• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብክነትና ምክነት

April 21, 2016 01:32 am by Editor Leave a Comment

በኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ የሚያባክን ማን እንደሆነ እናውቃለን። ጊዜም የሚያባክነው ማን እንደሆነ ሳናውቅ አንቀርም። እንዲሁም ወንድና ሴት እንደየተፈጥሯቸው እንዳይወልዱ የሚያመክናቸው ምን እንደሆነ አሳምረን እናውቃለን። አንናገርም እንጂ። ምሁራንንስ የሚያባክንንና የሚያመክን ማነው? ጎበዝ ማለት ይህን የሚያውቅ ነው። እኔም ማወቅ የምፈልገው ያገሬን ምሁራን የሚያባክንብኝና የሚያመክንብኝ ማን እንደሆነ ነው።

ሰሞኑን ያዲስ አበባው መንግስት ቀለም ቀለም ሲሸተው ጊዜ እኔንም እንዲሁ ቀለም ቀለም ስለሸተተኝ ስለምሁራን ብንጫወት ምናለ ብዬ ለዛሬ ቁም ነገሬ እንዲሆን መረጥኩት፤ የኢትዮጵያ ምሁራን ጉዳይ፤ በተለይ ያቋማቸውና የጥቅማቸው ጉዳይ። በይበልጥ ደግሞ እንዲያው እንደዋዛ የመባከናቸው ነገር። ባክነዋል እንዴ? ካላችሁ መልሴ እንክት ነዋ!   የሚል ነው። ላስረዳ። የምናገረው ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ምድር ስላሉ ምሁራን መሆኑን ልብ በሉልኝ። የውጪዎቹማ  እንዲያው እንዳይቆጡኝ ድምፃችሁን ዝቅ አድርጋችሁ አንብቡልኝ እንጂ እነርሱማ የባከኑት ገና ዱሮ ካገር ከወጡበት እለት ጀምሮ ነው።

ታዲያ ምሁር ማነው? እስከ ስንተኛ ክፍል የተማረ ነው? ምናምን አትበሉኝ። ከመንግስት ጋር የሚያጣላ ጥያቄ አልወድም። በቃ ምሁር። ይገባችኋል። ለምሳሌ ባለፈው በአሜሪካ ድምፅ አማርኛው አገልግሎት ቀርበው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ይዞታ ላይ አስተያየትና ትንተና የሰጡትን ከአዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ የህግ፣ ሶሲዮሎጂና የፖለቲካ ትምህርት ምሁራን አይነት ማለት ነው። ስም አልጠራም።

ምሁራን በሰው ልጅ እድገት ታሪክ ውስጥ የተጫወቱትን ሚና መዘርዘር ጊዜ ስለሚፈጅ ብቻ ሳይሆን እኔም ስለማላውቀው አናነሳውም። ግን አለምን ለውጠዋል፤ አቅጣጫዋንም ወስነዋል፣ ሲባል ስለሰማሁ እኔም እንዲያ ብንል ዋስ ጥራ የሚለን ያለ አይመስለኝም። በተለይ ከ18ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮና ምናልባትም ከዚያም በፊት በየዘርፉ የተቀመሩት ሳይንሳዊ ንድፈሃሳቦችና ግኝቶች ሰውን ዛሬን እንዲመስል አድርገውታል። በተለይ በመንግስታዊ ያስተዳደር ጉዳይና የፖለቲካ ጥያቄዎች አቅጣጫ እንደየሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ አወንታዊም አሉታዊም ሚና ተጫውተዋል። ባንፃሩ ደግሞ ምንም ፋይዳ ያለው ስራ ሳያከናውኑ እንዲያውም ለክፉ ገዢዎች መሳሪያ አቀባይ ሆነው ያለፉበት ታሪክም ይኖር ይሆናል። መሰረታዊ ጥያቄው የቱ ሀገር በምን አኳኋን ተጠቀመባቸው የሚለው ነው። የት ባከኑ? የትስ መከኑ? በማለት መጠየቅ ማለት ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሁራን ጠቅመውናል? በፖለቲካው ምዳ ሚና ኖሯቸው ካልጠቀሙን ባክነዋል ማለት ነው። ምናልባትም መክነዋል።

በኔ አስተያየት በተለይ ባለፉት 40 የምጥ አመታት ምሁራንን ሳንጠቀምባቸው ባክነዋል። ያባከናቸውም መንግስት ነው፤ ያለውም የሄደውም። ደርግ ከፊሉን በመግደል ቀሪውን ደግሞ በውድም በግድም አባሪ በማድረግ እውቀታቸውን አባከነው። ብዙዎቹም የሀገራቸው ጉዳይ ሆዳቸውን እያመማቸውና አንጀታቸው እያረረ በምሁርነት ካባቸው ላይ መንግስታዊ መለዮ ደርበው ከእገሌ ጋር ወደፊት እንዲሉ ተገደዱ። ቀሪዎችም ሲያቀብጣቸው (ወይም ሲፈርድባቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ለምን አሉና ተገደሉ። ባከኑ ማለት ይሄ አይደል? ወግነው የተረፉትም ተቃውመው የጠፉትም ያው ባክነዋል።

ዛሬስ? ዛሬም ቢሆን ታሪክ እምብዛም የተለወጠ አይመስልም። እንደመጥምቁ ዮሃንስ በበረሃ ያለሰሚ የሚጮኹ ሀቀኛ ምሁራን መኖራቸው ሳይካድ ብዙሃኑ ግን ወይ ለሆዱ ያለዚያም ለባለክንዱ አድሯል። ቀሪውም ጭልፊት እንዳየች ጫጡት በየተቋሙ ጎሬ አድፍጧል። የቀናውም ይብላኝልሽ ሀገሬ ብሎ ካገር ፈርጥጧል። እናም ሁሉም ባክነዋል።

ልማታዊ ምሁራኑ ሳይንስ፣ መንግስትና እድገት አንድም ሶስትም ናቸው በሚል ተጠምቀው 11 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ በሚያጣጥርባት ኢትዮጵያ 11 ጊዜ አድገናል ይሉናል። ማንም ሰው በማንነቱ መብት አለው የሚለውን የቀለም ትምህርት በላፒስ አጥፍተው ማንነት በሞት በሚያስቀጣባት ሀገር የብሄር መብት ተከበረ ይሉናል። ታዲያ ከዚህ በላይ ብክነትና ምክነት ከየት ይመጣል?

እዚህ ላይ መቼም አንተስ በኢህአዴግ አፍንጫ ስር ብትሆን ኖሮ ውዳሴ መንግስትን ከመድገም ሌላ ምን ታደርግ ነበር የሚል ተፈታታኝ አንባቢ መኖሩ አይቀርም። እኔም ባልሆን እውነቱን ተናግረው እመሸበት የሚያድሩ እውነተኛ የቀለም ልጆች መኖራቸውን አሌ የምንል አይመስለኝም። ያመኑበትን ተናግረው የለት እንጀራቸውን ያጡ ግን ደግሞ የቀለም ቃልኪዳናቸውን የጠበቁ ጀግና ምሁራን መኖራቸውን ዋቢ ጠቅሶ መከራከር ይቻላል። ሌላው ቢቀር የባለጊዜ ፖለቲከኞች ቃለአቀባይ በመሆን ሳይማር ባስተማረን ወገን ላይ ባላስተማረን ትምህርት በሃሰት ከምንፈርድ እሰየው ባያሰኝም እንኳን ጎመን በጤና ያሉትን ጎራ መቀላቀል ሳይሻል ይቀራል። ለነገሩ እሱም መፈቀዱ እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

አንድ በንጉሱ ዘመን ሹመት የተሰጠው ሰው ሹመቱን አልፈለገው ኖሮ ንጉሱ ፊት ቀረበና እባክዎ ጃንሆይ፣ ሹመቱ ቀርቶብኝ አርሼ ልብላበት ቢላቸው፥ አይ ሞኝ፣ እሱንስ እኛ ስንፈቅድ አይደል? አሉት ይባላል። እውነት ይሁን አይሁን አላውቅም ግን ተናግሮም ሆነ ዝም ብሎ መኖር በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንዲህ ቀላል ምርጫ እንዳልሆነ እረዳለሁ። እናም ዝም ብሎ ከመጠቃት ዋሽቶ መጠቀም የሚል ፈታኝ እና ጨካኝ አቋም የሚወስዱ ምሁራን ቢኖሩ ልንፈርድባቸው አይገባም ካላችሁ ባላምንበትም ልስማማ እችላለሁ። ብቻ ቁም ነገሩ ሀሰት ተናግረው የተጠቀሙትም፣ ፈርተው ዝም ያሉትም መባከናቸው ነው።

ኢትዮጵያ ከሁለቱም አላተረፈችም። ሁሉንም አጥታለች።

ኢትዮጵያ እግዜር ያፅናሽ! አሜን?


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule