Famine is back in Ethiopia. Famine and Ethiopia have become so interchangeable western comedians don’t feel shame making famine jokes using us as a punch line. How is our first 21st Century famine being welcomed in our precious homeland? I am afraid our response has not changed. Denial, surprise, blame and righteous indignation have been brought out of the closet. The response by the Emperor, the Junta and the ethnically challenged mafia group are typical Ethiopian. ‘Shit happens but this time … [Read more...] about Cry for Tigrai
Archives for November 2015
ብሔር ወይስ ሰው-ነት?
መኃኑን ታሪክ ለማዋለድ በሚደረገዉ "ጥረት" አብዝቼ ባዝንም፣ የቀደመዉን የሃገሬን ጠመዝማዛ የታሪክ መንገድ ግን ከነእንከኑ እቀበለዋለሁ፡፡ የታሪክ ክህደትም ሆነ የታሪክ ብዜትን ሊጭኑብኝ ለሚሞክሩ ሰንባችም ሆኑ አርፋጂ ብሄረተኞች ጆሮዬንም ሆነ አዕምሮዬን የምሰጥ ሰዉ አይደለሁም፡፡ ትላንትን በዛሬ መነጽር ባላየዉ እንኳን የቀደመዉን ዘመን በሰብዓዊነትና በማህበረሰባዊ ዉል ሚዛን ላይ አስቀምጬ እንድመለከተዉ ሰው-ነቴ ያስገድደኛል። ሰው ነኝና። ሰው።. . . . በገባኝ መጠን የዛሬዋን ቁርጭምጭሚት ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለማውጣትና ገጽታዋን ለማደስ ሲሚንቶው ሰብዓዊነት ሊሆን ይገባል። ከብሔር አጥር ባሻገር ዜግነት የሚባል ሰፊ ሜዳ እንዳለ ልብ እንበል። ኢትዮጵያችንን ከሁለንተናዊ ውድቀት ለመታደግም ሆነ ዳግም ለመገንባት የቀጥታ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ብቻ መፍትሄ አይደለም። ይልቁንስ … [Read more...] about ብሔር ወይስ ሰው-ነት?
Center for the Rights of Ethiopian Women welcomes Reeyot Alemu
Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) is delighted to announce the arrival of the award winning journalist, Reeyot Alemu to the United States on Saturday, November 7, 2015. CREW sent invitation to the respected journalist and freedom of speech advocate, Reeyot Alemu and her sister Eskedar Alemu to speak at the upcoming Women and Leadership Conference which will be held sometime in the coming month. Reeyot has been imprisoned for over 4 years and was released in July of 2015. Reeyot … [Read more...] about Center for the Rights of Ethiopian Women welcomes Reeyot Alemu
ሁለት ጥያቄ ብቻ አለን?
ድሬ ቲዩብ በመባል የሚታወቀው በአማርኛ "ትልቁ" የድህረ ገጽ እና ድህረ ምስል አውታር፣ ሰሞኑን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሁለት ጥያቄ ጠይቆ ነበር። 1ኛው የኢትዮጵያ መሪ (ፕሬዝዳንት) ማን ናቸው? የሚል ሲሆን 2ኛው ደሞ የአሁኑ የአዲስ አበባ ከንቲባ ስማቸው ማን ይባላል? የሚሉ ናቸው ። ሕዝቡም እንደ አቅሙ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ጥሯል። ሙላቱ አስታጥቄ፣ እንዳለ አድምቄ፣ አሰፉ ደባልቄ፣ ዶቅዶቄ፣ ቦሎቄ፣ አረቄ እና ወዘተ። የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች መለስ ነው አዲስ አበባን የቆረቆራት (ወይም ከንቲባዋ መለስ ነው) ሲሉ፣ የጥበቃ ሰራተኞች "ማን ነበር? ይገርማል!" በማለት አለማወቃቸውን አሳውቀዋል። ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ እና ኩማ ደመቅሳም ያሉም አሉ። ይህ እንግዲህ የአዲስ አበባ ከተማ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ። መረጃ … [Read more...] about ሁለት ጥያቄ ብቻ አለን?
“የኤርትራ ምሽት” ለስደተኞች ደራስያን
ካንድ አሰርት ዓመታት በላይ አባል ሁኜ የቆየሁበት ኖርዌጂያን ፔን (Norsk PEN/N0rwegian PEN) የሚያከናውናቸው የተለያዩ ተግባራት አሉት፡፡ ከነዚህም አበይት ትግባራቱ መካከል በያገራቱ ያሉ እህት ማህበራትን መታደግና ለስደተኛ ደራስያን የከተሞች የጥገኝነት (By Forfatter) መብትን ማሰጠት ነው፡፡ ሥራቸውም እንዲታተምና ለሕዝብ እንዲደርስ ጥረት ያደርጋል፡፡ በእስር ላይ የሚገኙ የሌሎች አገር ደራስያንንና ጋዜጠኞችን ማሰቢያ ምሽቶችን በየጊዜው ያዘጋጃል፡፡ ከዚህ ቀደም የማሰቢያ ምሽት ከተዘጋጁላቸው ጸሐፍት መካከል እውቁ ጸሐፊ ኢትዮጵያዊው እስክንድር ነጋና ስዊድናዊ/ኤርትራዊው ዳዊት ይስሃቅ ይገኙባቸዋል፡፡ እናም ኖርዌጂያን ፔን ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን "የኤርትራ ምሽት" የተሰኘ የምሽት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ይህ ምሽት ኤርትራ ወስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት … [Read more...] about “የኤርትራ ምሽት” ለስደተኞች ደራስያን
ሥደት
ቦሳሶ፣ ሶማሊያ ቦሳሶ በገልፍ ባህረ ሰላጤ ደቡባዊ ክፍል፣ሶማሊያ ጠርዝ ላይ የምትገኘው ከተማ፣ ካርታ ላይ ሲመለከትዋት፣ ያፍሪካ ቀንድ ላይ የተቀመጠች ዝምብ ትመስላለች። አፈ ታሪክ ስለከተማዋ አሰያየም እንዲህ ይላል። ቦሳሶ የቀድሞ ሥያሜዋን ያገኘችው ካንድ ታዋቂ ነጋዴ ሥም ነበር - ባንዳር ቃሲም ከተባለ ነጋዴ። ቃሲም ከተማ እየተባለች ትታውቅም ነበር። ነጋዴው፣ ባንዳር ቃሲም ደግሞ እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ቡሳስ የተባለች ግመል ነበረችው። ሥለዚህ ከተማዋ ከጊዜ በኋላ በቃሲም ተወዳጅ ግመል ቡሳስ ተብላ ተሰየመች። እያደር ከቡሳስነት ወደ ቦሳሶ ተቀየረች። አለምሰገድና ባለቤቱ ምህረት፣ ምህረትያንድ አመት ልጃቸውን አቅፋ፣ ከቦሳሶ ተነስተው ከሦስት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማሬሮ ገብትዋል። ማሬሮ ገደላማ ናት። ካርቶን አንጥፈው የሚቆረቁረው መሬት ላይ ተቀመጡ። አለምሰገድ ለራሱና ለምህረት … [Read more...] about ሥደት
ንቧ ድፍት ኣለች
እንደው ባለፈው አመት ህወሓት 40ዋን ስታወጣ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ እንዳደረገች የምታስታውሱት ነው። የዲያስፖራ ቀን በትግራይ ሲከበር 200 ሚሊዮን ብር ወጪ፣ የአርቲስቶች ጉብኝት፣ የከተሞች ቀለሞች መቀባት፣ የዜሮ አምፑል መብራቶች (ህዝቡ ዜሮ አምፑል መንግስት ያለው)፣ የካኪ ልብሶች፣ ድግሶችና ግዢዎች ወጪ ከ2 ቢሊዮን እንዳወጣች በወቅቱ የተገለፀ ነው። በወቅቱ የ38 ሚሊዮን ኩንታል ከክረምት፣ 75 ሚሊዮን ኩንታል ደግሞ ከመስኖ እርሻ እህል ተመረተ ብለው የተተረተሩበት ዓመት ነበር። እያንዳንዷ ካድሬ፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ የሊግ፣ የማህበራትና የአንድ ለ አምስት ኔትወርክ መሪ ሁላ አካኪ ዘራፍ እያለች የመለስ ራዕይ ተሳካ እያለች ስታሽካካ ነበር። እውነት እንኳን ድሃ ድህነት የሚል ቃልም ድራሹ የጠፋ አስመስለውት ነበር። ዳሩ ግን ያሁሉ ፕሮፖጋንዳ 4 ወር ሳይቆይ ለአለም ማህበረሰብ … [Read more...] about ንቧ ድፍት ኣለች
ሻምበል ሞገስ ወልደሚካዔል
በግልጽ መታወቅ ያለበት የግለሰቡ ማንነትና ያደረገው አስተዋፅዖ ዓመቱ ፲፱፻፷፫ ነበር። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ፤ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነበርኩ። በዚያ ጊዜ ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ፤ በስተግራ ከነበረው የፋሲካ ሆቴል፤ ከሆቴሉ በስተሰሜን ገባ ብሎ በረባዳው በኩል፤ ተከራይቶ የሚኖር፤ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ነበር። ይህ መምህር አቶ ክብረት ተስፋሁን ይባላል። የሻምበል ሞገስ ወልደሚካዔል የናቱ ታናሽ ወንድም ነው። አራት ሆነን ምሳ ስንበላ፤ ሞገስና እኔ በዩኒቨርሲቲው የምናደርገው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃመወያየት ጀመርን። ለኮንግሬስ ( የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበር - አዩተማ University Students Union of Addis Abeba – USUAA - ኡዙዋ) የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን … [Read more...] about ሻምበል ሞገስ ወልደሚካዔል
በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ
በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ኦክቶበር 31 -2015 (ጥቅምት 20 - 2008 ዓ.ም) ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል። በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ናቸው። ዝግጅቱ ረፋዱን 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን አቶ ጌታሁን ማሬ የዝጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የስዊድን የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ስለዝግጅቱ ገለጻ እንዲያደርጉና ዝግጅቱንም እንዲመሩ ጋብዘዋል። አቶ ዘለሌ በበኩላቸው የከተማው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ገልጸው እንግዶቹንም በማስተዋወቅ አቶ አበበ ቦጋለና አቶ ቸኮል … [Read more...] about በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ
የእኔ፣ ያንተ፣ የእናንተ፣ የእኛ ተጠቂዎች!
የብላቴናው መሀመድን እናት እርዳታ አድራጊ ወገኖቸ የቻልኩትን እርዳታ ለመሰብሰብ ወጣ ባልኩበት አጋጣሚ ስልክ ተደወለልኝ። አነሳሁት፣ ከሰላምታ በኋላ "ጠፋህ? የት ነው ያለህ?" ከሚለው አጭር የተለመደ የሰላምታ ማጀቢያ በኋላ ወዳጀ ወደ መልዕክታቸው ገቡ ... "አንተ ነብዩ የት ጠፋህ?" ሲሉ ደገሙና ስመለጥፋቴ ጠይቀውኝ ሲቀጥሉ "ናና አንድ እህት ከጅዳ ቆንስል በር ወድቃለች፣ ጸሀይ እየደበደበ አድክሟታል! እነሱ (የቆንስል ሰዎች ማለታቸው ነው) ቢነግሯቸው አይሰሙም። ሌላም ሶስት እህቶች ከቆንስሉ አጠገብ ካለው ንጉድ ፉአድ ሆስፒታል ያለ ጠያቂ ተኝተዋል። ጎብኟቸውና ችግራቸውን ተረዱ ወይ መፍትሄ ፈልጉ ወይ ወደ ሀገር ስደዷቸው ብል የሚሰማ የለም! አንተን ከሰሙህ ናና እያቸው!" ብለው ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት አስተላለፈውልኝ ተጣድፈው ስልኩን ዘጉት ... ! የእኒህ ወንድም … [Read more...] about የእኔ፣ ያንተ፣ የእናንተ፣ የእኛ ተጠቂዎች!