በቅርቡ በዚህ በምኖርበት አገር አንድ የልደት በአል ላይ ተጠርሼ ሄጄ ነበር፡፡ በዚሁ ዝግጅት ላይ ከዝህ በፊት በአካል አግኝቼው የማላውቀው የዚሁ አካባቢ ከበርቴ ጋር ስጨዋወት ነበር፡፡ በተለይ ከአመታት በፊት በኢትዬጵያ ታስርው ስለነበሩት የስዊድን ጋዜጠኞች ልቤ እስኪጠፋ ጠየቀኝ፡፡ እኔም የምችለውን ያህል ለመመለስ ሞከርኩ፡፡ ስንሰነባብት ያለኝ ነገር ግን ሰሞኑን በኢትዬጵያ ዙሪያ የሚሰማኝን ውጥንቅጥ ስሜት ቅልብጭ አድርጎ ገለጠልኝ። ምን አለኝ መሰላችሁ... "ሄዶ ኢትዬጵያ"። አለፍ ብሎም ስሜን በወጉ መጥራት እንደከበደው ነገረኝ። በዚህ በስዊድን አፍ "ሄዶ (hej då)" ማለት ቻው ወይንም ደህና ሁን/ሁኚ እንደማለት ነው። ከዚሁ ቤት እየወጣሁ ቃሉን በውስጤ ደጋገምኩት... ሄዶ ኢትዬጵያ ... ቻው ኢትዬጵያ ... በተመስጦ አሰብኩት። አዎ ልክ ነው። አሁን ሰለ ሃገሬ የሚሰማኝ … [Read more...] about “ሄዶ ኢትዬጵያ (hej då Ethiopia)”
Archives for April 2016
እስከመቼ ኢትዮጵያ!
የማይነጥፈው የኢትዮጵያ ማህፀን፤ ከዓመት ዓመት፣ ከገዢ ገዢ ካምባገነን አምባገነን፤ ሳይደክም ሳያርፍ የሚጎርፈው፣ ሚሊዮን ሃያ ሁለት አፍርቶ ነበር በትውልዴ እኔ ሳውቀው። አሁንማ፣ አሁንማ፣ ካራት እጥፍ በላይ አድጓል አሉኝ፤ ደስታ በፊቴ ሲረጩልኝ። (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about እስከመቼ ኢትዮጵያ!
ማዕረግ እንስጣቸው!
ሰው በሕይወት ሳለ መቼም ማድነቅ አንወድ ማሻሻል አለብን ይሄን ነገር የግድ እኚህ ጠንካራ ሰው ፕሮፌሠር መስፍን ለራሳቸው ቢሆን የለፉት እስካሁን ሀብት ከሥልጣን ጋር በእጃቸው ጨብጠው በታዩ ነበረ ከሁሉ ሰው በልጠው ነገር ግን እኚህ ሰው ለሀገር ሲለፉ ምንም ሳይኖራቸው ዕድሜአቸውን ገፉ ሆኖም እንደሳቸው ከህሊናው አድሮ መኖር ክብር አለው እየበሉ ሽሮ ጥንትም ሆነ አሁን በተሳሳተ ሀገር መቼም ድኖ አያውቅም አዋቂ ከችግር ገዢን የማይፈሩት በዕድሜ ዘመናቸው እኮ ለምንድነው ብለውም ቢሏችሁ ህሊናው የጸዳ ያልፈጸመ በደል እስከዛሬ ድረስ መቼ ፈርቶ ያውቃል ብላችሁ መልሱ ይሄን ተናገሩ ሌላ ምንም አይደል አትጠራጠሩ እኚህን ታላቅ ሰው እንያዛቸው በወግ በዕድሜ ዘመናቸው ክብርን አንንፈግ የሳቸው ብቸኛ … [Read more...] about ማዕረግ እንስጣቸው!
የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
ጥያቄ አለኝ፥ የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው? ዛሬ ያላቅሜ አንድ ጥያቄ ማንሳት ከጅያለሁ። ለነገሩ ዶክተር ያልተጠየቀ ማን ይጠይቃል? እናም ዶክተርን ልጠይቅ ነው። ዶክተር መሳይ በኢትዮጵያ የዘውግን ፖለቲካ የጀመረው ማነው? ዶ/ር መሳይ ከበደ፥ የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ፥ በሚል ርእስ በአንድ መድረክ አቅርቤው ነበር ያሉትን ፅሁፍ በዚህ ድረ-ገፅ ላይ አውጥተው አስነብበውናል። እንደውነቱ ከሆነ በመድረኩ ተገኝተን ፅሁፋቸውን ለመከታተል እድል ላላገኘን ሰዎች በረከቱን ስላሳተፉን አመሰግናለሁ። ግን ጥያቄ አለኝ። ለጥቂቶች ስውር የስልጣን ጥም ማርኪያ፣ ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ደግሞ የህልውና ፈተና የሆነውን የዘውግ ፖለቲካ በዚያች አገር የተከለው ማነው? ህወሃት ወይስ አማራ? ለችግሩ መፍትሄው ክልሎችን ማጥፋት ሳይሆን ራስ ገዝ ማድረግና ስልጣን መስጠት ነው … [Read more...] about የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ከ25 ዓመታት በፊት አንድ የኮሌጅ ዲፕሎማ የነበረው አስተማሪ ሲቀጠር የመነሻ ደመወዙ 347 ብር ነበር። ይህን ገቢ በወቅቱ ከነበረው የዶላር ምንዛሬ አንጻር ስናየው 173.5 ዶላር ይመዝን ነበር። ይህ አስተማሪ ገና ሲቀጠር የቀን ገቢው 5.8 ዶላር ነበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ነበር። ከ25 አመት “እድገት” በሁዋላ በህወሃት ኢህዓዴግ ዘመን አንድ የኮሌጅ አስተማሪ ዲፕሎማውን ይዞ ሲቀጠር 1663 ብር ቢከፈለው አሁን ባለው ምንዛሬ ሲታይ 77.3 ዶላር ያገኛል። ይህ ማለት የቀን ገቢው በዶላር 2.57 ሳንቲም ነው ማለት ነው። ይህ ማለት የደርግ ጊዜው አስተማሪ ደመወዝ ከህወሃት ኢህዓዴግ ጊዜ አስተማሪው ደመወዝ ከሁለት እጥፍ በላይ ይበልጣል ማለት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የድህነት ወለል የሚባለው ሁለት ዶላር አካባቢ ሲሆን ይህ በህወሃት ኢሃዴግ ዘመን የኮሌጅ ዲፕሎማ የያዘው አስተማሪ … [Read more...] about የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!
ጋምቤላ ውብ ምድር፣ ጋምቤላ የተፈጥሮ ባለጸጋ፣ ጋምቤላ ድንግል መሬት፤ ጋምቤላ ያላትን የማትበላ፣ የተረገሙ የሚመሯት፣ የደም መሬት፣ የዕንባ ምድር፤ ጋምቤላ የምትዘረፍ ምድር፣ ግፍ የተትረፈረፈባት የግዞት መሬት፣ የደም አውድ፣ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ “አካላችን”፤ ጋምቤላ ያላቸውን የማይበሉ ህዝቦች፣ ባላቸው ሃብት የተነሳ የግፍ መከራ የሚጋቱ ምስኪን ወገኖች የሰፈሩባት ገነተ ሲኦል፤ ተቆርቋሪ አልባ “ኢትዮጵያኖች” ፍትህን ስትናፍቁ ከሁልጊዜውም በላይ በከፋ ሃዘን ተመታችሁ!! አዎ፣ የጎልጉል ዝግጅት ክፍልን ጨምሮ ዜጎችን ያቃጠለው ዜና ባልተለመደ መልኩ የተበሰረው በህወሃት ንብረት ራዲዮ ፋና አማካይነት ነው። ባለፈው አርብ የተሰማው ክፉ ዜና እነዚያ ለቱሪዝም ማስታወቂያነት ብቻ የሚፈለጉት ወገኖቻችን በድንገት ስለመጨፍጨፋቸው ነው። ከ240 በላይ እናቶችና ህጻናት በጅምላ … [Read more...] about ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!
Shengo’s Press Release Regarding the US Senate Resolution
Following the European Parliament’s Resolution of January 21, 2016 on the situation in Ethiopia “strongly condemning the recent use of excessive force in Oromia and in all Ethiopian regions,” Shengo expressed its appreciation to the EU and called upon the Congress of the United States to take a similar stand. In this regard, we recognize the concerted and relentless campaign made by Ethiopian civil society, political, spiritual and professional groups as well as individuals. The United States … [Read more...] about Shengo’s Press Release Regarding the US Senate Resolution
ለንቅልፍህ አትሳሳ
የእንቅልፍ ምቀኛ (ከዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ) እወራረዳለሁ በአንድ ሚሊዮን ብር ሸለብ ሲያደርግህ ነው ስልክህ የሚል ቅርርር! ሚያዝያ 9፣ 2008 ዓ.ም. (አፕሪል 17፣ 2016 እ.ኤ.አ.)፤ ምንጭ፡- ፌስቡክ ምላሽ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለንቅልፍህ አትሳሳ ወለላዬ ይከሰታል አዎን! ልክ ነህ ዶክተሬ የት ይጠፋል ብለህ የሚል ፍቅሬ ፍቅሬ ደግሞም ትክክል ነው እንዳተ ለሚጽፍ በዚህ በአሁን ጊዜ ምን ይሠራል እንቅልፍ ላገራችን ችግር ስላለው አበሳ ካልተጻፈ በቀር በፍቅሬ ቶሎሳ ማን ይመጣል ብለህ ሁሉም እኮ አለቁ ካገሪቷ ጠፉ በሞት ተነጠቁ ቢቻልማ ኖሮ እነሱን መቀስቀስ እንኳን ስልክ ማጮህ ባናወጥነው በተኩስ ቢነሳማ ኖሮ ስልክ በማንጫረር በአሉን በጠራን ከዋጠችው ምድር ባስነሳነው ነበር ፀጋዬን … [Read more...] about ለንቅልፍህ አትሳሳ
ብክነትና ምክነት
በኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ የሚያባክን ማን እንደሆነ እናውቃለን። ጊዜም የሚያባክነው ማን እንደሆነ ሳናውቅ አንቀርም። እንዲሁም ወንድና ሴት እንደየተፈጥሯቸው እንዳይወልዱ የሚያመክናቸው ምን እንደሆነ አሳምረን እናውቃለን። አንናገርም እንጂ። ምሁራንንስ የሚያባክንንና የሚያመክን ማነው? ጎበዝ ማለት ይህን የሚያውቅ ነው። እኔም ማወቅ የምፈልገው ያገሬን ምሁራን የሚያባክንብኝና የሚያመክንብኝ ማን እንደሆነ ነው። ሰሞኑን ያዲስ አበባው መንግስት ቀለም ቀለም ሲሸተው ጊዜ እኔንም እንዲሁ ቀለም ቀለም ስለሸተተኝ ስለምሁራን ብንጫወት ምናለ ብዬ ለዛሬ ቁም ነገሬ እንዲሆን መረጥኩት፤ የኢትዮጵያ ምሁራን ጉዳይ፤ በተለይ ያቋማቸውና የጥቅማቸው ጉዳይ። በይበልጥ ደግሞ እንዲያው እንደዋዛ የመባከናቸው ነገር። ባክነዋል እንዴ? ካላችሁ መልሴ እንክት ነዋ! የሚል ነው። ላስረዳ። የምናገረው ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about ብክነትና ምክነት
ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም
የአንድ አገር ድንበር የሚደፈረው፣ ሕዝቡ ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጠው የአገሩን ድንበርና የሕዝቡን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል በሕዝብ፣ ለሕዝብ፣ የሕዝብ የሆነ መንግሥት በሌለበትና ለጸረ ሕዝብ ሃይሎች አመቺ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በሃይል የጨበጠው የጎሳ ስብስብ በተደጋጋሚ የአገራችንንና የሕዝባችንን ጥቅምና ደህንነት ለአደጋ እያጋለጠ እራሱም የአደጋው ፈጣሪ እየሆነ መቆየቱን የሥልጣን ዘመን ታሪኩ ይመሰክራል። ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም