• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እነ አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብታቸውን በማስረከብ ለመፈታት እየተደራደሩ ነው

November 17, 2017 11:04 pm by Editor 3 Comments

  • ንጉሥ ሳልማን በቅርቡ ከሥልጣናቸው ወርደው በአልጋ ወራሹ ይተካሉ
  • እስራኤል ከሳዑዲ ጋር የመረጃ (የስለላ) ልውውጥ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች

በሙስና እና የመንግሥትን ሃብት አለአግባብ በመጠቀም በሚል በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የሳውዲ ልዑላንና ሌሎች ታላላቅ ባለሥልጣናት ከእስር ለመውጣት እስከ 70 በመቶ ሃብታቸውን ለመንግሥት ለማስረከብ እየተደራደሩ መሆናቸው ተሰማ። አል-አሙዲ በ30 በመቶ መቀጠል አሳሳቢ ሆኗል። ንጉሥ ሳልማን ሥልጣናቸውን ለአልጋ ወራሻቸው ሊያስረክቡ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሳዑዲ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት የጀመረችው እስራኤል ከሳዑዲ ጋር በሚፈለገው መልኩ ለመተባበር ፈቃደኝነቷን አስታወቀች።

በኢትዮጵያ ላለፉት 26ዓመታት ከግብር ነጻ ንግድ በማካሄድ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የነበረው የህወሓት የቅርብ ወዳጅ አል-አሙዲ በሳዑዲ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ጊዜ ጀምሮ ደጋፊዎቹ ብዙ ሲዘግቡለት ቆይተዋል። ከአልታሰረም እስከ ተፈትቷል ሲባልለት የነበረው አል-አሙዲ አሁንም በእስር ላይ ይገኛል። የዜጎቹ ጉዳይ ከምንም የማያሳስበው ህወሓት/ኢህአዴግ በተወካዩ ኃይለማርያም አማካኝነት “መንግሥት የሚቻለውን እያደረገ ይገኛል” በማለት ለአንድ ግለሰብ ያለውን ተቆርቋሪነት ይፋ አድርጓል።

የሳዑዲ ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳውድ በቅርቡ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ከማቀዳቸው ጋር በተያያዘ የአልጋ ወራሻቸውን መቀመጫ ለማደላደል እና በሌሎች የፖለቲካ ምክንያቶች በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሳዑዲ ልዑላንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ክብራቸውን ከሚነካ የመኝታ ሁኔታ እስከ ስቅየት (ቶርቸር) ደርሶባቸዋል እየተባሉ የሚነገርባቸው ታሳሪዎች ንብረታቸው መንግሥት እንዲቆጣጠረው እንደሚደረግ ባለፈው ሳምንት የሳዑዲው አቃቤ ሕግ መናገራቸው ታወሳል።

ዛሬ (አርብ) ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተሰማው ዜና እንደሚያመለክተው አልጋወራሹ ሞሐመድ ቢን ሳልማን ሁኔታውን ለማረጋጋትና መስመር ለማስያዝ አቅጣጫዎችን እየቀየሩ መሆናቸው ተሰምቷል። ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው ከሆነ ታሳሪዎቹ እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ሃብታቸውን አሳልፈው በመስጠት ከእስር ለመፈታት እየተደራደሩ መሆናቸውን አስታውቋል። ዜናውን ሌሎች የዜና አውታሮች ለማረጋገጥ አልቻልንም ማለታቸው ተሰምቷል።

በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ተግባር በድንገት በተጀመረ ጊዜ ከተያዙት በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ባለሃብቶችና ንጉሣዊ ቤተሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። እንደተባለው እስከ 70 በመቶ በሚሆነው ሃብታቸው ከእስር ለመፈታት የሚደራደሩ ከሆነ የሳዑዲ መንግሥት በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እያሽቆለቆለ ወደሄደው ካዝናው ማስገባት ይችላል ተብሏል። ድርድሩንም ወደዚህ አቅጣጫ እንዲሄድ ያደረገው ግለሰቦቹን ለመፍታት ከማሰብ ሳይሆን ሃብታቸውን ከመውረስ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ያስረዳሉ።

አል አሙዲ ከኃይለማርያም ጋር በወልዲያ ስታዲየም (ፎቶ Addis Fortune)

በአድናቂዎቹና ከእጁ በበሉ “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ” እየተባለ የሚሞካሸው አል-አሙዲ 70በመቶ ሃብቱን አስረክቦ ከወጣ “ድርጅቶቼ” በሚላቸው ኩባንዎች ላይ ሊደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ካሁኑ አሳሳቢ ሆኗል። ለአልባሌ ጉዳዮች ከሚያባክነው ገንዘብ እና በሥሩ ከተሰገሰጉት ሞሳኞች ተርፎት በ30በመቶ ለመቀጠል የመቻሉና ኩባንያዎቹንም በዚህ የማስቀጠሉ ጉዳይ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ማስፈኑን ለጎልጉል አስተያየታቸውን ከአዲስ አበባ የላኩ ገልጸዋል። ከዚህ ሌላ ከሙስና ጋር በተያያዘ ታስሮ መፈታት በራሱ የሚፈጥረው ኃፍረትና ቅስም መሰበር ከሰውየው የጤና ችግሮች ጋር ተዳምረው ሁኔታዉን የከፋ ደረጃ እንዳያደርሱት ስጋት አለ።

የአል-አሙዲን “የጽድቅ ተግባራት” ዘርዝረው ለመናገር ቃላት የሚያጥራቸው ግለሰቡ የህወሓት አንጋሽና የዘረፋ ሃብት ተካፋይ ከመሆን አልፎ በጋምቤላ 424 ወገኖች በግፍ ከተጨፈጨፉ በኋላ መሬታቸው በሳንቲም ሲቸበቸብ መሬቱን ከተቀራመቱት ዋንኛ ድርጅቶች መካከል አብዛኛውን የወሰዱት የሕንዱ ካሩቱሪና የአል-አሙዲ ሳዑዲ ስታር መሆናቸውን መዘንጋታቸው ብቻ የአል-አሙዲ ደጋፊዎች ጭንቅላት “በስብ ለመደፈን” በአስረጅነት የሚቀርብ ነው በማለት ተቃዋሚዎቻቸው ይሞግታሉ። በአገር ውስጥ ያሉት የግለሰቡ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ በዳያስፖራም የህወሓት ቀንደኛ ነቃፊ የሆኑ “ከእጃቸው የበላን” የሚሉ ለአል-አሙዲ ጭፍን ድጋፍ የመስጠታቸውን ጉዳይ የህወሓትን አገዛዝ ጋር በተመለከተ የፖለቲካችንን ጭፍን ወገናዊነትን የሚያሳብቅ ነው ይላሉ።

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚ/ር ሌ/ጄ ጋዲ ኢዘንኮት (ፎቶ IDF Spokesperson)

ከእስራኤል ጋር የቅርብ ግንኙነት እየመሠረተች ያለችው ሳዑዲ አረቢያ እየወሰደች ላለችው እርምጃ የእስራኤል ሙሉ ድጋፍ አላት የሚሉ መረጃዎች በብዛት ይሰማሉ። የእስራኤሉ ጠ/ሚ/ር ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከተናገሩት በተጨማሪ አልጋወራሹ ልዑል ሳልማን በቅርቡ በምስጢር የእስራኤል የመከላከያ ሚ/ር የሚገኝበትን የቴልአቪቭ ከተማ ጎብኝተዋል እስከሚለው ድረስ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ትኩረትን የሳበ ሆኗል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚ/ር ሌ/ጄ ጋዲ ኢዘንኮት፤ ኤልፋ ከተባለ የሳዑዲ የድረገጽ ጋዜጣ ጋር “ታሪካዊ” የሚባል ቃለምልልስ ማድረጋቸው ሁኔታውን በታሳሪዎቹ ጉዳይ የእስራኤል እጅ እስከምን ድረስ ነው የሚለውን ጥያቄ አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎታል። በተለይም ሁለቱ አገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሳይኖራቸው አሁን እየተካሄደ ያለው “ትብብር” ከመከላከያ ሚ/ሩ ቃለምልልስ ጋር ተዳምሮ ነው ጉዳዩን “ታሪካዊ” ያስባለው።

የመከላከያ ሚኒስትሩ የኢራንን ጉዳይ አስመልክቶ ከሳዑዲና ከአሜሪካ ጋር ግምባር በመፍጠር አዲስ ዓለምአቀፋዊ የመተባበር ዕድል ተከፍቶልናል ያሉ ሲሆን “አስፈላጊ ከሆነ (ከሳዑዲ አረቢያ) ጋር የመረጃ (የስለላ) ልውውጥ ለማድረግ ተዘጋጅተናል፤ በሁለታችን መካከል በርካታ የጋራ ፍላጎቶች አሉ” ማለታቸው እነ አል-አሙዲ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የሞሳድ ዓይን የት ድረስ ይከተላቸው ይሆን የሚል ጥያቄ በአንዳንዶች ዘንድ አስነስቷል።

ማስታወሻ፤ አላሙዲንን “አንተ” ብለን መጥራታችን ለሚያሳስባችሁ ይህንን እንድታነቡ ይሁን።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    November 18, 2017 10:54 pm at 10:54 pm

    አደራ!! አደራ!! ጎልጉል!
    እስቲ እኛም እናሽሟጥ መሰል
    ጽሁፋችንን አትወርውር!! አትጣል !!
    ብቻ ለታዛቢ ይቅረብ ነው የምንል!!

    ጽሁፉ መላምትን ያዘለ: በይሆናል የተጫረ
    በዘፈቀደ ትንቢት የተጣመረ
    ከውነት የሸሸ በቅጥፈቱ የተባረረ
    ጭራሽ! በጭራሽ የተደናበረ
    በድርዱሩ የቀላወጠ ያልነበረ

    እንጂ ቅጥፈት ያቅራቢው ሆኖ
    ለማስመሰል የቀረበ ተጋኖ
    ጨቅላን ለመሸንገል: ጊዜ አባክኖ
    ሆን ተብሎ! ለመምሰል ተከናውኖ
    የፈጠራ ወሬ ዘልዝሎ ወይ ማስኖ
    ድሮ የቀረ ነው መክኖ!!

    አቀበት ሮጦ የሄደ ተጓዥ
    ሜዳ ወይ ቁልቁለት ቢባዥ
    ታብሌት ያስፈልግ ይሆን አደንዛዥ???
    ወሬ ነው! እንዲው ቦዥ! ቦዥ!!!
    ቅጥፈት ነው! መላ ያጣ ተያዥ!!!!

    Reply
  2. Ezira says

    November 20, 2017 12:10 am at 12:10 am

    ለሌባና አገርን ላራቆተ ማጅራት መች ቡድን ወይ ግለሰብ ከዚህ የተሻለ “አንተን” የሚተካ ቃል ቢገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር። ማጅራት መቺዉን አላሙዲንን በተመለከተ ሪያድ እግዚአብሄር ይስጣትና ቓሊቲ ውስጥ አስግብታ ከርችማልናልችና ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው። ለዚህ ማጅራት መቺ አላሙዲን “አንተም” ሲበዛበት ነው።፡ ከተቻለ ማጅራት መቹ አላሙዲን ቢባል ተግባሩን ቁልጭ አድርጎ ገለጭ የሆነ ቃል ነው ብል ማጋነን አይሆንም። አገራችንን ያራቆተ ወንበዴ አንተ ማለታችንም ምርጫ በማጣታችን የምንጠቀምበት ቃል እንጅ “አንተም” ይበዛበታል – “አንተ” የሚለውን ቃል እኮ ለሌላም የምንጠቀምበት ውድ ቃል መሆኑን ሳንዘነጋ። ለጎልጎሎች እንደ ማሳሰቢያ “አንተን” ምርጫ በማጣጥ የተጠቀምንበት ቃል እንደሆንም አብሮ ቢገለፅ ደህና ነበር ይሄ የግል አስተያየቴ ነው ለጎልጉሎች ። THANKS GOD

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    November 22, 2017 04:50 am at 4:50 am

    እዝራ! እዝራ! እዝራ!
    ውነት በዚህ ይሆን የምትጠራ??
    ማጅራት መቺ ምንድን ነው?
    በዱላ ነው? በጡጫ ነው?
    ለመቀማት ነው?

    እዝራ! ጽሁፍህ ለዛ ኣጣ ምነው??
    መግለጽ ቢያቅትህ ያሰብከው!
    እንዴ! ኣከናነብከኝ ከለዛው!
    ጣመኝ ልበለው!ሰዎች!? ልበለው??
    ስድብ ጎምዛዛ እንጂ መቼም ጣምየለው!
    እዝራ እራቁቴን ኣስቀረኝ ምነው!?
    ማጅራቴን መታኝ ምነው!??
    ኣይጣል ነው! ኧረ ኣይጣል ነው!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule