እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ! … [Read more...] about እግርና ጫማ
Archives for May 2016
“እንተያያለን አስክሬንህ ነው የሚወጣው” የህወሃት አሸባሪዎች
* "በክፉ ጊዜ የከዱን አሉ፤ ለእነሱም ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው" "የመጣሁት ከትግል እንጂ ከሽርሽር አይደለም" ይላሉ ዳንኤል ሺበሺ! የቀድሞው አንድት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊና የደቡብ ቀጠና ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ላለፉት 22 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ከእሥር ተፈትተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ አየር ጤና አካባ በተለምዶ ቻይና ካምፕ በተሰኘው የአቶ ዳንኤል መኖሪያ ቤት ተገኝታ በእስር ቆይታቸው ስላሳለፏቸው ነገሮች፣ ስለወደፊት ሀሳባቸውና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ እንዴትና በምን ሁኔታ ነበር የተያዙት? የተያዝኩት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በተለምዶ ጀርመን አደባባይ … [Read more...] about “እንተያያለን አስክሬንህ ነው የሚወጣው” የህወሃት አሸባሪዎች
የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የጀርመን ኤምባሲ የትግርኛ ቋንቋን ቁልፍ ቅድመ መስፍርት የሚያደርግ ክፍት የስራ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ለሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አወጣ። ትግርኛ ዋና መስፈርት የሆነበት ምክንያት ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የኤምባሲው ተግባር የኢትዮጵያውያንን እኩልነትን ከህወሃት በላይ ያንቋሸሸ ነው ብለውታል፡፡ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ ይጠበቃል። ኢምባሲው በድረገጹ ሜይ 4 ቀን 2016 ያወጣው ማስታወቂያ የሚፈልገው ባለሙያ የቪዛ ማመልከቻ ስራን የሚያመቻች፣ የሚያረጋግጥ፣ ቪዛ ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የቃልና የጸሁፍ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ የቪዛ ክፍያን የሚፈጽምና የመዝግብ አያያዝ ስራን የሚያከናውን እንደሆነ ያረጋግጣል። የስራው ቦታ ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ማስታወቂያውን የተመለከቱ ወገኖችን ያነጋገረውም … [Read more...] about የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
“አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዜጎች “አሸባሪ” እየተባሉ በሚታፈኑባት፣ በሚገደሉባት፣ የደረሱበት በሚጠፉባት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ ሰሞኑን “88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች” “ጠፍተዋል” እየተባለ በሰፊው እየተናፈሰ ከመሆኑ አልፎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህወሃት ሹመኛ መኩሪያ ኃይሌ በህወሃት ለተሰየመው የኢህአዴግ ምክርቤት (ወግ እንዳይቀር “ፓርላማ” በሚባለው) ቀርበው ስለነዚህ “ጠፉ” ስለተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ምንም አስተያየትም ሆነ ዘገባ ሳያቀርቡ እንደ ካኔተራ ውልቅ ብለው ሊወጡ ሲሉ፤ ምናልባትም ቤቶቹ የጠፉባቸው “የፓርላማው” አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፤ “የገባህበት ገብተህ ታመጣታለህ” የሚል እንደምታ ያለው ቀጭን ትዕዛዝ ለመኩሪያ ሰጥተው ሸኝተዋቸዋል፡፡ ከዜጋ እስከ ወርቅ የሚጠፉበት ህወሃት አሁን ደግሞ ብዙ ኮንዶሚኒየሞች ጠፍተውበታል፡፡ ወሮታው ምን እንደሆነ … [Read more...] about “አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500 ዓመተ ዓለም አንድ የነጻነት መሪ ነበር። በዘመናዊ የማኔጅመንት ትምህርት ውስጥ የስራ ክፍፍልን የፈጠረና መሰረት የጣለ ትልቅ ሰው ነው። ይህ ሰው የተወለደው በጭንቅ ሰዓት ነበር። እስራዔላውያን በግብጽ ምድር በባርነት ቀንበር ስር ባሉበት ሰዓት። ንጉስ ፈርዖን የእስራዔላውያንን የጥበብ ስራዎች፣ የሚሰሯቸውን ጡቦች ቢወድም ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ከመጡ መንግስቴን ይነጥቁኛል ብሎ ስለፈራ ህጻናትን ሁሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ የተላለፈበት የጨለማ ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የተወለደው ይህ ሰው ወላጅ እናቱ በዓባይ ወንዝ ላይ በእንዲት ቅርጫት ኣሳፈረችው። መደበቋ ነው። በርግጥም ከወታደሮች ሰይፍ መትረፍ ችሏል። ለሶስት ወራት በዚህ ሁኔታ ወላጅ እናቱ ደበቀችው። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን ልእልት እየችው። ልእልት ይህን ህጻን ስታየው ያማረ ነበርና ቤተመንግስት … [Read more...] about ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!
«የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር!
ከዛሬ ሰማኒያ ዓመታት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ከትግራይ እና ከኤርትራ ምድር በበቀሉ ባንዶች አጋዥነት በፋሽስት ጣሊያኖች ጦር ማይጨው ላይ ድል ሲመቱ «እሺ፣ አሜን፣ እንገዛለን» ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። ራሣቸው ፋሽስቶችም እንዳመኑት፥ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በጉራጌ፣ በጅባት እና ሜጫ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩት አርበኞች በመረጧቸው የጎበዝ አለቆቻቸው እየተመሩ፣ ለአምሥት ዓመታት የፋሽስት ጣሊያንን ጦር ከእነ ባንዳ ግሣንግሱ መውጫ መግቢያ አሣጥተውታል። ከዚያም ከየካቲት 1933 ዓም ጀምረው ጀግኖች አርበኞቻችን ባደረጉት የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ልክ የዛሬ 75 ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓም በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ መሪነት በድል አድራጊነት ዋና ከተማችንን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር … [Read more...] about «የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር!
ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!
የመን ትነድዳለች ኢትዮጵያውያን ግን ወደዚያው ያቀናሉ። ሶማሊያ ዋስትና ቢርቃትም ወገኖች ሊረማመዱባት አሁን ድረስ ምርጫቸው ናት። በሲና በረሃ ሰው በቁሙ ይበለታል። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሁንም አማራጭ መንገድ ነው። ሲኦል መሆኑ እየታወቀ እህትና ወንድሞች ወደ አረብ አገር ይተምማሉ። ኬንያን፣ ታንዛኒያን፣ ዛምቢያን፣ … አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ቁጥራቸው ሲቀንስ አይታይም። በደቡብ አፍሪካ ወገኖች በእሳት ሲቃጠሉና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ማየት ወደዚያ የሚደረገውን ጉዞ አልቀነሰውም። ለምን? በቀይ ባህርና በሜዲትራንያን የሰመጡ ወገኖች መርዶ ሳያሰልስ ሌሎች መሰመጥ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን እያወቁ ይገቡበታል። ሊቢያ የታረዱትን ወገኖች እያዩ ሌሎች ወደ ሊቢያ ለማቅናት አያቀማሙም። ለምን? በኩባ ቪዛ ተነስተው መከራቸውን ለወራት በበረሃ የሚያሳልፉ ወገኖች ቁጥር ... ስንቱ … [Read more...] about ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!
“በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከኅሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል”
* “... እህታችን ታሪኳን ስትነግረኝ፣ ለፍትህ እንደምትመጥን አመንኩ” ኦባንግ “... የተረሳሁ ነበርኩ፡፡ የደረሰብኝ ግፍ ጠባሳ የሚያልፍ መስሎ አይታየኝም ነበር። ግን ብርሃን ሆነልኝ። በየትኛውም ወቅት ልረሳው የማልችለው ኦባንግ ሜቶ ችግሬን ዝቅ ብሎ አደመጠኝ። ና ባልኩት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ፍትህ ደጅ እንድቆም ረዳኝ። ስለ እሱ ለመናገር ቃላቶች የሉኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ያለመድሃኒት አልተኛም ነበር። ዛሬ መድሃኒት ከመቃም ተገላግያለሁ። በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከህሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል። … በየቦታው ፍትህ የተዛባባችሁ ወገኖቼ ዝም አትበሉ። ፍትህ በደጃችሁ ነው። ግን ተናገሩ። ሆን ብላችሁ ያላጠፋችሁት ጥፋት አያሳፍራችሁምና ራሳችሁን ከዝምታ ድባብ አላቅቁ...” ይህ ስሟ እንዳይነገር ከጠቀችው እህት አንደበት ነው። “... እኔ የሰራሁት ሥራዬን ነው። … [Read more...] about “በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከኅሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል”