018 05:05 am at 5:05 am

    What is power? What is being powerful? What is being powerless? Lately we do not see those powerful guys on TV windows. That is powerlessness to me and wished to know what they are feeling. Power made them blind and feel and act they way they did. When in power, they may not know what they felt and did. Do they feel their irresponsible deeds when they are powerless now? If they do they are learning and regranting and deserve forgiveness. If they do not, the Ethiopian people need to say enough is enough.
    I do believe in love and forgiveness. Those obviously committed crime, but were set free through love and forgiveness, should genuinely demonstrate that they deserve, by showing at least refrain
    From other evil deeds.
    I do not by that those criminals retreated and barracked in a certain corner. To me it is like both, depriving them opportunity to regret and give them freedom to do their dirty works. That tells me that love and forgiveness do not work with those individuals. Justice is the only solution, the only solution to make them regret and ask for forgiveness.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule