
- ህወሓትን ለመምራት ደብረጽዮን፣ ዓለም፣ ጌታቸውና ፈትለወርቅ ታጭተዋል
እርስበርሱ ሲነታረክ የቆየው የህወሓት ግምገማ አባይ ወልዱን በማባረርና አዜብ መስፍንን በማገድ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። እነደብረጽዮን የሚመሩት የማጽዳት ዘመቻ በመለስ “ሌጋሲ” ላይ አብሮ እርምጃ ወስዷል። የመሪነቱን ቦታ ፈትለወርቅ፣ ደብረጽዮን፣ ጌታቸውና ዓለም እየተፎካከሩበት ነው ተብሏል።
አፍቃሪ ህወሓትና የህወሓት ልሳን ከሆኑ የዜና ምንጮች በቀረበው መረጃ መሠረት ሰሞኑን በግምገማ እርስበርሱ ሊበላላ ደርሶ የነበረው የህወሓት ግምገማ “ቆራጥ” እርምጃዎችን ወስዷል። በዚህም መሠረት በመለስ ዜናዊ ምትክ የ“ወንበዴ” ድርጅቱ ኃላፊ ሆኖ ሲሠራ የነበረው አባይ ወልዱ ከሊቀመንበርና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊነቶች ተወግዶ በተራ አባልነት እንዲቀጥል ተወስኖበታል።
ከአባይ መሰናበት በተጨማሪ “አዜብን መንካት የመለስ ሌጋሲን አደጋ ላይ መጣል ነው” በሚል እንድምታ በግዱ ለአዜብ ሲያጎነብስ የነበረው ትግራይን ለመገንጠል የተቋቋመው ቡድን አዜብን ከከፍተኛ ኃላፊነቷ አንስቷታል። ከቀናት በፊት አዜብንና ተላላኪዎቿን ለመቀርጠፍ ግምገማው ሲጣደፍ በነበረበት ጊዜ አዜብ መስፍን ስብሰባውን ረግጣ መውጣቷ ይታወቃል። ለዚህ ድርጊቷ በተደጋጋሚ ይቅርታ ብትጠይቅም ሆነ ደብዳቤ ጽፋ ብታስገባም “ኃጢአቷን ካናዘዘ” በኋላ በዕገዳው ጸንቷል።
“ባለራዕዩ መሪ” እየተባለ ሲሞገስና ሲሞካሽ የኖረው መለስ በሙት መንፈስ አገሪቱን ሲመራ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። ሞት እንደ ቡሽ ክዳን በድንገት ቢያስፈነጥረውም ህወሓት በእርሱ መንፈስ እመራለሁ ሲል አዜብም “አንዲት ሓሳብ ይዞ ወደ ምድር” የመጣውን ሙት ባሏን ከለላ በማድረግ ያሻትን ስትናገርና ስትከውን ላለፉት አምስት ዓመታት ቆይታለች።

በህወሓት ነባር ወንበዴዎች ዘንድ በንቀት የምትታየው አዜብ ከመለስ ሞት በኋላ ከማንኛውም ኃላፊነት እንድትወገድ ሲሞከር ቆይቷል። ሆኖም እርሷን በሙስና ወይም በሌላ ሰበብ ማባረር በመለስ ውርስ (ሌጋሲ) ላይ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል በሚል ውሳኔው ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል። በሙስና ከተባረረች የሙስናው እፍታ ለመለስም ደርሷል የሚለው አስተሳሰብ የባለራዕዩን መሪ ስም የሚያጠለሽ ነው የሚል አስተያየት ሲሰጥበት ቆይቷል። በኪራይ ሰብሳቢነት ወይም በችሎታ፣ በአቅም ማነስ ወይም በአስተሳሰብ ደካማነት ወይም በሥልጣን መባለግ በሚሉ ሰበቦች ብትባረር ያለ ችሎታዋና ያለ አቅሟ ወደ ሥልጣን እንድትመጣ ያደረገውን መለስ አሁንም የሚያዋርድ ነው በሚል ጥርስ ሲነከስባት ሰንብቷል።
በህወሓት ጉዳይ ውስጥ አዋቂ ነን የሚሉ እንደሚናገሩት አዜብ መታገድ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከድርጅቱ ትባረራለች የሚል አስተያየት እየሰጡ ናቸው። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ከእርሷ ጋር አብሮ የመለስ ሌጋሲ በዜሮ እንዳባዛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ያሳስባሉ። በመሆኑም እስካሁን የአዜብን ጉዳይ በትዕግስት ሲያስታምም የቆየው ህወሓት አዜብ የምትባረረው ከመለስ ሞት በኋላ በፈጸመችው ስህተት መሆኑን በማጉላት የመለስን “ሌጋሲ” ለማዳን የፕሮፓጋንዳ ሥራ የመሥራት ዕቅድ ያስፈልጋል የሚሉ ወያኔዎች የሚሰጡት አስተያየት አብላጫነት እያገኘ መጥቷል።
አዜብን በማገድ፣ በየነ ምክሩንና አባይ ወልዱን በማባረር የቀጠለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ግምገማ በተባረሩት ምትክ አዳዲስ አባላትን ያስገባል። በዓለምአቀፋዊ የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ለተመዘገበው ድርጅት – ህወሓት – መሪ ይመርጣል። ሁለቱ የደኅንነትና የስለላ ማሽኖች ደብረጽዮን ገብረሚካኤልና ጌታቸው አሰፋ እንዲሁም ዓለም ገብረዋህድ ለመሪነት ቀዳሚ ተፎካካሪዎች እንደሆኑ የህወሓት ተላላኪዎች ቢናገሩም በበረሃ ስሟ “ሞንጆርኖ” እየተባለች የምትጠራው ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ቀጣይዋ የህወሓት መሪ እንደምትሆን ስዩም ተሾመ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል በማለት በፌስቡክ ገጹ ላይ ዘግቧል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
ውድ ጎልጉል፣
የሚያሳዝነው፣ ህወሓት በአገራችን ዕጣ ብቸኛ ወሳኝ ሆኖ የሚያካሄደውን ስብሰባ ሌላው እንደ ተመጽዋች እጁን አጣምሮ መጠባበቁ ነው። ዛሬ ደግሞ አፍቃሬ ወያኔው ሪፖርተር፣ ምሑራን ወደ ኤርትራ ሄደው ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲያደርጉ ህወሓት መፍቀዱን ገልጿል። ምሑራኑን የሚመሩት ሀብቶም እና መድሐኔ ናቸው። ትልቅ ቀልድ፣ የሰው ልክ የማያውቅ መንግሥት ገጥሞናል። የሥልጣን ጥመኛውና ሥራፈቱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ደግሞ የኢትዮጵያ ደመኛ ኢሳይያስ የሥልጣን ኮርቻ ላይ ያፈናጥጠኛል ብሎ ተስፋ አድርጓል። ከሌንጮ ለታ፣ ከታምራት ላይኔ እንኳ መማር አልቻለም። ዶ/ር ብርሃኑ በ97 ምርጫ ህዝብ ተገልብጦ ወጥቶ እርሱ ግን ፈርጥጦ ከአገር ወጣ። ህወሓት ወዲያው የተበተነውን ወጣት ለቃቅሞ ኪሱ ከተተ። ከዚያን ወዲህ “ተቃዋሚ” ገለመሌ የሚለው ቋንቋ ወጣቱን ቋቅ ብሎታል። የህወሓት ጥንካሬ የኛ ዝርክርክነትና ዓለማ ቢስነት ግልባጭ ነው። ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ የድረገጾች የውሸት ናዳና ተስፋ ነው። ህወሓት ሊወድቅ ነው! ምሥጢሩን ይዘናል! የውሸት ተስፈኞች አድርጎናል። ስንት ዓመት ይህን ስንሰማ ኖርን፤ አንዱም እውን አልሆነም። እናንተ ግን ጎልጉላችሁ እውነቱን ከመናገር ችላ አትበሉ።
ሰላም Alem
ለላኩልን መልዕክት እናመሰግናለን።
በተለይ “… ዛሬ ደግሞ አፍቃሬ ወያኔው ሪፖርተር፣ ምሑራን ወደ ኤርትራ ሄደው ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲያደርጉ ህወሓት መፍቀዱን ገልጿል። ምሑራኑን የሚመሩት ሀብቶም እና መድሐኔ ናቸው …” ባሉት ጉዳይ ላይ እየሠራንበት ነው በቀጣይ የምናቀርበው የዜና ዘገባ ይሆናል።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የጎልጉል አርታኢ
አይ ዓዜብ!ዓዜብ!የመለስ ሚስት! ዓዜብ!
ልክሰስሽ!? አሁን!?ሰው እስኪታዘብ?
ላዋርድሽ!? ቂሊንጦ ላስገባሽ?ላስጠብቅሽ በዘብ?
አየሽ! ዓዜብ!ዓዜብ!
ላሸክምሽ! የውርደትሽን ቀለብ?
ባልሽና አንቺ ከጠላት ወግኖ መረባረብ?
እሱ ሲሞት አንቺ በማደብ!
በመደበቅ! ዱካ አጥፍቶ መረባረብ?
ልክተትሽ?ከሴ?ዓዜብ?
ነውር ነው!! በስርቆት ተለክፈሽ!
ይባስ ብለሽ አይናውጣ ሆነሽ!እኔን ልታጠፊ ሞክረሽ!
ልክተትሽ? በተራ ስርቆት ላስገባሽ?
ውነት ቅን ነበር ባልሽ?
እኛን ጨፍልቆ አንቺን ሲያሻሽ!
በስርቆት ወንጀል ላስገባሽ?
እስቲ ማን ዋቢ ይሁንሽ?
ቢቀር ቢቀር ስድስት ወር ታጪያለሽ?
ነውር ነው! ነውር ነው! ያንቺና የባልሽ!
መልስ ስጪኝና ላሳይሽ!
ተቀመጪ ቅሌት ተከናንበሽ!
ዓዜብ! ዓዜብ!አበቃልሽ!የተራ እንኳን አባልነትሽ!
ዕድሜ ለሃይለ ማርያም ብለሽ!
ተቀመጪ ከእንግዲህ በቃሽ!!
ከእንግዲህ ስልጣን አይመርሽ!!
የቀን ገቢው ሚሊዮን፣
የወር ገቢው ቢሊዮን፣
ከጫካ ሲመጣ ያልነበረው ስሙኒ፣
ዛሬ ባለ ካምፓኒ፣
ሎተሪ ያልወጣለት ውርስ የሌለው፣
ይህን ሰው ማን ዕንበለው?