• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ

November 16, 2017 11:30 pm by Editor Leave a Comment

መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌ አልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን ለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል።

በግል ጸብ ለሁለት መሰንጠቃቸው የአደባባይ ምስጢር ይሁን እንጂ፤ እርቅ እና ሰላም በአጀንዳቸው ውስጥ አልተካተተም። ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ወደጎን ትተው፣ “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” ሲባባሉ እንደከረሙ ነው እየተሰማ ያለው። ይህንን የማይታረቅ ቅራኔ ይዘው አብረው ስለማይዘልቁ የአንዱ ቡድን ማሸነፍ ግድ ይላል።

በዚህ ‘ታሪካዊ’ ስብሰባ የሙስና እና የሌብነት ፋይሎች ተጠርዘው ቀርበዋል። ህወሃቶች አፍ አውጥተው “በስብሰናል”ም ብለዋል። እንደ አጀንዳ በቀረቡ በነዚህ የክስ ፋይሎች ላይ ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል።

ስብሰባውን እየረገጡ የወጡት ወንጀል ሲዶለትባቸው የነበሩትና “ተሸናፊ” ህወሃቶች ናቸው። በሃብታቸው ብዛት “ቀዳማዊት እመቤት” የተባሉት አዜብ መስፍን የመጀመሪያው ስብሰባ ረጋጭ መሆናቸውን ሆርን አፌይርስ ከውስጥ ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል።

አዜብ ተከትለው ስብሰባውን እየረገጡ የወጡት የነ ስዬ አብርሃን ጽዋ ይቅመሱ አይቅመሱ ገና ባይታወቅም፣ ዛቻውና ጥርስ መናከሱ መቀጠሉን ግን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል።

ወሩን ሙሉ መቀሌ ላይ ከትመው ሲጠዛጠዙ ውለው ሲጠዛጠዙ መሰንበታቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል። ግምገማው ቀድሞ እንደሚያደርጉት አንዱ ባንዱ ላይ ጣት መሰባበቅን አልፎ፣ በተራ ስድብ እና ዘለፋ የታጀበ ነው። አጀንዳቸው ብሄራዊ ጉዳይ ቢሆን ባልከፋ ነበር። እጅግ የሚያሳፍረው ጸቡ እኔ እበልጥ፣ የግል መሆኑ ነው። ሌቦች የሚጋጩት ሲሰርቁ ሳይሆን ሲካፈሉ ነው ይባል የለ።

አቶ ሀብቶም ገ/እግዚያብሄር የህወሃቱ ድረገጽ በሆነው አይጋ ፎረም ላይ ኢህአዴግ ያለበት መንታ መንገድ እና የሀገራችን እጣ ፈንታ! በሚል የለቀቁት ያልተለመደ ጽሁፍ ከወዲያ እየነደደ ያለውን እሳት ይጠቁመናል። አይቴ ሃብቶም ስለዛሬው መግማማትና የሌቦች ፖለቲካን ክፉኛ ይኮንናሉ። ዛሬ ብቸኛው የመክበሪያ መንገድ ወይ የመንግስት ስልጣን መያዝ ወይ ከመንግስት ባለስልጣን መጠጋት እሳቤ መሆኑን እና ለዚህም ሙሉ ተጠያቂው ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ነው ይላሉ።

እርግጥ ነው። በህወሃት ውስጥ ሽኩቻ እና መጠላለፍ አዲስ አይደለም። የከዚህ ቀደሙን ተመክሮ እንዳየነውም፤ ስብሰባ ረግጦ መውጣት ለችግሮቹ መፍትሄ አልሆነም። ከ16 አመት በፊት እነ አቶ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ስዬ አብርሃ፣ ፃድቃን ገ/ተንሳኤ የመለስን ሰነድ አንቀበልም ብለው ስብሰባ ረግጠው ነበር። እነ ስዬ በወቅቱ አብዛኛ ድምጽ ነበራቸው። ግና ማኬቬሊያዊው መለስ ቀደማቸውና እንደወጡ በዚያው ቀሩ።

አሁን መለስ የለም። ጸቡም የውስጥና የርስበርስ ብቻ አይደለም። ሽኩቻው ከሕዝብ ጋርም ነው። ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር። የከረረው ክፍፍል ከህዝብ እንቢተኝነት ጋር ተደምማሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ታምራት ገለታን መጠየቅ አያስፈልግም።

ፋይዳ ላይኖረው፣ እንዲሁ ሲቀያየሩ መሰንበታቸው “ስልቻ ቀልቀሎ…” ይሁን እንጂ፣ የኑሮው ውድነት፣ ከጣና ኬኛ ፖለቲካ እና የሼኩ ያልጠጠበቀ መታሰር፣… ተደማምሮ ለውጥ ፈልጎ ለተነሳው ኃይል በር መክፈቱ ግልጽ ነው። (ፎቶው ከHorn Affairs የተወሰደ ነው – አባይ ወልዱና ደብረጽዮን የመቀሌውን የህወሃት ስብሰባ ሲመሩ)

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule