• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቀፎ አይሁኑ!

April 8, 2016 03:46 am by Editor 1 Comment

“ምን አባቴ ላድርግ?” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ. . .እኔ ደግሞ የምለው አይዞት ክቡር ሚኒስትር ፤ አንድ ነገር ብቻ ያድርጉልን. . .እባክዎት ቀፎ መሆኑን ያቁሙልን። እንዴ ደግሞ የምን ቀፎ ነው? ቀፎ ስትል ምን ማለትህ ነው? ብሎ ግራ በመጋባት ለሚጠይቅ. . .ስለ ቀፎ ታሪክ ትንሽ ጀባ ልበል።

ነፍሳችውን ይማርና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለሰ ዜናዊ አገሪቱን እንደዚህ ጉድ በጉድ ወይም የጉድ አገር አድርገው ወደ ማይቀረው ሞት ሲሄዱ እሳቸውን የሚተካ ማን ይሆን? የሚለው ጉዳይ በፓርቲው ውሰጥ መጠነ ሰፊ መገራገጭ ፈጥሮ ነበር። ብዙ መላምቶችም ይመቱ ነበር፡፡ የሆነው ሆነ እና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚለው ዲስኩር እንዲሁም በብዙ አጀብ አቶ ሃይለማርያም ቦታቸውን ተኩ፡፡ አሊያም ተተክተው ቦታቸው ላይ ተዘፈዘፉ፡፡ በዚያ ወቅት አንዱን “የጊዜው” ሰው የሚባለውን ወዳጄን “የአቶ ሃይለማርያም መተካት እንዴት ነው?” ብዬ ጠየኩት፡፡ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች በእኔ አስተያየት የለበጠ በሚመሰል ሳቅ ካሰካካ በኋላ “የተቀየረው እኮ ቀፎው ነው፡፡ ሲም ካርዱ አልተቀየረም፡፡ ሲም ካርዱ መቼም አይቀየርም፡፡” ብሎ መለሰለኝ፡፡

እንግዲህ የቀፎው ነገር የተገለጥላችሁ መሰለኝ፡፡ በወቅቱ የወዳጄን መልስ ለመቀበል አስቸግሮኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም የፈለገ ቢሆን አንድ በአእምሮም በአካልም ሙሉ የሆነ ሰው፣ በጉልምሰና እድሜ ላይ የሚገኝ እና ፊደል የቆጥረ ሰው እንዴት ሙሉ ለሙሉ ቀፎ ሊሆን ይችላል? በፍጹም ለመቀበል ይከብዳል፡፡ በዛ ላይ ደግሞ እሳቸው “አዲስ የልማት ሰራዊት” ከሚባሉት ናቸው፡፡ ማለቴ በጫካው ትግል ውስጥ አልነበሩበትም በሚለው እሳቤ ለማለት ነው፡፡ በእርግጥ አብዛኛው “አዲስ የልማት ሰራዊት” ተብለው ሲያበቁ እነሱ ግን “አዳዲሰ ጅቦች” በመሆን እኛን እና አገራችንን አድምተው እየዘረፉን ቢሆንም፡፡ በጥቅሉ “እኛ ታግለን ባመጣነው” በሚል መታበይ ውሰጥ የሉበትም በሚለው እንውሰደው፡፡ በአጭሩ ሙሉ ለሙሉ ቀፎ ይሆናሉ የሚል ግምት አልነበረኝም፡፡ ትንችም ቢሆን የለውጥ ንፋስ ጠብቄ ነበር፡፡

ነገር ግን ይኽው እንደምናየው አሪፍ ቀፎ ሆነው እርፍ! ያውም የድሮው ኖኪያ፡፡ የጥቁር ሰሌዳ ማፅጃ ዳሰተር የሚያክለውን ድንጋይ የሆነ ቀፎ፡፡ ለማንኛውም ሰሞኑን “ምን አባቴ ላድርግ?” አሉ፡፡  ለዚህ ነው እኔ. . .ምንም አባትዎ አያድርጉ. . .እባክዎት ቀፎ መሆንዎን ብቻ ያቁሙልን የምለው፡፡ ሌላ ታሪካዊም ሆነ ምሁራዊ ትንታኔ የለኝም፡፡ አጭር እና ግልጽ፡፡ እስቲ ይቺን ብቻ ያድርጉና ያኩሩን እሰቲ. . .እስቲ የእውነት ታሪክ ይስሩ! ለምሳሌ . . .

ምሳሌ አንድ፤

ከወራት በፊት የአገሪቱን ከፍተኛ እና ትክክለኛ ባለሥልጣናት ወይም በሌላ ስማቸው ይሁን ማእረጋቸው የእርስዎ አማካሪዎችን ሰብስበው “በመልካም አስተዳደር መጥፋት እና የሙስና አለቅጥ መስፋፋት” ጥናታዊ የስብሰባ አጢባራዎት ላይ ቀፎ የሆነ የቀፎ ዲስኩሩን አቁመው ለአንድ አፍታ ህሊናዎን በመጠቀም ቢያስተውሉ. . .በዲስኩሩ መሃል አንድ የእርስዎ አማካሪ “ይህን ነገር በዘመቻ ወይስ በስትራቴጂ እንዋጋው” እያለ ፊለፊትዎ ተጎልቶ ይደሰኩር ነበር፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው እርሶዎም ግጥም አድርገው እንደሚያውቁት ይህ አማካሪዎ ቁጥር አንድ ሌባ እና ሙሰኛ ነው፡፡ በዚህ አማካሪዎ ላይ የመረጃም ሆነ የማስረጃ ችግር የለም፡፡ ስለዚህም በህግ ከተሰጥዎት ስልጣን በመመዥረጥ እስቲ ይህን አማካሪዎን ህግ ፊት አቅርቡልን እና የእርስዎም ቀፎ መሆን ይብቃ! እስቲ እንዲያው በሞቴ፣ አፈር ስሆን ብሎ እንደሚማጸነው ያገሬ ሰው ልለምንዎት አቶ ሃይለማሪያም እንዲያው አፈር ስሆን ይህን አማካሪዎ ለፍትህ ያቅርቡልን፡፡ ይሄ አማካሪዎ በተለይ የቦሌን ክፍለ ከተማ ከዘመድ አዝማዱ ጋር በመሆን ሸንሽኖ በመሰልቀጥ ትልቅ “የመሬት ከበርቴ” እንደሆነ የአደባአባይ ሚስጥር ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አሰገራሚ የሆኑትን የቦሌ ክፍለ ከተማ ሰነዶች ቢመረምሩ እውነታው አሁንም አፍጥጦ ይገኛል፡፡ የጸረ-ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎችም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ምርመራ እንዳያደርጉ ከበላይ በቀጭን ትእዛዝ ታግደዋል፡፡ ሌላም ከፈለጉ ይህ አማካሪዎ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ነበር፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ነበር፡፡ ኮርፖሬሽኑን ለማመን በሚያስቸግር መልኩ እስከ መጨረሻው ጠብታ ዘርፏል እየዘረፈም ነው፡፡ ታዲያ አቶ ሃይለማሪያም ይህን የሚያክል ግዙፍ የሆነ መረጃ እና ማስረጃ እያለ “ምን አባቴ ላድርግ?” የሚሉት እውን ቀፎነት ለህሊናዎ ይህን ያህል አይጎረብጠውም ማለት ነው?

ምሳሌ ሁለት፤

ሰሞኑን በተደረገ ስብሰባ ላይ ከእራስዎ አንደበት እንደሰማነው አገራችን ውስጥ የራሱ እስር ቤት ያለው አንድ ትልቅ ሀብታም አለ አሉን፡፡ እሺ ይሁን ብለን እየመረረን እንቀበለዎት ግን እባክዎን፣ እንዲያው በፈጠርዎት አምላክ (መንፈሳዊ ነዎት ተብሎ ስለሚወራ ነው በአምላክዎት የምለው) ቀፎ አይሁኑብን!

ማነው ይሄ ሃብታም? የትኛው የደኅንነት እና የወታደር ጎራ (ግሩፕ) ነው እንደዚህ እንዲፈነጭ፥ ወጥ እንዲረግጥ ያገዝው? ለምንድ ነው እውነቱን አፍረጥርጠው ከቀፎነት የማይገላገሉት? እንደገና ነጋዴዎችን ሰብስበው “ማሰር ከጀመርን ብዙ ይታሰራል. . .” እያሉ ከሚያፌዙ፥ ህግ የጣሰውን ለምን አያስሩም? ህግ የማያከብር ነጋዴስ ከቶ ምን ሊረባን? ነው ወይስ ሌሎችም ነጋዴዎች እስር ቤት እስኪሰሩ ነው የሚጠብቁት? “ወይ ነዶ…..” ይላል ያገሬ ሰው!

አቶ ሃይለማሪያም እባክዎት በህዝብ እና አገር ላይ አይቀልዱ፡፡ አሁን የሚኖሩበት ምቹ ቤት እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ የሚደርሱት እኮ ዛሬ እየተራበ እና እየሞተ ካለው ምስኪን ደሃ ገበሬ መሆኑን አይዘንጉት፡፡ እርስዎም የገበሬ ልጅ ነበሩና፡፡ እንደ አንድ ተራ ዜጋ የምጠይቀዎት ነገር አንድ እና አንድ ብቻ ነው፥ አሁንም በድጋሚ. . .እባክዎት ቀፎ መሆንዎን ያቁሙ!?

አገራችንን ፈጣሪ ይባርክልን!

ወንድምአገኝ እጅጉ
ከስቶኮልም፥ ስዊድን

(ፎቶ: AddisFortune)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mame Nasir says

    April 15, 2016 12:14 pm at 12:14 pm

    Oy Oy Oy

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule