መቀሌ ላይ ሲሰዳደቡ የቆዩት የበረሃ ወንበዴዎች ደብረጽዮንን መሪያቸው አድርገው በመምረጥ የፈትለወርቅን ዋና መሪነት ውድቅ አድርገዋል። ይህ ለስብሃት ነጋ ሽንፈት የሆነው ክስተት በአዜብ ላይ የተጣለው ዕገዳ እንዲነሳ ወደመቀበል ሊገደድ ይችላል እየተባለ ነው። የኤፈርት ጉዳይ አሁንም አከራካሪ ሆኗል። ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀሌ ላይ ሲወነጃጀሉና ሲሰዳደቡ የቆዩት የህወሓት የበረሃና የድህረ በረሃ ወንበዴዎች በመጨረሻ ላይ የስለላውን ማሽን ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ዋና መሪያቸው አድርገው መርጠዋል። “ሞንጆሪኖ” በማለት ሳሞራ ዩኑስ ጣሊያናዊ ስም የሰጣት ፈትለወርቅ በነስብሃት ቡድን የዋናውን ቦታ እንድትይዝ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግላትም “የመለስ ራዕይ” አስጠባቂ የሆነው ቡድን አልረታም በማለት ውድቅ አድርጓታል። በውጤቱም በዓለምአቀፍ የመረጃ ቋት በአሸባሪነት የተመዘገበው የህወሓት ቡድን … [Read more...] about ፈትለወርቅን ማንገስ ያቃተው የስብሃት ቡድን የአዜብ ዕገዳ እንዲነሳ ሊቀበል ነው
Archives for November 2017
አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች
የጉዞ ዕገዳ እንደ ተጣለባት ይነገራል ከሰሞኑ የህወሓት የሥልጣን ሽኩቻ ጋር በተያያዘ የነደብረጽዮን ቡድን አዜብ መስፍንን ከማንኛውም የፓርቲ ሥልጣን ካገዳት በኋላ በቁም እስር ላይ እንደምትገኝ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። የጉዞ ዕገዳም ተጥሎባታል። ከህወሓት በተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደሚቻለው የአዜብ ጉዳይ በዕገዳ ቆይቶ በቀጣይ የሚታይ ቢሆንም ዕገዳው በራሱ የቁም እስር እንደሆነ መረጃው ይጠቁማል። አዜብ የኤፈርት ዋና ኃላፊ እንደመሆኗ በቀጣይ ከዚያ ሥልጣኗ ጋር በተያያዘ ውሳኔ ቢሰጥ የሚያመጣው ተቀጣጣይ ውጤት እየታሰበበት ያለ ጉዳይ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያስረዳል። ከዚህ የቁም እስር ጋር በተያያዘ አዜብ የጉዞ ዕገዳ እንደተጣለባት ተጠቁሟል። መለስ የሞተ ጊዜ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ዋና “ወንበዴ” የሆነው ስብሃት ነጋ “የግለሰብ ሌጋሲ የሚባል የለም፤ ሌጋሲ … [Read more...] about አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች
“ሃፍታም ምሆነው ሕወሃት ሲለቅቀኝ ነው!” አዜብ መስፍን
የህወሃት ሽኩቻ አላባራም! "ሃፍታም የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቀኝ ብቻ ነው!" ብላ ከነገረችን ገና መንፈቅ እንኳ አልሞላም። ከጥልቅ ተሃድሶ እና ከመተካካት ቀጥሎ የተመሰከረለት የአዜብ ጎላ መሪ ቃል ነበረች። የመልቀቁን ጨዋታ ለኛ ተየት አድርጊያትና መሪርዋን ጽዋ ተጎንጪ ሲሉ እነሆ መርዶውን ነግረዋታል። ሂስዋን አልውጥም ብላ ከመቀሌ እንደፈረጠጠች በዚያው ቀርታለች። መቼም "መለስ የሞተው አሁን ነው!" ሳትል አትቀርም በልብዋ። የዛሚዋ ደላሊት እድል አትሰጣትም እንጂ፣ ይህንኑ የልብዋን ሃሳብ "ለሚወዳት ሕዝብ" ትተነፍሰው ነበር። ግን ምን ያደርጋል? የወደቀ ፈላጊ አይኖረውም። ቀልደኛይቱ የጎላ ልጅ፣ "ድሮስ ቢሆን ድሃን ማን ይወደዋል" ማለትዋ በፌዝ ቡክ ላይ አነበብን። አዎ! አዜብ መስፍን ከታሰረችበት የህወሃት ጎራ አሁን ተለቅቃለች። ቃል እንደገባችውም የድህነትን … [Read more...] about “ሃፍታም ምሆነው ሕወሃት ሲለቅቀኝ ነው!” አዜብ መስፍን
የመለስ “ሌጋሲ” በአዜብ መታገድ መቃብር ገባ
