• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የምናውቀውን አብይ እንፈልጋለን!

August 18, 2018 08:05 am by Editor 1 Comment

“ህልም በሥራ ብዛት ይታያል። እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል”

“ብዙ ህልም ባለበት ዘንድ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ።” መፅሀፈ መክብብ ምዕ 5 ቁጥር 3 እና 7

አስቀድሞ ቃል ተነገረ፤ ቃሉም የአብይ ነበረ፤ ቃሉም ኢትዮጵያዊነትን ከወደቀበት ማንሳት ነበረ፤ ቃሉም በእኛ ዘንድ ህያው ሆነ፤ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን ከመሪዋ ጎን ቆመን ከፍ አደረግን፤ ከአፅናፍ አፅናፍ ሆ! ብለን ተነሳን፤ በያደባባዩ ተመምን፤ መሪያችንን አብይን እንደ ጨው በተበተንባት ምድር ሁሉ ስሙን ጠራን፤ እነሆ ኢትዮጵያ መሪዋን ሙሴን አገኘች ስንል ብሥራት ተናገርን፤ እርሱም አላሳፈረንም፤ ሙሴነቱን እጃችንን ይዞን አቅፎንና ስሞን እንባችንንም አብሶና ደሙንም ለግሶን አልቅሶና አንሰቅስቆን ከሰቆቃና ከግርፋት ከእስርና ከስደት ነፃ አውጥቶን ወደ ነገይቷ ኢትዮጵያ መንገድ በመደመር ጉዞ መጋቢት 24 ቀን 2010 አስጀምሮን እስከ ሐምሌ መገባደጃው ከጎናችን ለቅፅበት ሳይጠፋ፤ ስንጀግን እየተደሰተ፤ ስናጠፋ እየወቀሰ፤ ስናኮርፍ እየመከረ፤ ስንበድል ይቅር እያለ፤ ወደ ሁዋላ ስናፈገፍግ እያበረታን፤ ስንቃወመውም እያዳመጠን ማዕበሉን እየቀዘፈና ባሻገርም እየተመለከተ ከጎናችንና ከፊታችን ከቶም ሳናጣውና ሳይጠፋብን ሳይርቀንና ሳንራራቅ መራን። ለአራት ወር ገደማ የምናውቀውና የሚያውቀን አብይ መሪያችን ይህ ነው።

ከእኛ ጋር ለመነጋገር፤ ችግራችንን ለመስማት በደላችንን ለመጋራት፤ ሀዘናችንን ለማፅናናት የምናውቀው መሪያችን አብይ ቀጠሮ አይዝም። ሀገር ስትታመስ፤ ገንጣይ ሲረባረብ፤  የዕምነት ቤቶች ሲጋዩ፤ ቀሳውስት ሲፈጁ፤ የሚወደው ህዝብ በጭንቅ ማጥ ውስጥ ገብቶ ሲዳክር፤ መውጫ መግቢያው ሲጨንቀው የምናውቀው አብይ ዝም አይልም። የምናውቀው አብይ ከተፎ ነው። በፈገግታ በታጀበ ፊቱ ፍካትን ፍቅርንና መቻቻልን እየናኘ፤ እንደ ሌሊት ተወርዋሪ ኮከብ በሚበራው አይኑ ብርሃንን ተስፋንና ዕምነትን እያሳየ አቧራ የቃመ ፀጉራችንን፤ እድፍ የተሸከመ ልብሳችንን የሻከረ እጃችንን ሳይጠየፍ የሚዳስሰን ሳይቀፈው የሚያቅፈንና የሚጨብጠን የምናውቀው ሙሴያችን አብይ መሪያችን የሩቅ ሰው ከሆነብን ሰነበተ። የምናውቀው አብይ መሪያችን የቅርብ እሩቅ ሆነብን። ብዙ መናገር ወይም ብዙ መፃፍ በወደድን። ሆኖም አሁን ላይ የኢትዮጵያን ህመም በብዕር ምጥ በቃላት ንግግርም ለዘመናት ሲያስተጋቡ የኖሩ ‘የታወቀ’ ስም ወይም የፖለቲካ ድርጅት ሥልጣን የሌላቸው ከመፃፍም ሆነ ከመናገርም ለመታቀብ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ እኛም የዚሁ አካል ነንና ከዚህ በላይ ብዙም አንል። የኢትዮጵያ ጭንቅ የሚያስጨንቀው ሁሉ ግና ይገባዋልና እንግባባለን።

ይህ የመደመር ጉዞ ጠቢቡ መክብብ ‘ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ ብዙ ከንቱ ነገር አለ’ እንዳለው ዛሬ በኢትዮጵያችን በተለይም አብያችን ከአሜሪካ ጉዞው ከተመለስ ወዲህ  አብይ በሌለበት ምድሪቱ በብዙ ከንቱና አብያዊ ጉዟችንን በሚያጨናግፉ ዲስኩሮችና የድል አጥቢያ አርበኝነት አባዜ ተወርራለች። ከቦሌ እስከ ሚለንየም አዳራሽ የሚሰማው ፉከራና ትርምስ አስደንግጦናል። የሁሉም ተቃዋሚ ‘ተፎካካሪ’ ድርጅት/ፓርቲ ዝግጅት ለዚህ ከቦሌ እስከ ሚለንየም አዳራሽ ለሚደረግ የአቀባበልና የዲስኩር ‘ገድል’ ሆኗልና ወይም ይመስላልና። ኢትዮጵያንና አብይን እንዴት ‘እንታደግ?’ የሚል ዝግጅትና መንፈስ የውይይትና የተግባር መድረክም አይታይም። ሁሉም ለየራሱ ገድልና ታሪክ ጥድፊያ ላይ ነው!! ከወዲያ ማዶም ነጋሪቱ ከጥቂት ወራት በፊት ባልታየ ድምፀት በህወሃት አጋፋሪዎች እየተጎሰመብንና እየተፎከረብን ይገኛል። በዚህ ሁሉ ሆያሆዬ የምናውቀው አብይ ከጎናችን የለም። አለ ብለው ከቤተመንግሥት በአፈቀላጤዎቹ በኩል (እንደ በፊቱ በቀጥታ አይደለም) የሚያሳዩን የፎቶ ምስሉን እንጂ የምናውቀውንና የሚያውቀንን አብረን የተጓዝነውን ሰዋዊውን አብይ መሪያችንን አብይ ወንድማችንን አብይ ልጃችንን አይደለም።

እኛ ቀቢፀ ተስፈኞች አይደለንም። በሃያ ሰባት አመት የስደትና የፅናት ዘመን፤ ለአንዲትም ደቂቃ ለህወሃትና ህወሃታውያን ለጎጠኞችና ለሀገር በታኞች አጎብድደን አልያም ተመሳስለን ኖረን አናውቅም። የሴራ ፖለቲካም የእኛ ቁማር አይደለም። አብይን የደገፍነው ጎርፉ ሲያስገመግምም አይደለም። ‘አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው’ እንዲሉ እኒያ አብናቶቻችን የለማንና የአብይን ጉዞ ገና ከጠዋቱ በአደባባይ የደገፍነው አያያዝና አካሄዱን ለይተንና አይተን  የህወሃትን ‘ጭብጦ’ (ሥልጣን) ለመንጠቅም ብቸኛው መንገድ የእነርሱ መሆኑን ተረድተን እንጂ። እና እኛ ሴረኞች ወይም የሴራ ፖለቲካ አራማጆች አይደለንም። በነፈሰበትም አንወዛወዝም። ግን ደግሞ ሰሞኑን ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት የሚተላለፈውን ‘ድብብቆሽ’ ለማወቅና ለመረዳት ደግሞ የህይወት ተሞክሮ ብቻ በቂ ነው። ከዚህ በላይ ብዙ ማለት አያሻንም። እና ድብብቆሹ ይብቃ!!! አብይ ናፍቆናል!! የምናውቀውን አብይ ማግኘትና ማነጋገር እንፈልጋለን!!! ወደ ጨለማው ዘመን እንዳንመለስ ከተፈለገ አብይ፤ የምናውቀው አብይ፤ በነፃነት የሚፍለቀለቀው አብይ አደባባይ ወጥቶ እንዲመራንና ከጎኑም እንድንቆም በነፃነት ልናገኘው እንፈልጋለን!!! የሚሰማ ጆሮ የሚያስተውል ልብ ያለው ይስማ ያስተውልም!! ጊዜው ሳይሄድ ምልሽ እንፈልጋለንና!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

ነሀሴ 2010 ዓ/ም
ኦገስት 2018
ሲድኒ አውስትራሊያ
mmtessema@gmail.com 


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Adoniyas says

    August 23, 2018 12:15 am at 12:15 am

    ይቺ ሃገር ቀዳዳዋ ብዙ ነው ብሏል እሱ ራሱ
    ….ስማ የውልህ አብይን በረባ ባልረባው በመቅረጸ መስኮት መጠበቁን ብንተው ነው የሚሻለን ብዙ ከማውራት ትንሽ ዝም ብሎ መስራት ያዋጣል ስሜታችንን ሁልጊዜ እያከከ መኖር አይችልም ፡፡ መስራት ማደራጀት መምራት አለበት፡፡ እንደሚታወቀው በአሁን ጊዜ ከውስጥ በኩል ከፍተኛ የማጨናገፍ ግፊት እየተደረገበት ነው ለእያንዳንዱ ነገር መልስ ለእኛ መስጠት አይኖርበትም እንደ መንግስት የሚሰሩ አሰራሮች አሉ፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule