• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕገመንግሥቱ የፀደቀው በቀጥታ ሕዝቡ ወስኖበት ሳይሆን በተወካዮች ነው – ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ

July 4, 2017 09:50 am by Editor 2 Comments

በህወሓት ትዕዛዝና አርቃቂነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን “ሕገ መንግሥት” “አርቃቂ” ኮሚሲዮን በሊቀመንበርነት የመሩት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ “ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱን ስናፀድቅ ህዝቡ በቀጥታ አልወሰነበትም፡፡ በተወካዮች በኩል ነው የወሰነው” በማለት ከሌሎች አዲስ አድማስ ቃለ meጠይቅ ካደረገላቸው ግለሰቦች ጋር በመሆን “የማይገሠሠው ሕገ መንግሥት” “ክብሩ”ን አውርደውታል፡፡ ዘገባው እንዲህ ቀርቧል:-

በፓርቲዎች ድርድር ኢህአዴግ፤ “ልደራደርባቸውም አልችልም” በሚል ውድቅ ካደረጋቸው አጀንዳዎች አንዱ የህገ መንግስቱ መሻሻል ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ህገ መንግስቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር መቅረብ የሚችል አይደለም? ኢህአዴግ ለምን ለድርድርና ለውይይት እንዳይቀርብ ፈለገ? ህገ መንግስቱ ሲጸድቅ ተሳትፎ የነበራቸው አንጋፋ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ምሁራን አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡ እንደተለመደው አጀንዳው ለውይይት ክፍት ነው፡፡ ለፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄው ፖለቲካዊ ውይይት ነው፡፡

“ህገ መንግስት ለምንድነው ለድርድር የማይቀርበው?” ስዩም ተሾመ (የዩኒቨርሲቲ መምህር)

ህገ መንግስቱ ተግባር ላይ ከዋለ ከ20 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ህገ መንግስቱ በወቅቱ በውይይት ነው የፀደቀው፡፡ በውይይት የፀደቀ ነገር በውይይት የማይሻሻልበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ ህገ መንግስቱ መሻሻል አለበት ለሚለው መነሻ ተደርገው ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል ለምሳሌ የፌደራል የስራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ አንዱ ነው፡፡ በተለያዩ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን፤“በአፍሪካ ብዙ ተናጋሪ ካላቸው ቋንቋዎች አንዱ ኦሮሚኛ ነው፤ በኢትዮጵያም ሰፊ ማህበረሰብ ቋንቋውን ተናጋሪ ነው፡፡” የሚሉ ጉዳዮች ይነሳሉ፡፡ ይሄን ለማስተናገድ እንግዲህ ህገ መንግስቱን ማሻሻል ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

በርካታ ቋንቋዎችን ለስራ ቋንቋነት መጠቀም ደግሞ በሌላው አለምም የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ አስራ አንድ የስራ ቋንቋ ነው ያላት፡፡ በኛም ሀገር ይሄ ቢለመድ በግሌ መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡ የስራ ቋንቋ መጨመር ደግሞ ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም፡፡

እነዚህን የመሳሰሉ በተቃውሞ ወቅት ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ካስፈለገ ህገ መንግስቱ መሻሻሉ የግድ ነው፡፡ ህገ መንግስቱ በሚፀድቅበት ወቅት ያልታዩ፣ አሁን ግን ቢካተቱ ተብለው የሚቀርቡ ሀሳቦችን ለማካተት ድርድር ቢደረግ ምንድነው ችግሩ? ህገ መንግስቱ ለድርድር መቅረብ አለበት፡፡ የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት ከታሰበ ይሄን ማጤን ተገቢ ነው፡፡ የትኛውም ህገ መንግስት ዘመን የሚጠይቃቸውንና የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ለማሟላትና ለየወቅቱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት መሻሻል ካለበት፣ ለውይይት ቀርቦ መሻሻል አለበት።

ለምሳሌ ህገ መንግስቱ ለግለሰቦች መብት ያለው ቦታ ትንሽ ነው፡፡ ለብሄርተኝነትና ለብሄር ጉዳይ ትኩረት የሚሰጥ ህገ መንግስት ነው፡፡ ይሄ ብሄርተኝነት የህዝቦች ማህበራዊ ግንኙነት እየዳበረ ሲሄድ ተቀይሮ፣ ብሄርተኝነቱ እየላላ ሄዶ፣ ግለሰባዊ እሳቤና አንድነታዊ አስተሳሰብ ሊጎለብት ይችላል። ከቡድን መብት ወደ ግለሰብ መብት እየተቀየረ ይሄዳል፡፡ ይሄን ሂደት ለማስተናገድ ህገ መንግስቱ መፈተሽ አለበት፡፡

ሰዎች በውይይትና በድርድር ያፀደቁትን ነገር ለድርድር አይቀርብም ማለት ምን ማለት ነው? ይሄ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በቃ! ህገ መንግስቱ መሻሻል ካለበት ወይም ለውይይት መቅረብ ካለበት፣ መቅረብ አለበት፡፡ ጉዳዩን ዝግ ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡

ህገ መንግስቱ ከችግር የፀዳ፣ መሻሻል የማይችል ከሆነ፣ ያን መሆኑን የሚታወቀውም ለውይይትና ለድርድር መቅረብ ሲችል ብቻ ነው፡፡ የህገ መንግስቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ከዚህ የተሻለ እድልም አይኖርም፡፡

ስለ ትክክለኝነቱ በተለያየ አውድ ከማስረዳት፣ በዚህ መንገድ መፈተሽ የተሻለ መፍትሄ ያመጣል። ከዚህ ውጪ ህገ መንግስቱ ለውይይት ይቅረብ እየተባለ አይቀርብም ማለት፣ “ህገ መንግስቱ ችግር አለበት፤ አዎ እንዳይቀየር የምንፈለገው ነገር አለ” እንደማለት ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ለውይይትና ድርድር መቅረቡ በምንም መመዘኛ ችግር ሊሆን አይችልም፤ መቅረብ ይችላል፡፡ ሌሎች ህጎችና አዋጆች ላይ ተደራድሮ ህገ መንግስቱ ላይ አለመደራደር አንደምታው ምንድን ነው? ከዚህ አንፃር መታየት አለበት፡፡


“በሀገሪቱ የተነሱ ውዝግቦች ከህገ መንግስቱ ጋር የተገናኙ ናቸው” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ፖለቲከኛ)

ህገ መንግስቱ ፀድቆ ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ብዙ አከራካሪ ጉዳዮች ይነሱበታል፡፡ ዘመንና ጊዜም አዳዲስ ነገሮችን ያመጣል፡፡ በህገ መንግስቱ ተፅፈው ወደ ተግባር ተሟልተው ያልወረዱ ጉዳዮችም አሉ። አዳዲስ አስተሳሰቦችም መጥተዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የምርጫ ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ከ2 ዓመት በፊት ህገ መንግስቱ የሚሻሻልበት መንገድ መኖር እንዳለበትና ሊታሰብበት እንደሚገባ ያቀረብኩት ሃሳብ ነበር፡፡ ይህ ሀሳብ አሁንም ቢጤን መልካም ነው፡፡

በሀገሪቱ የተነሱ ውዝግቦች ህገ መንግስቱን ይመለከታሉ፡፡ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በኮንሶ—በሌሎችም የተነሱ ተቃውሞና ግጭቶች ማጠንጠኛቸው ህገ መንግስቱ ላይ ያሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ቢሆንም አብላጫው ህገ መንግስታዊ ነው፡፡ “ህገ መንግስቱ በትክክል ተግባራዊ አልተደረገም፤ ህገ መንግስቱ እንደገና መታየት አለበት” የሚሉ ሀሳቦች ሁሉ ሲቀርቡ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሰሞኑን ይፋ የተደረገው ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ የሚኖረው ልዩ ጥቅም ጉዳይ፣ እንዲሁም የህገ መንግስቱ አንቀፅ 39 ጉዳይ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በተቃውሞ ወቅት ሲንፀባረቁ የነበሩ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ህገ መንግስቱን በድጋሚ መፈተሹ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ህገ መንግስቱ እንዴት ይሻሻል ወይም እንዴት ውይይት ሊደረግበት ይችላል የሚለው በዚያው በህገ መንግስቱ የሰፈረ ጉዳይ ነው፡፡ ማሻሻያ ሀሳቡን ግለሰቦችም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ በእነዚህ አካላት የሚቀርቡ የማሻሻያ ሀሳቦች በረቂቅ ደረጃ ከተዘጋጁ በኋላ ለህዝብ ውይይትና ለህዝብ ውሳኔ ይቀርባሉ፡፡ ይሄ ነው ሂደቱ፡፡

ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱን ስናፀድቅ ህዝቡ በቀጥታ አልወሰነበትም፡፡ በተወካዮች በኩል ነው የወሰነው፡፡ አሁንም መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የማሻሻያ ረቂቅ ሀሳብ ከተዘጋጀ በኋላ ለህዝብ ውሳኔና ውይይት ነው የሚቀርበው፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተናጥላዊ ድርድር ብቻ ህገ መንግስት አይሻሻልም፡፡ ሊወያይበት የሚገባውም ህዝቡ ነው። ህገ መንግስቱ ይሻሻል አይሻሻል የሚለው ሀሳብ በራሱ፣ ለህዝበ ውሳኔ መቅረብ አለበት፡፡


“ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ህዝቡን ማወያየት ያስፈልጋል” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ (ፖለቲከኛ)

በመጀመሪያ እየተደረገ ያለው ድርድር ላይ ኢህአዴግ በቀና መንገድ ገብቶበታል ብዬ አላምንም። “ሀገሪቱን ወደ አለመረጋጋት የከተታት ምንድን ነው?” ተብሎ ተጠንቶ፣ ምክኒያቶቹ ቅደም ተከተል ተሰጥቷቸው መቅረብ ነበረባቸው፡፡ ህገ መንግስቱን በተመለከተም መነጋገር የምንችለው ከዚህ በመነሳት ሊሆን ይገባው ነበር፡፡ አሁን እየተኬደበት ያለው መንገድ የለብለብ ነው፡፡

ኢህአዴግ በድርድሩ “ይሄን ተቀብያለሁ፣ ያንን አጀንዳ አልተቀበልኩም” ብሎ ሲገልፅ የተቀበላቸው አጀንዳዎች ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ አይደለም የተቀበላቸው፡፡ የፀረ ሽብር፣ የፕሬስ ህጎችን… የአፈፃፀም ጉዳይ ብቻ አድርጎ ነው የተመለከታቸው። እንዴት በአፈፃፀም ላይ ድርድር ይደረጋል፡፡ የአፈፃፀም ጉዳይ ብቻ አድርጎ ነው የተመለከታቸው። እንዴት በአፈፃፀም ላይ ድርድር ይደረጋል፡፡ በአፈፃፀም ላይ ተደራድሮ ሀገሪቱን አቅጣጫ ማስያዝ አይቻልም፡፡ ህገ መንግስቱ መሻሻል ካለበት፣ አይነኬ አይደለም መሻሻል ይችላል፡፡ እንዴት ይሻሻላል የሚለው ደግሞ በራሱ በህገ መንግስቱ በግልፅ ተደንግጓል፡፡

ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ህዝቡን ማወያየት ያስፈልጋል፡፡ እያወያዩ ሀሳቦችን እያሰባሰቡና ወደ መድረክ እያመጡ፣ ህዝብ በፈለገው መንገድ መኬድ አለበት፡፡ የህገ መንግስት መሻሻል ይቅርና ሀሳብን በነፃነት መግለፅ፣ መደራጀት በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ለመደራደር ራሱ ቅድሚያ ከህዝቡ ጋር ነፃ  ውይይት መደረግ አለበት፡፡ አስቸኳይ አዋጅ ባለበት ሁኔታ ድርድር ቢደረግም፣ ከህዝቡ ያልመነጨ ድርድር የትም አያደርስም፡፡

በኔ አተያይ የኢትዮጵያ ወቅታዊ አንገብጋቢ ችግር፣ በሀገሪቱ የህግ ልዕልና እየተጣሰ መሆኑ ነው፡፡ በርካታ ህጎችን ህገ መንግስቱ አካቷል፡፡ ግን አሁን ወቅቱ የሚጠይቀው ነገር ካለ፣ ህገ መንግስቱ ተፈትሾ ሊካተት ወይም ሊቀነስ የማይችልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እንደ‘ኔ ግን ያሉትን የህግ ጥሰቶች ለማስተካከል ጥረት ቢደረግ፣ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ችግር ለመቅረፍ ብዙ ርቀት መሄድ ይቻል ነበር፡፡ ህገ መንግስት ማሻሻል ኋላ ላይ ሊመጣ ይችላል፡፡ የህገ መንግስት ማሻሻያ በአስቸኳይ ካልተደረገ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይመጣም የሚል እምነት የለኝም፡፡ እምነቴ ህገ መንግስቱ ውስጥ ያሉ መብቶች፣ በትክክለኛ መንገድ ቢተገበሩ ኖሮ፣ ወደዚህ አለመረጋጋት አንገባም ነበር የሚል ነው፡፡


“ከህዝቡ በስተቀር ማንም ህገ መንግስቱን መንካት አይችልም” ዶ/ር ንጋት አስፋው (ፖለቲከኛ)

ህገ መንግስቱን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ማቅረቡ ትንሽ ከበድ ይላል፡፡ ህገ መንግስት ማለት ህዝብ ያወጣው ህግ ማለት ነው፡፡ የህዝብ ህግ ነው፡፡ በተወካዮች ም/ቤት የፀደቀ ህግ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የፖለቲካ ድርጅቶች በመጠየቃቸው ሳይሆን ህገ መንግስቱ ሊሻሻልባቸው የሚችሉ የራሱ አካሄድ አለው፡፡

ህዝቡ በሚያደርገው ውሳኔ ነው የህገ መንግስቱ ጉዳይ ሊታይ የሚገባው፡፡ ለድርድር ይቅረብ አይቅረብ የሚለውም ቢሆን በህዝበ ውሳኔ (Referendum) የሚወሰን መሆን አለበት፡፡ ሊሻሻልና ሊቀየር የሚችለውም በህዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ባለቤቱ ህዝብ ነው፡፡

አንድ ህገ መንግስት፤ የሀገር ህግ ሊሆን የሚችለው፣ ከዳር እስከ ዳር የህዝብ ተወካዮች በሙሉ ያሉበትና በህግ ባለሙያዎች ተቀምሞና ተዘጋጅቶ፣ ህዝቡ በየደረጃው ተወያይቶበት የሚፀድቅ ሲሆን ነው፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ስናይ፣ ህግ የሚያወጣው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው። የሚያስፈፅመው መንግስት፣ ተርጓሚው የፍትህ አካላት ናቸው፡፡

እዚህ ላይ የኔ ጥያቄ፤ አሁን በእርግጥ ትክክለኛ የህዝብ ተወካይ አለን ወይ የሚለው ነው። አለ! ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ሳይሆን የኢህአዴግ አባላት ተወካዮች ነው ያለው፣ የሚል እምነት አለኝ። መቶ በመቶ በዚህ ስርዓት የተያዘ ነው፡፡ ህግ የሚያወጣው፣ የሚያስፈፅመው፣ የሚተረጉመው ራሱ ስርአቱ ነው፡፡ በአንድ ሳንባ የሚተነፍስ የፖለቲካ ስርአት ነው ያለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህን ህገ መንግስት ከምልአተ ህዝቡ በስተቀር ማንም ተወካይ ሊነካው አይገባም ባይ ነኝ፡፡ ከህዝቡ በስተቀር ማንም ሊነካው አይችልም፡፡ የህገ መንግስቱ ባለቤት ህዝቡ ነው፤ ሊነካው ሊያሻሽለው ሊያስተካክለው የሚችለው ባለቤቱ ብቻ ነው፡፡ ከባለቤቱ ውጪ ማንም አውቅልሃለሁ የሚል ሊነካው አይችልም፡፡ ይህ ህገ መንግስት በአመዛኙ ከፌደራል ስርአቱ ጋር ተጣጥሞ የወጣ ነው፡፡ በዚህ መሃል አንዳንድ ግልፅ ጉድለቶች አሉ፡፡ ያሉትንም ጉድለቶች ቢሆን ማሻሻል የሚችለው ህዝቡ ነው፡፡


“ህገ መንግስቱ ለውይይትና ድርድር መቅረብ ይችላል” አቶ ገብሩ አስራት (ፖለቲከኛ)

በመጀመሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለበት፣ የተቃዋሚ አመራሮችና ግለሰቦች በታሰሩበት የሚደረግ ድርድር እውነተኛ ነው፤ኢህአዴግም በአሁን ወቅት ለድርድር ዝግጁ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ኢህአዴግ ሊያሻሽላቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች የፓርቲዎች ይሁንታ አለበት ለማለት እንጂ እውነተኛ ድርድር አይደለም፡፡ አጀንዳ አቀራረፁም ችግር አለበት፡፡ ኢህአዴግ የሚፈልጋቸው ብቻ ናቸው ለድርድሩ የቀረቡት፡፡

የህገ መንግስት ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም ብሎ ዋናውን ጉዳይ ዝግ አድርጎታል፡፡ የህገ መንግስት ጉዳይ ሁኔታው ከፈቀደ ለድርድር ሊቀርብ ይችላል፡፡ ራሱ ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ ወደዚህ ድርድር ሲገባ፣ “ካስፈለገ አንዳንድ የህገ መንግስት ማሻሻያዎችን አደርጋለሁ” ብሎ ነበር፡፡ ታዲያ ይሄ ቃል የት ገባ? ለምሳሌ የፓርላማ ውክልና ጉዳይ መሻሻል እንዳለበት ኢህአዴግ አስታውቆ ነበር፤ ይሄን ለማድረግ የህገ መንግስቱን መሻሻል ይጠይቃል፡፡

የህገ መንግስት ጉዳይ ላይ ከመሄዳችን በፊት ከህገ መንግስቱ በመለስ ያሉ ጉዳዮችን ሳይቀር ኢህአዴግ ሊያነሳቸው የፈለገ አይመስልም፡፡ እኛ ወሳኝ የምንለው የፖለቲካ ምህዳር ጉዳይ ነው፡፡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለበት ደግሞ የፖለቲካ ምህዳር መስፋት አይታሰብም፤ ይሄ ባለበት እንዴት ነው ድርድር ሊካሄድ የሚችለው? “በኢትዮጵያ ምንም የፖለቲካ እስረኞች የሉም” ብሎ ከሚያምን ጋር እንዴት ድርድር ሊካሄድ ይችላል? ከህገ መንግስቱ በፊት እነዚህን ጉዳዮች ኢህአዴግ መቀበል ነበረበት።

ህዝቡ ያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ህገ መንግስቱን ማሻሻል የሚያስፈልጉ ከሆነ፣ ህገ መንግስቱ ለምን አይሻሻልም? ፖለቲከኞች እኮ ህዝቡን ይወክላሉ፡፡ ስለሚወክሉም ነው የህገ መንግስት ድርድር የጠየቄት፡፡ ለምሳሌ አንቀፅ 39፣ የመገንጠል ጉዳይ አለ፡፡ ይሄ ችግር ያለበት አንቀፅ ነው፤ መገንጠል የሚለው አስፈላጊ አይደለም፤ የመገንጠል ጥያቄ የሚለው መሻሻል አለበት፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ይቀድማል፤ ከዚያም በህገ መንግስቱ ላይ መወያየትና መደራደር ያስፈልጋል፡፡ ህገ መንግስቱ ለድርድር መቅረብ ይችላል፡፡ መሬት የመንግስት ነው የሚለው የህገ መንግስቱ አንቀፅ በራሱ ተቃውሞ  የሚቀርብበት ነው፡፡

የፖለቲካ ምህዳር ሲጠብ ፅንፈኝነትና ነውጥ ነው እያየለ የሚመጣው፡፡ እነዚህ ከተለወጡ በኋላ ህዝቡ ራሱ በሚፈልገው መንገድ ማሻሻል መለወጥ ይችላል፡፡ (አለማየሁ አንበሴ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    July 6, 2017 05:56 pm at 5:56 pm

    ህገ መንግስቱ ለውይይትና ለድርድር መቅረብ ይችላልን?
    ኢህአዴግ ለምን ሕገመንግስቱ ለድርድርና ለውይይት እንዳይቀርብ ፈለገ?
    “ሕገ መንግስቱ ሲፀድቅ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልብሳቸውን አውልቀው ጨፍረዋል።”የነጻው አውጭው አባት ስብሃት ነጋ
    ___በመግባባትና በመተማመን በዕኩልነት እና በፍትሃዊነት ላይ የተመሠረተ የማይለው ማኒፌስቶ በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ የሚለው ሽሙጥ አዳሜን የህወአት ልዩ ጥቅማጥቅመኛ..(ተሞሳሽ…ሞሳሽ..አሟሳሽ)»አድርጎ ስለጠረነፈው ነው።አራት ነጥብ።
    ስዩም ተሾመ (የዩኒቨርሲቲ መምህር)ደቡብ አፍሪካ አስራ አንድ የስራ ቋንቋ ነው ያላት፡፡ እኛ በአንድ ቋንቋ ተግባብተን ለመኖር አልቻልንም ስለምስራቀ አፍሪካ ብዙ ቋንቋ ብትናገር ኦርሞ ተጠቃሚ ይሆናል በሚለው ህሳቤ ነው? ይህ በሰሜን ኬንያ ያሉ ጋሎችን እራሳችሁን ኦሮሞ በሉ ብለው እሰው ሀገር ገብተው ሲቀሰቅሱና ሲቆሰቁሱ ተገኝተው የታሰሩም ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎች እንዳሉ ይታወቃል። ታንዛኒያም፡ ኡጋንዳም፡ ያሉ አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ጋሎች የራሳቸው አኗኗርና ባሕል ስላላቸው የግድ እኛ ቤት መጥተው ባለቤት እንዲሆኑ ባንታገልም የፈለገ ቋንቋዬ ሕዝቤ ያለ የመሔድ መብቱ የተፈቀደ ነው።
    ** በእርግጥ ህገ መንግስቱ ለግለሰቦች መብት ያለው ቦታ ትንሽ ነው፡፡ ለብሄርተኝነትና ለብሄር ጉዳይ ትኩረት የሚሰጥ ህገ መንግስት ነው፡፡(ለዚህም ነው ዜግነት አልባ መንጋ ብመፈጠሩ የውጭውን ይሚያስመኘው እንጂ የቋንቋ መብዛትና ማነስ አደለም…ቢሆንማ ኖሮ ኦሮሞ ላልፉት ፳፮ ዓመት በክልሉ በቋንቋው ተናግሮ ምን አተረፈ? አሁንም በእግሩ ይሄዳል የአልቅት ወሃ ይጠጣል..እየጨፈረ ድዱን ይሚያሰጣ የበይ ተመልካች ሆኖ ድንዝዟል፡ ባትከልሉና ባትከለክሉት የመብቱ ጠያቂና ተወዳዳሪ ሆኖ ይለወጥ ነበር። ይሄ ብሄርተኝነት የህዝቦች ማህበራዊ ግንኙነት እየዳበረ ሲሄድ ተቀይሮ፣ ብሄርተኝነቱ እየላላ ሄዶ፣ ግለሰባዊ እሳቤና አንድነታዊ አስተሳሰብ ሊጎለብት ይችላል።”አማርኛ ቋንቋው ምን አጠፋ? ሕገመንግስቱ አብለቶ አባይ ነው። አብዛኛው ተመችቶታል ፈንጥዟል…አሁንም ምፎከሪያ ሆኗል (የተወያየበት ማነው?)
    ******************!
    “በሀገሪቱ የተነሱ ውዝግቦች ከህገ መንግስቱ ጋር የተገናኙ ናቸው”
    ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ፖለቲከኛ)
    “ህገ መንግስቱ በትክክል ተግባራዊ አልተደረገም፤ ህገ መንግስቱ እንደገና መታየት አለበት”
    ” ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱን ስናፀድቅ ህዝቡ በቀጥታ አልወሰነበትም፡፡ በተወካዮች በኩል ነው የወሰነው፡፡
    በፖለቲካ ፓርቲዎች ተናጥላዊ ድርድር ብቻ ህገ መንግስት አይሻሻልም፡፡ ሊወያይበት የሚገባውም ህዝቡ ነው። ህገ መንግስቱ ይሻሻል አይሻሻል የሚለው ሀሳብ በራሱ፣ ለህዝበ ውሳኔ መቅረብ አለበት፡፡” (፳፱ ተወካዮች ተሳተፉ ማለት የማን? ምን? በማን ተሰየሙ? ምን ተቃወሞና ማሻሻያ አቀረቡ የሚለው ለሕዝብ አልተገለጸም…ስዩም ተሾመ “ህገ መንግስቱ በወቅቱ በውይይት ነው የፀደቀው፡፡”የሚለን ሌንጮ ለታ ከኦነግ ፅፎ መለስ ዜናዊ ከህወአት ስላፀደቀው ነው?
    *************!
    “ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ህዝቡን ማወያየት ያስፈልጋል”
    ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ (ፖለቲከኛ)
    “በመጀመሪያ እየተደረገ ያለው ድርድር ላይ ኢህአዴግ በቀና መንገድ ገብቶበታል ብዬ አላምንም። “ሀገሪቱን ወደ አለመረጋጋት የከተታት ምንድን ነው?” ተብሎ ተጠንቶ፣ ምክኒያቶቹ ቅደም ተከተል ተሰጥቷቸው መቅረብ ነበረባቸው፡፡ ህገ መንግስቱን በተመለከተም መነጋገር የምንችለው ከዚህ በመነሳት ሊሆን ይገባው ነበር፡፡” አጀንዳው ሲቀረፅ ፓርቲዎች ተደረደሩ እንጂ ሊደራደሩ አደለም ምክንያቱም አልተወያዪም ልዩነታቸው የፖልቲካ ይሁን፡የሥልጣን ሽሚያ/መጋራት፡ የሕገመንግስት የሥረዓት ለውጥ ለማምጣት ይሁን አልታወቀም። ህወአት/ኢህአዴግ እናንተ የምታወቁትን ሁሉ አወሩልኝ እኔ አስፈጽመዋለሁ አለ…ቋንቋንና ልዩ ጥቅማጥቅምን አጮሁት እሱ ፈታው አሁን እነሱ ማጯጯህ ያዙ…”የ፹፭ ከመቶ የኢትዮያ ሕዝብ ገብ(በ)ሬ ነው ችግሩ በኢህአዴግ ብቻ እንዲፈታ ገበሬውም ህወአት/ኢህአዴግ ይግደለኝ ሲል ቃል ሰጥቷል ስለዚህ ተቃዋሚዎች አኡንም ወደፊትም ምንም የመግቢያ ቀዳዳና ፋይዳ የላችሁም ” በረከት ስሞኦን
    ************!
    “ከህዝቡ በስተቀር ማንም ህገ መንግስቱን መንካት አይችልም”
    ዶ/ር ንጋት አስፋው (ፖለቲከኛ)
    “አንድ ህገ መንግስት፤ የሀገር ህግ ሊሆን የሚችለው፣ ከዳር እስከ ዳር የህዝብ ተወካዮች በሙሉ ያሉበትና በህግ ባለሙያዎች ተቀምሞና ተዘጋጅቶ፣ ህዝቡ በየደረጃው ተወያይቶበት የሚፀድቅ ሲሆን ነው፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ስናይ፣ ህግ የሚያወጣው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው። የሚያስፈፅመው መንግስት፣ ተርጓሚው የፍትህ አካላት ናቸው፡፡
    እዚህ ላይ የኔ ጥያቄ፤ አሁን በእርግጥ ትክክለኛ የህዝብ ተወካይ አለን ወይ የሚለው ነው። አለ! ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ሳይሆን የኢህአዴግ አባላት ተወካዮች ነው ያለው፣ የሚል እምነት አለኝ። መቶ በመቶ በዚህ ስርዓት የተያዘ ነው፡፡ ህግ የሚያወጣው፣ የሚያስፈፅመው፣ የሚተረጉመው ራሱ ስርአቱ ነው፡፡በአንድ ሳንባ የሚተነፍስ የፖለቲካ ስርአት ነው ያለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህን ህገ መንግስት ከምልአተ ህዝቡ በስተቀር ማንም ተወካይ ሊነካው አይገባም ባይ ነኝ፡፡”
    ታዲያ ይህ ተቃዋሚ/ተቋቋሚ የህወአት/ኢህአዴግ አጋር፡ ተለጣፊ፡ ጋሻ ሻግሬ፡ ተፂላ ፓርቲ ይሚባሉ ሁሉ የሚያወሩት ያው፡አንድና አንድ አደለምን? ለምን ፬ ወሳኝ ፓርቲ አድርገው ወጥና ግልጽ አጀንዳ የላቸውም? ተጠቃሚና ጠቃሚ ልዩ የሕገመንግስት ጥቅማጥቅመኞች….!
    ***************!
    “ህገ መንግስቱ ለውይይትና ድርድር መቅረብ ይችላል”
    አቶ ገብሩ አስራት (ፖለቲከኛ)
    “የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ይቀድማል፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለበት ደግሞ የፖለቲካ ምህዳር መስፋት አይታሰብም፤ ህዝቡ ያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ህገ መንግስቱን ማሻሻል የሚያስፈልጉ ከሆነ፣ ህገ መንግስቱ ለምን አይሻሻልም? ጠባብና ጽንፈኛ እያለ የሚቦጥርና የሚወጠር ካድሬ አዋጁ ሲነሳ መልሶ መኮማተሩ/መተንፈሱ አይቀርም! ጥቅማጥቅምን ለቀቅ ሲደረግ ይረግብ ይሆን!? **የፖለቲካ ምህዳር ሲጠብ ፅንፈኝነትና ነውጥ ነው እያየለ የሚመጣው፡፡ቀድሞ መነጋገር፡ መምከርና መደማመጥ ቢኖር አመፅ ባልኖረ….እነዚህ ከተለወጡ በኋላ ህዝቡ ራሱ በሚፈልገው መንገድ ማሻሻልና መለወጥ ይችላል፡፡”
    *** የታፈነ ሕዝብ ምን ተናግሮ ነው ጥያቄው ገብቷቸው ለድርድር የተደረደሩት!?
    ____”ሕገመንግስት ለሕዝብ መጨቆኛና ማስፈራሪያ ሳይሆን፡የሕዝብ ድምፅ የተሰጠው መንግስት በሕጉ ላይ በተፈቀደለት የሥራ ዘመኑ፡ እራሱን ለሕግ የበታች አድርጎ ሊያስተዳድርበትና ከሕገመንግስቱ ሥር ሆኖ የተሰጠውን የምርጫ(የማስተዳደሪያ ግዜ የሕገመንግስቱን አንቀፅና ትርጓሜዎችን ሳያዛባ፡ ሳይጨምርና ሳይቀንስ እንዲመራመበት ከሚያወጣቸው ሕጎች ድንብና መተዳደሪያዎች ሁሉ የበላይ ሆኖ የሚያገለግል የኢትዮጵያዊ ዜጋ (ሕዝብ)ሰነድ ነው።አራት ነጥብ።

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    July 8, 2017 03:46 am at 3:46 am

    These politicians are damaging the theory; constitution couldn’t be forwarded to the people like referendum . Any constitution is drafted by the representative of the people. The EPRDF members of the drafters were correct.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule