“የትምህርት ጥራቱ እጅግ አሳፋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል” ዶ/ር መስፍን “ከኮሌጅ ተመርቀው 7ኛና 8ኛ ክፍሎችን ለማስተማር ዝግጁ ከሆኑ መምህራን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ብቻ ሳይሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና ማለፍ አልቻሉም” “የኢትዮጵያ 7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ፣ አሜሪካ፣ ሲንጋፖርና መሰል አገራት የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ ጋር እኩል ነው” የግንቦት 20 መርዛማ ፍሬዎችን በተከታታይ ባተምንበት ጊዜ ከፍሬዎቹ መካከል “ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፖሊሲ” አንዱ እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ሕወሓት ሆን ብሎ በሚከተለውና አዲሱን ትውልድ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ አስተሳሰብም ሆነ አመለካከት ለመነጠል በሚያራምደው ፖሊሲ በድንቁር ተገዢ አድርጎ የመግዛቱን ዓላማ በፖሊሲ ደረጃ ሲተገብረው ቆይቷል፡፡ በድንቁርና ጭለማ ውስጥ ያሉትን ሹማምንቱን “ተፈጭና ተመረቅ” … [Read more...] about የተማሪዎች ዕውቀት ደረጃ “150 ዓመታት ወደ ኋላ” ቀርቷል!
Archives for July 2017
“ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]
ለብዙዎቹ ችግሮቻችን ፍቱን መድኃኒት አድርጌ የምወስደው፣ ጉዳዩን በዘመን ቁመት እና በዓለም ሕዝቦች ታሪክ አግድም መመልከት ነው። ዓለም በበቂ ሁኔታ የምንማርባቸው ስኬቶች እና ውድቀቶች አሏት። ዘውጌኝነት፣ ብሔርተኝነት እና ዜግነት የመሳሰሉትም የብቻችን ጉዳዮች አይደሉም። ዓለም በየፈርጁ የዳከረችበት እና እየዳከረችበት ያለ ችግር ነው። ስለዚህ ጥያቄውን በቅጡ ለማበጃጀትም ይሁን፣ አዋጭ መልስ ለመፈለግ ከሰው ልጆች እንደአንድ የሚያደርገንን ታሪክ የምናውቀውን ያክል ማሰስ ያስፈልጋል። ይህን ከጠቆምኩ በኋላ ወደ የበኩሌን ለመሞከር ወደ አጀንዳዬ እዘልቃለሁ። የዘውግ ብሔርተኝነት ምንድን ነው? የዘውግ ብሔርተኝነት (ethnonationalism) የአንድ ዘውግ (ethnic) ቡድን ነጻ አገር እንዲመሠርት ወይም ከመገንጠል ወዲህ ያለውን የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ለማስቻል የሚደረግ … [Read more...] about “ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]
ሕገመንግሥቱ የፀደቀው በቀጥታ ሕዝቡ ወስኖበት ሳይሆን በተወካዮች ነው – ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ
በህወሓት ትዕዛዝና አርቃቂነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን "ሕገ መንግሥት" "አርቃቂ" ኮሚሲዮን በሊቀመንበርነት የመሩት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ "ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱን ስናፀድቅ ህዝቡ በቀጥታ አልወሰነበትም፡፡ በተወካዮች በኩል ነው የወሰነው" በማለት ከሌሎች አዲስ አድማስ ቃለ meጠይቅ ካደረገላቸው ግለሰቦች ጋር በመሆን "የማይገሠሠው ሕገ መንግሥት" "ክብሩ"ን አውርደውታል፡፡ ዘገባው እንዲህ ቀርቧል:- በፓርቲዎች ድርድር ኢህአዴግ፤ “ልደራደርባቸውም አልችልም” በሚል ውድቅ ካደረጋቸው አጀንዳዎች አንዱ የህገ መንግስቱ መሻሻል ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ህገ መንግስቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር መቅረብ የሚችል አይደለም? ኢህአዴግ ለምን ለድርድርና ለውይይት እንዳይቀርብ ፈለገ? ህገ መንግስቱ ሲጸድቅ ተሳትፎ የነበራቸው አንጋፋ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ምሁራን አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡ … [Read more...] about ሕገመንግሥቱ የፀደቀው በቀጥታ ሕዝቡ ወስኖበት ሳይሆን በተወካዮች ነው – ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ
ስለ ሸገር የምለው አለኝ
"ነፍጠኛው ስርዐት ስማቸውን ቀየራቸው ከተባሉት ቦታዎች ውስጥ መርካቶ፣ ፒያሳና ካዛንቺስ ይገኙበታል፤ እነዚህ ጣሊያናዊ ስሞች ናቸው፤ የክሪስፒና የምኒልክ፣ የተፈሪና የሙሶሎኒ ዝምድና ይጣራልን፡፡ * የታሪክ መፅሐፍቱ "Oromo migration movement" ሲሉን ከርመው አይ "Oromo population movement" ነው ብለው አስተካከሉና መዳ ወላቡ ከህዝቡ መስፋፋት በፊት የኦሮሞ ማዕከልና መነሻ መሆኑን ነገሩን፡፡ መስፋፋቱ ደግሞ እ.ኤ.አ ከ1522-1618 ነው እስከዛ ድረስ አዲስ አበባ የማን ነበረች? * ከክርስቲያኑ ግዛተ አፄ እና ከሙስሊሙ የ16ኛው ክ/ዘ አታካችና ረጅም ጦርነት በኋላ የሁለቱም ወገን ጃይንቶች ገላውዲዎስና ኢማም አህመድን ሞት ተከትሎ ተዋጊዎቹ መዳከማቸው ለኦሮሞ ግስጋሴ አይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አፄ ሚናስ የጦራቸውን መሳሳት ተከትሎ የኦሮሞ ተዋጊዎችን … [Read more...] about ስለ ሸገር የምለው አለኝ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የ EDF አቋም መግለጫ
የኢትዮጵያውያን የውይይትና ምክክር መድረክ (ኢውምመ) (EDF) በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተመሰረተ መድረክ ሲሆን በኢትዮጵያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የፖለቲካዊ ችግሮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ ለተፈላጊ ለውጦች የሚታገል ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት አመራር አባላት በቅርቡ በሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚተነትነውን ረቂቅ አዋጅ በጥልቀት ተወያይቶበታል። ተወያይቶ የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል በEDF እምነት በመጀመሪያ ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ከብሄር ፖለቲካ የመነጩ አንዳንድ የህገ መንግስቱ አንቀጾች ናቸው። ለዚህ ለአሁኑ የሚንስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ መነሻውም ይሄው ህገ-መንግስቱ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 5 ነው። ህገ-መንግስቱ ከብሄር … [Read more...] about የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የ EDF አቋም መግለጫ
የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
ራዕይ ለኢትዮጵያ - Vision Ethiopia Vision Ethiopia and ESAT Fourth Conference Second call for papers, July 3, 2017 Conference Theme: Building Democratic Institutions in Ethiopia የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት Vision Ethiopia, an independent network of Ethiopian scholars and professionals, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT), is pleased to announce that the Fourth Conference will be held in Washington D.C. on September 16 and 17, 2017. We thank those who … [Read more...] about የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ሚያዚያ 27፤2009 የተከበረበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዕለቱ (May 5, 2017) “የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ለኅትመት አቅርቦ ነበር፡፡ የጽሁፉ ዓላማ በዚህ መልኩ ቀርቦ ነበር፤ “በየዓመቱ ሚያዝያ 27 የሚከበረው የድል ቀን በኢትዮጵያ የቀን መቁጣሪያ (ካሌንደር) ላይ ሥራ ተዘግቶ እንዲከበር ቢደረግም ትውልዱ የቀደሙ እናትና አባቶቹን የተጋድሎ ታሪክ እንዲያወቅ የሚያስችል የበዓል አከባበር አይታይም፡፡ ዕለቱም እንደአንድ ተራ የረፍት ቀን ያልፋል፡፡ በአንጻሩ አንዳች አገራዊ ፋይዳ የሌላቸው የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ … የምሥረታ ቀን እየተባለ በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ የሚወጣባቸው ለወራት በዕቅድ ተይዘው የሚደገሱ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ይደረጋል፡፡ “አዲስ አበባ አራት … [Read more...] about ራስ እምሩን በተመለከተ፤
“ደግ ሰዉ አለፈ ..”
አባት ያቆየዉን ልጅ እዲጠብቀዉ የተከበሩ ኮ/ል አስናቀ እንግዳ፤ ኢትዮጵያን ለሚረከበዉ ወጣት ትዉልድ አዘዉትረዉ እንዲህ ይሉ ነበር። "አንተ የዛሬ ትዉልድ ሆይ! አንድ ጊዜ ቆም ብለህ አዳምጠኝ። ከተቻለ አባቶችህ ከሠሩት ላቅ ያለ፤ በስተቀር የእነሱን ያህል ካልሠራህ ሐገር አይኖርህም። የእኔ ትዉልድ በስልጣኔ ኋላ ቀር ቢሆንም፤አባቶቹ ከሠሩት በላይ አከናዉኖ አደራዉን ተወጥቶ፤ሀገሪቱን አስረክቦሃል።አንተም ለልጆችህ ይህችን ጥንታዊ ሐገር በክብር ለማስረከብ እንድትችል፤ ወኔ ይኑርህ። ወኔ እንዲኖርህ ለሆድህ አትገዛ። ኩራት ራት ነዉ ብለህ፤ ለራስህ ኀሊና ተገዛ " ይሉ ነበር። እንግዲህ ይህን የመሰለ ቁምነገር ሲያስተምሩ የኖሩ አባት፤ የወጣትነት ጊዚአቸዉ ምን እንደሚመስል ከአርበኝነትና ከጠቅላላ የትግል ታሪካቸዉ የቀነጨብኩትን ከዚህ በታች በግጥም እያቀረብኩ፤ኮ/ል አስናቀ እንግዳ በርግጥ … [Read more...] about “ደግ ሰዉ አለፈ ..”