• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በክልሎች ጉዳይ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብነት እስከምን ድረስ ነው?

August 6, 2018 12:12 am by Editor Leave a Comment

በኢትዮ-ሶማሌ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና መፈናቀል በክልሉ አስተዳደር በኩል መፍትሔ ተሰጥቶት እንዲስተካከል በፌዴራል መንግሥት በኩል የተለያዩ ጫናዎችና የሽምግልና መድረኮች ላይ የእርቅ ስምምነቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ሲብስበት እንጂ ሲቀንስ አልታየም፤ በዚህ ጊዜ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ነገሮችን በቸልታ እንዳያይ የሚያደርገውና ጫን ያለ እርምጃ እንዲወስድ የሚያስችለው የህግ ማዕቀፍ አለው። ይኸውም የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/2003 (95) ሲሆን በዚህ አዋጅ መሠረት የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ወሰኑ እስከምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ ተደንግጓል።

የፌደራል መንግሥት በክልሎች የሚፈፀሙ ህገመንግሥታዊም ሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰተቶች ሲያጋጥሙ ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ቅዳሜ ያየነው የመከላከያ ሠራዊት ጣልቃ ገብነት አንዱ ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ ሊወሰዱ የሚችሉ ተግባራትስ በምን አግባብ ወደ ህጋዊነት ሊመጡ ይችላሉ የሚለው ነጥብ ዋናውና አንኳሩ ነው። የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብቶ ያረጋጋውን ሰላምና ደህንነት ለማን አስረክቦ ይወጣል? ለክልሉ ፖሊስ ያስረክብ የሚባል ከሆነ ከከዚህ ቀደሙ የከፋ ቀውስ ሊያጋጥመን ይችላል፤ ክልሉንስ ማን ይምራው የሚለው ጥያቄም ሌላኛውና መሰረታዊ ነጥብ ነው።

በአዋጁ አንቀፅ 14(2)(ለ) ስር እንደተደነገገው የፌዴራሉ መንግሥት የክልሉን ምክር ቤትና የክልሉን ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚ አካል በማገድ ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የመወሰን ስልጣን አለው። ጊዜያዊ አስተዳደሩም ክልሉን በበላይነት ከመምራት ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩ የአስተዳደር አካላትንና የፀጥታ ክፍል ኃላፊዎችን ለፍርድ እስከማቅረብ የሚደርስ ሥልጣን የሚኖረው ይሆናል።

ስለሆነም የቅዳሜው የመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ ግቡን መምታቱ ሲረጋገጥ በቀጣይ የሚደረገው ተግባር ክልሉን ለጊዜያዊ አስተዳደር የማስረከብ ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው።

እነዚህ የሽግግር ሂደቶች ህጋዊነታቸውን ጠብቀው በመሄድ ለክልሉ ሰላም መደፍረስ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል የክልሉን ሰላምና መረጋጋት የማስቀጠል ኃላፊነት ለፌዴራል መንግስቱ የተሰጠ ስለሆነ በአንዳንድ ወገኖች እየተነሳ ያለው ትችት ህጋዊ መሰረት የሌለው ሲሆን የፌዴራል መንግሥት የዛሬውን እርምጃ ለመውሰድ በመዘግየቱ ቢወቀስ እንጂ አብዲ ኢሌን ጠምዝዞ ከስልጣን በማውረዱ ተጠያቂ መሆን አይችልም። የክልሉ ምክር ቤትም ቢሆን ክልሉን የማስተዳደር አቅሙ ከተሽመደመደ ከህዝብ የተሰጠውን ውክልና እስከመነጠቅ የሚደርስ ተግባር ሊፈፀምበት እንደሚችል ከህጉ መረዳት ይቻላል።

በጋምቤላ ክልል ከአስራ ሶስት አመታት በፊት ተከስቶ የነበረውን የእርስበርስ ግጭት ለማስቆም በማሰብ የወጣው አዋጅ ዛሬ ለሌላ ተግባር ተመዞ የወጣበትን ሁኔታ እያየን ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ በፌዴራል መንግሥቱ የሶህዴፓን ወክለው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ክልሉን በጊዜያዊነት ሊመሩ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ መሆኑን አንዳንድ ሹክሹክታዎች እየተሰሙ ነው።

በታደሰ ተክሌ የቀረበ ምልከታ፤ ከፌስቡክ ገጹ የተወሰደ።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Law Tagged With: abdi illey, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule