• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?

August 19, 2018 03:15 pm by Editor Leave a Comment

1. የአሜሪካ ሃያልነት ከጃፓን እስከ ቻይና

ላለፉት አንድ መቶ አመታት አሜሪካ የዓለም ልዕለ-ሃያል ሀገር መሆኗ እርግጥ ነው። የአሜሪካ ሃያልነት ግን ያለ ተቀናቃኝ በብቸኝነት የዘለቀ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በየግዜው ከሚመጡ ተቀናቃኝ ሀገራትና ቡድኖች ጋር ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ስለዚህ የአሜሪካ ሃያልነት እነዚህን ጦርነቶች በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ ነው። ባለፉት መቶ አመታት ከአሜሪካን ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ከገቡት ሃይሎች መካከል የመጀመሪያው ከ1930ዎቹ ጀምሮ ከጃፓን ጋር የተደረገው ነው። በዘመኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደው ትንቅንቅ በመጨረሻ ጃፓንን ለኒኩለር ቦንብ ዳርጓታል። ይህን ተከትሎ ደግሞ አሜሪካ ከሶቬት ህብረት ሩሲያ ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ገባች። የሶቬት ህብረት ተቀናቃኝነት እ.አ.አ. በ1989 ዓ.ም ከጀርመን ግንብ ጋራ አብሮ ወደቀ።

ከዚያ በመቀጠል አሜሪካን በግሎባላይዜሽን ስም በዓለም ሀገራት ላይ እንዳሻት ስትፈነጭ ሀገርና ድንበር የሌለው ተቀናቃኝ ኃይል የመጣ ሲሆን እሱም “ሽብርተኝነት” ይባላል። በተለይ በኒውዮርክ መንትያ ህንፃዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካን መንግስት ዓለም-አቀፉን የፀረ-ሽብር ዘመቻ አወጀ። “ከእኔ ጎን ያልቆሙ የአሸባሪዎች ደጋፊ ናቸው!” በሚል በዋናነት ምስራቅና ሰሜን አፍሪካን፣ ምዕራብና ደቡባዊ አውሮፓን፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢሲያ ሀገራትን ማተራመስ ጀመሩ። አሜሪካ የምትከተለው የውጪ ፖሊሲና ለደሃና ታዳጊ አገራት የምታደርገው ድጋፍና ትብብር በዋናነት ከዓለም-አቀፉ የፀረ-ሽብር ዘመቻ ጋር የተቆራኘ ሆነ። አሜሪካ ከፍተኛ እርዳታ የምትሰጣቸውን ሀገራት እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል።

ከላይ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ከአሜሪካ ከፍተኛ እርዳታ የሚያገኙት ሀገራት ዓለም-አቀፉ የፀረ-ሽብር ዘመቻ በስፋት በሚካሄድበት የዓለም ክፍል ነው። ለምሳሌ ኢራቅና አፍጋኒስታን በቀጥታ በአሜሪካ ጦር ወረራ የተፈፀመባቸው ናቸው፣ እስራኤል በፍልስጤሞች ላይ በምትፈፅመው ግፍና በደል በመካከለኛው ምስራቅ ሽብርተኝነት እንዲፈጠርና በመላው ዓለም እንዲስፋፋ አድርጋለች፣ ግብፅ፥ ጆርዳን፥ ሲሪያና ፓኪስታን የሽብርተኞች መፈልፈያ ቋት ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ፥ ኬኒያና ኡጋንዳ ደግሞ በዓለም አቀፉ የፀረ-ሽብር ጦርነት የአሜሪካ አጋሮች ናቸው። በአጠቃላይ የአሜሪካ ወታደራዊና ዴፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዋናነት በሽብርተኞችና ሽብርተኝነት ላይ ብቻ ያጠነጠነ ነበር ማለት ይቻላል።

2. የቻይና ሃያልነት እና ስልት

አሜሪካ ከሽብርተኞች የተቃጣባትን ጥቃት ለመመከት በምትሯሯጥበት ወቅት ግን ሌላ ተቀናቃኝ ኃይል ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ አቅሙን አሳድጎ ከአሜሪካን ጋር ጫማ መለካካት ጀመረ። ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ጃፓን፣ ሶቬት ሩሲያ እና ሽብርተኝነት ቀጥሎ የአሜሪካንን ልዕለ-ሃያልነት መቀናቀን የጀመረው ሃያል ሀገር “ቻይና” ይባላል። ቻይና በዓለም ሀገራት ላይ በወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ስር የምታሳርፈው ከመሰረተ ልማት ግንባታና የብድር አሰጣጥ፣ እንዲሁም በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ባለመግባት ነው። ቻይና ይህን ፖሊሲ ተግባራዊ ባደረገችበት ወቅት የቀድሞ የዝምባብዌ ፕረዜዳንት ሮበርት ሙጋቤ “We turn our face to east where the sun rises, give our back to the west where the sun sets” ማለታቸው ይነገራል።

በዚህ መሰረት እንደ ዓለም-አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፣ የዓለም ባንክ (World Bank) እና ምዕራባዊያን ሀገራት ለሚያስቀምጧቸው መስፈርቶች ተገዢ መሆን የማይሹ፣ እንዲሁም በውስጥ ጉዳዮቻቸው ጣልቃ-ገብነት አጥብቀው የሚቃወሙ ጨቋኝና አምባገነን መንግስታት ያሏቸው ነገር ግን ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ያላቸው ደሃ ሀገራት በቀላሉ በቻይና ተፅዕኖ ስር ይወድቃሉ። በዚህ መልኩ በቻይና ተፅዕኖ ስር እየወደቁ ያሉት ሀገራት አሜሪካ በዓለም-አቀፉ የፀረ-ሽብር ዘመቻ የምታተራምሳቸው የምስራቅና ሰሜን አፍሪካ፣ ምዕራብና ደቡባዊ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የደቡብ ምስራቅ ኢሲያ ሀገራት ናቸው።

ቻይና እነዚህን ሀገራት በተፅዕኖዋ ስር ለማድረግ የተነሳቸው “One Belt, One Road” በሚል በጥንታዊ ቻይና ስልጣኔ የነበረውን ዓለም-አቀፍ የንግድ መስመር መልሶ በመዘርጋት ነው። ይህ የንግድ መስመር “የሀር መንገድ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከቻይናዋ ዚያን (Xi’an) ከተማ ተነስቶ በካዛኪስታን፣ ኢራንና ቱርክ አድርጎ ሩሲያ ሞስኮ ከደረሰ በኋላ በጀርመንና ቤልጂዬም በኩል አድርጎ የኢጣሊያን ቬኒስ ከተማ ይደርሳል። ይህ የየብስ (መሬት) መንገድ የሚገነባው “Silk Road Economic Belt” በሚባል የግንባታ ፕሮጀክት ነው። ከኢጣሊያኗ ቬኒስ ከተማ ጀምሮ ደግሞ በግሪክ፣ ግብፅ፣ ጅቡቲና ኬኒያ አድርጎ ወደ ኢሲያ በመሻገር በሲሪላንካ፣ ህንድ፣ ማሌዢያና ቬትናም በኩል አድርጎ የቻይናዋ “Guangzhou” ከተማ ይደርሳል። ይህን የባህር ላይ የንግድ መስመር እውን ለማድረግ ደግሞ “Maritime Silk Road Initiative” የተባለ ፕሮጀክት ተግባራዊ ተደርጓል። ከታች ያለው ምስል ቻይና “One Belt, One Road” በሚል የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ወታደራዊ ተፅዕኖ ለማሳረፍ የምትንቀሳቀስበትን የዓለም ክፍል ያሳያል።

ከላይ በተጠቀሱት የየብስና የባህር ላይ የንግድ መስመር 68 ሀገራትን ያካትታል። ከእነዚህ ሀገራት ውስጥ 14 ሀገራት በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ኢሲያ፣ 13 ሀገራት በመካከለኛውና ደቡብ ኢሲያ፣ 24 ሀገራት በአውሮፓና ዩሮኢዥያ፣ እንዲሁም 17 ሀገራት ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው። በመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ከሚገኙት 17 ሀገራት የሚከተሉት ናቸው። እነሱም፡- ባህሬን፣ ጅቡቲ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ እስራኤል፣ ዮርዳኖስ፣ ኬኒያ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ሶሪያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜረት እና የመን ናቸው።

3. የቻይና የዕዳ ጫና

በቻይና የሀር ንግድ መስመር ላይ ያሉት 68 ሀገራት አመታዊ የምርት መጠን (GDP) በድምሩ $25 ትሪሊዮን ዶላር ነው። ነገር ግን፣ ከ25 ትሪሊዮን ዶላር ውስጥ 45%ቱ የቻይና ድርሻ አመታዊ የምርት መጠን ነው። ስለዚህ የተቀሩት ሀገራት በቻይና የሀር ቀበቶ (Silk Belt) ተጠፍንገው የሚታሰሩ ናቸው። አብዛኞቹ ሀገራት ቻይና በምትሰጠው ብድር የዕዳ ጫና አለባቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 23 ሀገራት በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በክፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ካሉት ሀገራት፤ 3 ሀገራት በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ኢሲያ፣ 7 ሀገራት በመካከለኛውና ደቡብ ኢሲያ፣ 6 ሀገራት በአውሮፓና ዩሮኢዥያ፣ እንዲሁም 7 ሀገራት ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው።

“Center for Global Development” የተባለ ድርጅት በሰራው ጥናት ከላይ የተጠቀሱት 23 ሀገራት የቻይና የሀር መስመርን ለመዘርጋት ከመደበው ገንዘብ ተጨማሪ ብድር የሚወስዱ ከሆነ የዕዳ ጫናው ሉዓላዊነታቸውን ሊያሳጣ የሚቻል አደጋ ያስከትላል። ቻይና ብድር ምክንያት ሉዓላዊነታቸው አደጋ ላይ የወደቀ የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፡- ጅቡቲ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ ኬኒያ እና ሊባኖስ ናቸው። ከላይ የተጠቀሰው ተቋም ባደረገው ጥናት መሰረት ከላይ ከተጠቀሱት ሀገራት መካከል ከቻይና በተጣለባት የዕዳ ጫና ምክንያት በሉዓላዊነቷ ላይ ከፍተኛ ስጋትና አደጋ የተጋረጠባት ሀገር ጅቡቲ ናት። ከጅቡቲ በመቀጠል ኢትዮጵያ፣ ኬኒያና ግብፅ ከቻይና በተሰጠ ብድር ምክንያት በተፈጠረ የዕዳ ጫና ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ስለዚህ የቻይና መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመግፈፍ ያቆበቆበ የዕዳ ጅብ ነው።

በዓለም ልዕለ-ሃያል ለመሆን በአሜሪካ እና ቻይና መካከል የሚደረገው ትንቅንቅ የጀመረው ጅቡቲ ላይ ነው። ጅቡቲ በአሜሪካና ቻይና መካከል ስትራቴጂካዊ ውጊያ የሚካሄድባት የጦር አውድማ ናት። ሁለቱ የዓለም ሃያላን መንግስታት ፍልሚያ የገጠሙት በኢትዮጵያ አፍንጫ ላይ ነው። ሁለቱ ሀገራት ግብግብ ሲገጥሙ ኢትዮጵያ ያስነጥሳታል። ምክንያቱም ጅቡቲ ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በወታደራዊ የጦር ሰፈር ጭምር የተደገፈ ነው። ከጎን በምስሉ ላይ እንደሚታየው ጅቡቲን በምታክል ትንሽ ሀገር ላይ ከፈረንሳይና ቻፓን በተጨማሪ የአሜሪካና ቻይና የጦር ሰፈር ማዶ-ለማዶ ተገንብቷል። በሁለቱ ሃያላን መንግስት መካከል የሚደረገው ፍጥጫ በኢትዮጵያ፣ አፍሪካ፣ ብሎም የዓለም ፖለቲካ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል የሚለውን በቀጣይ ክፍል እንመለከታለን።

ማጣቀሻዎች(በከፊል)

  • Examining Debt Implications Belt and Road Initiative Policy Perspective
  • China Opens First Overseas Military Base
  • Chinese investment aid to Sri Lanka has been a major success—for China — Quartz
  • More neighbors are saying _no thanks_ to Chinese money — Quartz

(ምንጭ፤ Ethiopian Think Thank Group by Seyoum Teshome; (የመግቢው ፎቶ ከኢንተርኔት የተወሰደ ነው፤ ሌሎቹ በጸሃፊው የተመረጡ ናቸው)

Filed Under: Politics Tagged With: africa, china, Djibouti, Ethiopia, Full Width Top, Middle Column, usa

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule