ዜጎች “አሸባሪ” እየተባሉ በሚታፈኑባት፣ በሚገደሉባት፣ የደረሱበት በሚጠፉባት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ ሰሞኑን “88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች” “ጠፍተዋል” እየተባለ በሰፊው እየተናፈሰ ከመሆኑ አልፎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህወሃት ሹመኛ መኩሪያ ኃይሌ በህወሃት ለተሰየመው የኢህአዴግ ምክርቤት (ወግ እንዳይቀር “ፓርላማ” በሚባለው) ቀርበው ስለነዚህ “ጠፉ” ስለተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ምንም አስተያየትም ሆነ ዘገባ ሳያቀርቡ እንደ ካኔተራ ውልቅ ብለው ሊወጡ ሲሉ፤ ምናልባትም ቤቶቹ የጠፉባቸው “የፓርላማው” አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፤ “የገባህበት ገብተህ ታመጣታለህ” የሚል እንደምታ ያለው ቀጭን ትዕዛዝ ለመኩሪያ ሰጥተው ሸኝተዋቸዋል፡፡
ከዜጋ እስከ ወርቅ የሚጠፉበት ህወሃት አሁን ደግሞ ብዙ ኮንዶሚኒየሞች ጠፍተውበታል፡፡ ወሮታው ምን እንደሆነ ባይታወቅም ሰሞኑን “የአፋልጉኝ” ማስታወቂያ ሳያወጣ አይቀርም፡፡ (ጎልጉል – ፎቶ: Addis Fortune)
Yetayal gudooo says
ቤቶቹ እራሳቸው እንደ ኢሃድግ መሰረት የሌላቸው ቢሆኑ ነዋ ። አለበለዚያማ እንዱት ቤቶች ጣራና ግድግዳ እያላቸው ይሰረቃሉ? በዘመነ ኢሃድግ የማይሰማ ነገር የለም ዉሾች !!!!!!!!!!!
በለው! says
” የህወሃት /ኢህአዴግ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ፪ ሚሊየን የአማራ ሕዝብ ከጠፋበት ፹፰ ቤት ምን አላት?”
ምን አልባት የቆጠራው ዕለት ቤቶቹ ፀሐይ ሊሞቁ ጣሪያ ላይ ወጥተው ይሆን!?