ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት … [Read more...] about የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ
Archives for August 2017
ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
ለፖለቲከኞች እስር እውቅና የሰጡ “ፓርቲዎች” እየተደራደሩ - ሕዝብ እያመጸ ወዴት? “እንወክለዋለን” በሚሉት ሕዝብ ዘንድ እውቅና ያላቸው ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እጅግ አነስተኛ እንደሆኑ ይነገራል። አብዛኞቹ በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጥቂት” ከተሰኙት ውጪ ስለመኖራቸው እንኳን እንደማይታወቁ በተደጋጋሚ አስተያየት ይሰጣል። እነዚህን ፓርቲዎች ሰብሰቦ ድርድር መቀመጥ የአገሪቱን ችግር ማስተንፈስ እንደማይቻል የሚከራከሩ ወገኖች ድርድሩን አያከብሩትም። በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ እዚህ ደረጃ መምጣቱ በራሱ አንድ ርምጃ ነው የሚሉና ድጋፋቸውን የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም። በውጤቱ ሲታይ ግን አመጹም፣ ቅሬታውም፣ ችግሩም መልኩን ሲቀያይር እንጂ ሲለዝብ ማስተዋል አልተቻለም። ለዚህም ይመስላል የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ “ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር … [Read more...] about ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
ከውጪ ሀገር የመጡ ሰዎች ለአፄ ምኒልክ ስለ ፎቶግራፍ እንዲህ ብለው አስረዷቸው "በአውሮጳ አንድ ትንሽ ሳጥን አለች ሰውን፣ ፈረሱን፣ ቤተመንግስቱን ሁሉ ወደ ሳጥኗ ታስገባና ሁሉን ትንሽ አርጋ ታሳያለች" አሏቸው። ምኒልክም በሰሙት ነገር ተገርመው እንዴት ይሆናል ይሄን ነገር ማየት አለብኝ ብለው የፎቶ ማንሻ እንዲመጣ አዘዙ። የፎቶ ማንሻውም (ካሜራ) ከእነ አንሺው በ1875 ዓም ወደ ሀገራችን ገባ። ሆኖም ግን አጼ ምኒልክ ፎቶውን ሊነሱ ሲሉ ቀሳውስቱ መኳንንቱ ከለከሏቸው፣ ርኩስ ነገር ነውና አጥፉልን አሏቸው። ምኒልክም "እግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር አታርጉ፣ አትንኩ፣ ነውር ነው ማለት አምላክን መቃውም ነው እንዲህ ያለ ሀሳብ አታስቡ ዞር በሉ ከፊቴ" ብለው ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ም አጼ ምኒልክ የምትመለከቱትን የመጀመሪያ ፎቶ ተነሱ። መልካቸውንም በማየታቸው … [Read more...] about ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
Remembering Peaceful Demonstrators Murdered by TPLF in Bahir Dar One Year Ago The area in which this took place is called Abay Mado“Kobel”, located in Bahir Dar. It was in the August of last year when all over the country, Ethiopians, including the youth were peacefully demonstrating in large numbers, expressing their displeasure towards the ethnocentric, extremely corrupt and suppressive regime of the TPLF. The youth in Bahir Dar was expressing its solidarity with “Welkite” and “Oromo” … [Read more...] about Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!
ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ህወሓት የሚመካበትን የታጠቀ ሰራዊት የሚመሩ ከፍተኛ መኮንኖችና ጄኔራሎች በጡረታ ለመሰናበት ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። የአስቸኳይ አዋጁ ሲነሳ መልስ እንደሚያገኙ ቃል የተገባላቸው እንዳሉም ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ለደህንነት ሲባል መረጃውን ያገኘበትን ሳይገለጽ እንደጠቆመው “መከላከያ ሰራዊት” የሚባለውን የህወሓት ሥልጣን አስጠባቂ የታጠቀ ኃይል ከሚመሩት ጄኔራሎች መካከል “በቃኝ” ያሉት ጄኔራሎች ከሰባት በላይ ሲሆኑ፣ በከፍተኛ መኮንን ደረጃ ያሉት ግን ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው። ጄኔራሎቹ ሰራዊቱን ለመሰናበት ያቀረቡትን ዋና ምክንያት የመረጃ ሰዎቹ ቃል በቃል ይፋ ባያደርጉም፣ ከሰራዊቱ ጋር ላለመቀጠል ዕድሜ፣ ጤና፣ ጋብቻና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎችን እንደ ምክንያት አቅርበዋል። መልቀቂያ ያስገቡት ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች ተመሳሳይ ፍላጎት … [Read more...] about የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!
ትልቅ ሰው ትልቅን
ይባላል ... ድሮም ይነገራል ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ሲባል በፊትም ሰምተናል ይኸው ዕውነት ሆኖ ሲፈጸም አየን ቃሉ በነጋሽ ገ/ማርያም፣ በተስፋዬ ሳህሉ የሐምሌ ወርን የሰላሳ ቀናት እቅፍ በነኀሴ ተክተን ሳናልፍ ሁለቱን ታላላቅ የጥበብ ከዋክብት አከታትለን አጣን የአዛውንቶች ክበብን ዘጋን ፀጋዬ ገ/መድህን በጻፈው አባተ መኩሪያ ባዘጋጀው አውላቸው ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ በተጫወቱበት ዓለሙና ሲራክ አብረው በሆኑበት እነ አስናቀች ወርቁ፣ በላይነሽ አመዴ፣ እነ አባተ መኩሪያ መላኩ አሻግሬና ዘነበች ታደሰ እነ ሠይፈ አርኣያ ሙናዬ መንበሩ፣ ኃይማኖት ዓለሙ፣ እነ አስራት አንለይ በኃይሉ መንገሻ፣ ሱራፌል በጋሻው፣ ያ ፍስሀ በላይ በተካፈሉበት ... የላይ ቤት ትዕይንት ተባብረው አብረው አንድ … [Read more...] about ትልቅ ሰው ትልቅን
ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ክምሩን የሀገር ሀብት ስርቆት ፣ ብክነት ሳስበው ... ክምር በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር መዋዕለ ንዋይ ከመቶ ባልበለጡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የመዘረፉን ወንጀል እየሰ ማን ነው ። ጥሎብኝ ገንዘቡን ወደ አባይ ግድብ አስጠጋውና የሳውዲ ነዋሪ ለአመታት ካጠራቀመው ጋር አወዳድረዋለሁ። አልገናኝህ ይለኛል ... ገንዘቡ ከፍ ሲል ሌላ ማወዳደሪያ እፈልጋለሁ ። .. ውጭ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ ወደ ሀገር ከሚልከው ገንዘብ የተገኘውን ገቢ አስበውና እንደገና የተሰረቀው ከባድ የመሆኑን ክብደት ያስደነግጠኛል ፣ እደነግጣለሁ ። "ጠፋ ፣ ተሰረቀ" የተባለው የዚህች ድሃ ሀገር ገንዘብ ስንት አውሮፕላን እንደሚገዛ ሳሰላ ውዬም አውቃለሁ፣ የሞኝ ነገር ትሉኝ ይሆናል። ግን አይደለም። የገንዘቡን ክብደት ለማወቅ እንጅ ... እንዲህ ሲቆጨኝ ስዳክር ነው የሰነበትኩት ክምሩ የሀገር ሀብት መሰረቅ … [Read more...] about ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫሎች ላይ የቦይኮት (እቀባ) ዘመቻዎች ተነስተው ነበር። የዘመቻዎቹን ውጤቶችም አይተናቸዋል። በዚች አጭር ጽሁፌ የማተኩረው በውጤቶቹ ላይ አይደለም። በሲያትሉም ሆነ በሮም ዝግጅቶች ላይ ስለነበርኩ፣ የቦይኮት ዘመቻዎቹ ከጅምሩ ጥቅም እና ጉዳቶችን አመዛዝነው ነበር ወይ የሚለውን በጥቂቱ ለመፈተሽ እሞክራለሁ። በዚህ ርዕስ ላይ ስጽፍ አዋራ እንደሚነሳ አምናለሁ። በጉዳዩ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲወያዩ ብታዘብም በፍርሃት ይሁን በሌላ ምክንያት ሃሳባቸውን በአደባባይ ለመናገር ግን ሲደፍሩ አይታይም። ሃሳባቸውን በድፍረት የሚሰነዝሩ ወገኖችም ቦይኮት ስለሚደረጉ ብዙዎች ዝምታን ቢመርጡ አይደንቅም። "አህያ የለኝ ከጅበ አልጣላ" ብሎ ሃሳቡን በነጻ ለመግለጽ የሚሞክር ደግሞ ይሰደባል። በሳይበሩ አለም፣ ወቅትን እየጠበቀች በምትነደው … [Read more...] about ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
የግፍ ለከት አልባው ህወሓት
የፌዴሬሽን ምክር-ቤት የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የሚባለው ኮሚቴ እንደግዴታው "ተርጉሞ" መመለስ የነበረብትን ሠነድ ባለመመለሱ የ3 ወር (ጥቅምት 2010) ተለዋጭ ቀጠሮ ለዶ/ር መረራ ጉዲና ተሰጥቷል - የህወሓት ግፍ ለከት የለውም። ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የግፍ ለከት አልባው ህወሓት