ህወሓትን ለመምራት ደብረጽዮን፣ ዓለም፣ ጌታቸውና ፈትለወርቅ ታጭተዋል እርስበርሱ ሲነታረክ የቆየው የህወሓት ግምገማ አባይ ወልዱን በማባረርና አዜብ መስፍንን በማገድ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። እነደብረጽዮን የሚመሩት የማጽዳት ዘመቻ በመለስ “ሌጋሲ” ላይ አብሮ እርምጃ ወስዷል። የመሪነቱን ቦታ ፈትለወርቅ፣ ደብረጽዮን፣ ጌታቸውና ዓለም እየተፎካከሩበት ነው ተብሏል። አፍቃሪ ህወሓትና የህወሓት ልሳን ከሆኑ የዜና ምንጮች በቀረበው መረጃ መሠረት ሰሞኑን በግምገማ እርስበርሱ ሊበላላ ደርሶ የነበረው የህወሓት ግምገማ “ቆራጥ” እርምጃዎችን ወስዷል። በዚህም መሠረት በመለስ ዜናዊ ምትክ የ“ወንበዴ” ድርጅቱ ኃላፊ ሆኖ ሲሠራ የነበረው አባይ ወልዱ ከሊቀመንበርና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊነቶች ተወግዶ በተራ አባልነት እንዲቀጥል ተወስኖበታል። ከአባይ መሰናበት በተጨማሪ “አዜብን መንካት የመለስ … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” በአዜብ መታገድ መቃብር ገባ
እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
ንጉሥ ሳልማን በቅርቡ ከሥልጣናቸው ወርደው በአልጋ ወራሹ ይተካሉ እስራኤል ከሳዑዲ ጋር የመረጃ (የስለላ) ልውውጥ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች በሙስና እና የመንግሥትን ሃብት አለአግባብ በመጠቀም በሚል በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የሳውዲ ልዑላንና ሌሎች ታላላቅ ባለሥልጣናት ከእስር ለመውጣት እስከ 70 በመቶ ሃብታቸውን ለመንግሥት ለማስረከብ እየተደራደሩ መሆናቸው ተሰማ። አል-አሙዲ በ30 በመቶ መቀጠል አሳሳቢ ሆኗል። ንጉሥ ሳልማን ሥልጣናቸውን ለአልጋ ወራሻቸው ሊያስረክቡ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሳዑዲ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት የጀመረችው እስራኤል ከሳዑዲ ጋር በሚፈለገው መልኩ ለመተባበር ፈቃደኝነቷን አስታወቀች። በኢትዮጵያ ላለፉት 26ዓመታት ከግብር ነጻ ንግድ በማካሄድ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የነበረው የህወሓት የቅርብ ወዳጅ አል-አሙዲ በሳዑዲ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ጊዜ ጀምሮ … [Read more...] about እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው
“9ኙ የእግር ጣት ጥፍሮቼ በጉጠት ተነቅለው” ንቃዩን ይዤ እንዳልቀርብ ተጥለውብኛል – ንግሥት ይርጋ
ንግስት ይርጋ አቃቤ ህግ ባቀረበባት የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረበችው መቃወሚያ ላይ የተወሰደ (በጌታቸው ሺፈራው) በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበበት የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረበው መቃወሚያ ላይ የተወሰደ↓(በጌታቸው ሺፈራው) በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ 2ኛ ተከሳሽ እና የጎንደር ዙሪያ የመኢአድ ሰብሳቢ የነበሩት ዓለምነህ ዋሴ ካቀረቡት የሰነድ መቃወሚያ ላይ የተወሰደ ↓↓(በጌታቸው ሺፈራው) የወልቃይት ሕዝብ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት መብራቱ ጌታሁን፣ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌ፣ አለነ ሻማ እና ነጋ ባንተይሁን ለተመሰረተባቸው ክስ ካቀረቡት የክስ መቃወሚያ የተወሰደ ↓↓(በጌታቸው ሺፈራው) (ምንጭ: Addis Gazetta) … [Read more...] about “9ኙ የእግር ጣት ጥፍሮቼ በጉጠት ተነቅለው” ንቃዩን ይዤ እንዳልቀርብ ተጥለውብኛል – ንግሥት ይርጋ
ህወሓት በሚገዛት ኢትዮጵያ ብቻ!
ደብዳቤ አርቃቂ - ዶ/ር አብዱል ቃድር ሁሴን ፈራሚ - ዶ/ር አብዱል ቃድር ሁሴን ሿሚ - ዶ/ር አብዱል ቃድር ሁሴን ተሿሚ - ዶ/ር አብዱል ቃድር ሁሴን (ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) (ምንጭ: @addisgazetta) … [Read more...] about ህወሓት በሚገዛት ኢትዮጵያ ብቻ!
“ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ”
የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፣ ሁለተኛውን ዓለማቀፍ ኮንፈረንስ December 2, 2017 በብሪስልስ ከተማ ያዘጋጀ መሆኑንበደስታ ይገልጻል። ዘንድሮም “ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የአንድ ቀን ሴሚናር ላይ አራት ታውቂ ባለሙያዎች ጥናታዊ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡጋብዟል። የኮንፈረንሱን ዝርዝር መረጃ የያዘውን ፖስተር እዚህ ላይ በመጫን ያገኙታል። ዕርስዎም የዝግጅታችንን መርሀ ግብር ላይ እንዲገኙልን እና ጥሪያችንንም ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዲያስተላልፉልን በትህትና እንጠይቃለን። ከማክበር ሰላምታ ጋር ኮሚቴው “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ”
“አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌ አልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን ለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል። በግል ጸብ ለሁለት መሰንጠቃቸው የአደባባይ ምስጢር ይሁን እንጂ፤ እርቅ እና ሰላም በአጀንዳቸው ውስጥ አልተካተተም። ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ወደጎን ትተው፣ “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” ሲባባሉ እንደከረሙ ነው እየተሰማ ያለው። ይህንን የማይታረቅ ቅራኔ ይዘው አብረው ስለማይዘልቁ የአንዱ ቡድን ማሸነፍ ግድ ይላል። በዚህ ‘ታሪካዊ’ ስብሰባ የሙስና እና የሌብነት ፋይሎች ተጠርዘው ቀርበዋል። ህወሃቶች አፍ አውጥተው “በስብሰናል”ም ብለዋል። … [Read more...] about “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
ፎቶና ታሪኩ
በወያኔ ዘመን በህወሃት ቀንበር ያሳለፍነው ህይወት የጠጣነው አረር እንዴት እንደሆነ እንዴት እንደነበር ጠበቃ ከማቆም እማኝ ከመደርደር ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር። *የተከበርክ አንባቢ ሆይ! ቀጣዮቹን ፎቶዎች በፅሞና እና በማስተዋል ተመልከታቸው፤ መልዕክቶቹንም ረጋ ብለህ ወደ ነፍስህም ቀርበህ አንብብ። ምናልባት ለመፍትሄውም ሆነ ለችግሩ አንተ ትቀርብ ይሆናልና። በጎንደር ከተማ የሚታየው ዘግናኝ የቁልቁለት ‘እድገት’። በህወሃት በይፋ ጠላትነት ተፈርጆ የቁም ስቅሉን እያየ በሚገኘው የአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በመካሄድ ላይ ያለው የኢኮኖሚ ተዐቅቦ ያስከተለው መከራና ድህነት እጅግ ዘግናኝ ሲሆን በቅርቡ በወጣ ጥናታዊ ዘገባም የአማራ ህፃናት ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ (በርግጠኝነትም በሌሎች ክልሎች በዚህ ስፋትና መልክ ያልተከሰተ) ያለ ዕድሜያቸው … [Read more...] about ፎቶና ታሪኩ