የሆላንድ ዜምብላ ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። "መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን..." በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ። ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። "ከአምባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም" ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። … [Read more...] about “ለሕዝብ ይፋ ካላደረጋችሁት የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ”