• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሄዶ ኢትዬጵያ (hej då Ethiopia)”

April 29, 2016 03:10 pm by Editor 1 Comment

በቅርቡ በዚህ በምኖርበት አገር አንድ የልደት በአል ላይ ተጠርሼ ሄጄ ነበር፡፡ በዚሁ ዝግጅት ላይ ከዝህ በፊት በአካል አግኝቼው የማላውቀው የዚሁ አካባቢ ከበርቴ ጋር ስጨዋወት ነበር፡፡ በተለይ ከአመታት በፊት በኢትዬጵያ ታስርው ስለነበሩት የስዊድን ጋዜጠኞች ልቤ እስኪጠፋ ጠየቀኝ፡፡ እኔም የምችለውን ያህል ለመመለስ ሞከርኩ፡፡  ስንሰነባብት ያለኝ ነገር ግን ሰሞኑን በኢትዬጵያ ዙሪያ የሚሰማኝን ውጥንቅጥ ስሜት ቅልብጭ አድርጎ ገለጠልኝ። ምን አለኝ መሰላችሁ… “ሄዶ ኢትዬጵያ”። አለፍ ብሎም ስሜን በወጉ መጥራት እንደከበደው ነገረኝ። በዚህ በስዊድን አፍ “ሄዶ (hej då)” ማለት ቻው ወይንም ደህና ሁን/ሁኚ እንደማለት ነው። ከዚሁ ቤት እየወጣሁ ቃሉን በውስጤ ደጋገምኩት… ሄዶ ኢትዬጵያ … ቻው ኢትዬጵያ … በተመስጦ አሰብኩት። አዎ ልክ ነው። አሁን ሰለ ሃገሬ የሚሰማኝ ስሜት ይሄ ነው። ቻው ኢትዬጵያዬ የሚል አይነት ስሜት። ለማስረዳት ልሞክር።

ሰሞኑን በጋምቤላ ወገኖቼ ላይ የተከሰተው አሰቃቂ ክስተት ለእኔ ከመቼውም ጊዜ በላይ የገለጠልኝ ሁለት ቁም ነገሮች አሉ።

አንድ።

እኛ ኢትዬጵያውያን መከላኪያ ሰራዊት ሳይሆን ማፈሪያ ሰራዊት ነው ያለን። በእጅጉ የሚያሳፍር እና የሚያሸማቅቅ። የማንኛውም አገር መከላኪያ ሰራዊት ተቀዳሚ ተግባሩ እንዲሁም የሰራዊቱ መኖር ዋንኛ ምክንያት የአገሩን ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑ ግልብ ነው። ከዚህም በላይ አንድን አገር እንደ አገር (solid state) ከሚያስቆጥሩ ቁልፍ እና ወሳኝ ነገሮች አንዱ ሉአላዊነት እንደሆነ ነው የሚገባኝ። ወደ እኛው ጉድ ስንመጣ ግን  ማፈሪያው ሰራዊታችን ተግባሩ እና አላማው ለየቅል ነው። እስከአሁን እንዳየነው ማፈሪያው ሰራዊታችን ለሰላማዊ ተቃውሞ የሚወጡ ኢትዬጵያውያን፣ ህጻናት እና እናቶች ሳይቀር መግደል ተቀዳሚ ተግባሩ ከሆነ ቆየት ብሎአል። በሙስና እስከ አፍንጫቸው ከተጨማለቁ የመንግስት ተቐሞች አንዱ መከላኪያ ነው። ለእኔ ይኼ ማፈሪያ የሆነ ሰራዊት ንጹሀን ኢትዬጵያውያንን መግደል እና የአገሪቱን ሀብት መዝረፍ የእለት ከእለት ተግባሩ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።

እሺ ሌብነቱስ ይሁን። ከከርስ ባለፈ ማሰብ በማይችሉ የግለሰቦች ስብስብ ከተሞላ መስሪያ ቤት የሚጠበቅ ነው። (በነገራችን ላይ ስለ መከላከያ ሌብነት በማስረጃ ማሳየት እችላለሁ። በግሌም ያየሁት ስለሆነ)። ንጹሀን ኢትዬጵያውያንን በተደጋጋሚ መግደሉ ለአገር ሳይሆን የሕወሀት አሽከር መሆኑን መግለጫ ነው ብለን እንውሰደው። ነገር ግን የታጠቀ የውጭ ሐይል (ያውም ከደቡብ ሱዳን) ስንት እና ስንት ኪሎ ሜትር የኢትዬጵያን ዳር ድንበር በመድፈር ሰሞኑን የሰማነወን አሰቃቂ ጭፍጨፋ በኢትዬጵያውያን ላይ መድረሱ እኛ ኢትዬጵያውያን መከላከያ ሰራዊት እንደሌለን አስረግጦ የሚያሳይ ይመስለኛል። በዚህ መልኩ የኢትዬጵያ ሉአላዊነት መደፈሩ የሚያመላክተው የኢትዬጵያን መለዮ የለበሰው እና የኢትዬጵያን የጦር መሳሪያ የታጠቀው የግለሰቦች ስብስብ (ወታደር ለማለት ስለከበደኝ ነው) መከላከያ ሳይሆን በእርግጥም ማፈሪያ ነው! ይኼን አገራዊ ውርደት ተሸክመን ሌላ አገር ሄዶ ሰላም ማስከበር፤ በእሳት እየተቃጠሉ እሳት የመሞቅ ያህል ቂላቅልነት ነው። ድንቄም አሉ!

ሁለት።

እኛ ኢትዬጵያውያን መንግስት ሳይሆን ማፍያ ነው አገራችንን የሚመራት። ለይስሙላ የሚታይ የመንግስት መዋቅር ቢኖርም፣ ፓርላማውን ጨምሮ። አገሪቱን በትከክክል የሚመራው እና የሚያስተዳድረው የግለሰቦች ስብስብ ነው። ስሙ ሕወሀት ሲሆን ተግባሩ ደግሞ የማፊያ ነው። ይኸ የይስሙላ የመንግስት መዋቅር ከስም ውጪ ሌላ እርባና የለውም። በውስጡ የተሰገሰጉት ግለሰቦች ባዶ ቀፎ ናቸው። (በዚሁ በጎልጉል ጋዜጣ ላይ ከጥቂት ጊዜ በፊት “ቀፎ አይሁኑ” በሚል ሃሳቤን ለማካፈል ሞክሬአለሁ)  ። ይኸ መዋቅር የሕወሀት ፈረስ ማለት ነው። ለዚህም ይመስለኛል ” አባ ዱላ የመለስ ጥሩ ፈረስ” እየተባለ የሚቀለደው … የሚቀለደው ልበል፤ ወይስ የሚታማው፤ ወይስ የሚታወቀው እንዲያውም እንደሚታወቀው ብንለው ይቻላል። ግልጽ ስለሆነ። የበፊት ነገስቶቻችን ከፈረሶቻቸው ስም በፊት “አባ” የሚለውን ተቀጽላ በማስታወስ። ለነገሩ ፈረስ እኮ ጥሩ እንሰሳ ነው። ታዛዥ እንሰሳ። ስለ ፈረስ ካነሳሁ አይቅር … አንድ ነገር ልበል።(የፈለገ ቢሆን አንድ ኢትዬጵያዊ ያልተማረ ፈረስ እንግሊዘኛ ሊናገር አይችልም! ግብጽ ድረስ ዲፕሎማት አድርጋችሁ ብትልኩትም። በዚህ በቅንፍ ውስጥ ያለው ለሚገባው ይገባዋል።) ወደ ጉዳዬ ልመለስ። ይኸ ራሱን ሕወሀት እያለ የሚጠራው የማፊያ ቡድን በዚህ ከላይ በጠቀስኩት ፈረስ ላይ ተቆናጦ ይኸው ለ ሃያ አምስት አመታት እየጋለበን ይገኛል። እንግዲህ ማፊያው እንደማፊያ እየዘረፈ፤ እየዋሸ እና እየገደለ እዚህ ላይ ደርሰናል። ቅጥፈቱ ከመቅረናቱ የተነሳ የሚታየው ረሃብ እና የኢትዬጵያውያን ሰቆቃ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ መርገም ነው።

ላጠቃለው፤ ስጀምር በመግቢያ ላይ ቻው ኢትዬጵያ በሚለው እደምታዬ ነበር።  አዎ የታለች ያአቺ የምናውቅት አገር? ሉአላዊ ኢትዬጵያ ወዴት ነው ያለችው አሁን?  ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁር ሕዝብ ድል አድራጊነት ለአለም ያሳየች ኢትዬጵያ የት ናት አሁን? ከነጻነት ተምሳሌትነት ተንደርድረን ወርደን ይኼው ዛሬ ኢትዬጵያውያን በበርሃ እየታረዱ ነው፤ በአደባባይ በተሰደዱበት በእሳት እየተቃጠሉ ነው፤ በርሃብ እየታረዙ ነው፤ በሜዲትራኒያን ባህር እየተዋጡ ነው፤ ጭራሽ ብለን ብለን ኢትዬጵያ ውስጥ ተጠልለው በሚገኙ የሌላ አገር ስደተኞች፤ ኢትዬጵያውያን እንደሚታደነ የዱር እንሰሳ በየጫካው ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ እየተገደሉ ነው። ታዲያ እንዲያው ድፍረት አይሁንብኝና ጥያቄ ልጠይቅ። ሁሉንም ኢትዬጵያዊ። እንደዚህ ናት እንዴ የእኛ ኢትዬጵያ? እንዴት ነው ነገሩ? ወዴት እየሄድን ነው? እንጃ?! እኔ ግን አንድ ነገር በእርግጠኝነት ልንገራችሁ። ይኸን ማፊያ መንግስት እና ማፈሪያ መከላከያ ሠራዊት ቆመን የምናይ ከሆነ፤ እውነት እውነት ኢትዬጵያን ቻው እያልናት ነው። ማፍያስ ያው ማፍያ ነው፤ ቀፎም ያው ቀፎ ነው፤ ፈረስም ያው ፈረስ ነው። እኛ ግን ምን ሆነን ነው ቆመን የምናየው?

በዚህ አጋጣአሚ በጋምቤላ ለሚገኙ እናቶቼ፤ አባቶቼ፤ እህት እና ወንድሞቼ ፈጣሪ ጽናቱን እና ብርታቱን ይስጣችሁ።

ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ።

ወንድምአገኝ እጅጉ
ከስቶኮልም፥ ስዊድን


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. ተስፋዬ አበራ says

    May 14, 2016 07:03 pm at 7:03 pm

    ወንድሜ ወንድም አገኝ የፃፍከውን አስተያየት አንብቤዋለሁ ሀሳብህን ሙሉ በሙሉ የምጋራው ሲሆን ” ኢትዬፕያን ቻው እያልናት ነው” የሚለውን ቃል ግን አልወደድኩትም ከእኛ ይልቅ እነዚህን ጉዶች ከሀገራችን እንዴት እንደምናስወግድና እነርሱኑ በሰሩት ግፍ እና ሀጥያት ለፍርድ አቁመን ቅጣታቸውን ሲጨርሱ እነርሱንም ሆነ ስርአቱን በተግባር ቻው ቻው ማለት የለብኝ ይመስለኛል።
    ታዲያ በወሬ ሳይሆን በተግባር ሁላችንም በምንችለው መንገድ መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል ሰዎቹ በህዝባችን እና ሀገራችን ላይ እየተፀዳዱብን ይገኛሉ ንቀውናል አዋርደውናል ጭራሽ የጋራ ሀብታችንን እየዘረፉ በውጭ ሀገራት ባንኮች ውስጥ ገንዘብ እንደሚያስቀምጡ ይታወቃል ስለሆነም ለተግባራዊ ትግል እንነሳ !

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule