ሰው ማሰቡን የሚያቆመው ሲሞት ብቻ ነውና ሃሰቡን ለመሰሎቹ በማካፈሉ የሚወገዝበት ዘመን ማክተሙን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሥትራችን፣ ዶ/ር አብይ አህመድ ከቃል በላይ በተግባር ዕውን እነዲሆን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደሚሰሩ በማረጋገጣቸው በእጅጉ ተደስቻለሁ።
“ለምን ታስባለህ? ሃሰብህንስ ለምን ታካፍላለህ ?” በማለት የሚገድበው ሳይኖር” ህዝብን ታነቃለህ፣ የግለሰብን ህሊና በማንቃትና የግንዛቤ እጥረቱንም በመቅረፍ፣ በድምርም ህዝብ እንከኔን እንዲያይ በማደረግ ህግ እና ህገመንግስት እኔ ራሴ ሆኜ ሳለ፣ ህገመንግስቱን ጥሰሃል፣ በሥልጣንም ያለአግባብ ባልገሃል፣ በማሰኘት እንደጠላ ታደርጋለህ። … አንተ እኔ ህዝብን እንዳሻው እየመራው የምሰራው ሥራ የማይታይህ ፀረ-ልማትና ፀረ-ህዝብ ነህ፣ ፀረ ህገመንግስት ነህ፣ ወዘተ። በማለት ሰዎች በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው እነዳይጠቀሙ የሚያደርግ ሥርአት አክተሞል። እነዚህ “ሊበልዋትን ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ይሏታል። በሚል ቅኘት የሚጓዙና የሚገዙ ሸባቢ መንግስታዊና ሥልጣናዊ አሰተሳሰቦችና ድረጊቶች በዚህ በዲጂታል(አለም በቴክኖሎጂ ተራቆ አለም በጠበበችበት ዘመን) ላይመለሱ ተሰናበተዋል።” በማለት የልብ ልብ ለዴሞክራሲ ርሃብተኞች ሰጥተዋል። በርግጥም እንዳንናገር የሥልጣን አለንጋ ይዞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ “ዋ! ውርድ ከራሴ …” በማለት የሚየሥፈራራን፣ የሥልጣን ጠመንጃ ዛሬ የለም። ነገ እንደሚከሰት ግን ምንም ማረጋገጫ የለንም።
ዘንድሮ
ዘንድሮ፣ ዘንድሮ፣ ዘንድሮ
የሥንቱ ተወርቶ የሥንቱ ተነግሮ፡፡
ዘንድሮ!
ወሎ በማደሩ ተዋሀደንና
መጥፎ ከደህና ጋር ተማታብንና
ብዙ ዓመታት አልፈው ዛሬ ነቃንና
ያስቀን ጀመረ ግራ ገባንና፡፡
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply