ካንድ አሰርት ዓመታት በላይ አባል ሁኜ የቆየሁበት ኖርዌጂያን ፔን (Norsk PEN/N0rwegian PEN) የሚያከናውናቸው የተለያዩ ተግባራት አሉት፡፡ ከነዚህም አበይት ትግባራቱ መካከል በያገራቱ ያሉ እህት ማህበራትን መታደግና ለስደተኛ ደራስያን የከተሞች የጥገኝነት (By Forfatter) መብትን ማሰጠት ነው፡፡ ሥራቸውም እንዲታተምና ለሕዝብ እንዲደርስ ጥረት ያደርጋል፡፡ በእስር ላይ የሚገኙ የሌሎች አገር ደራስያንንና ጋዜጠኞችን ማሰቢያ ምሽቶችን በየጊዜው ያዘጋጃል፡፡ ከዚህ ቀደም የማሰቢያ ምሽት ከተዘጋጁላቸው ጸሐፍት መካከል እውቁ ጸሐፊ ኢትዮጵያዊው እስክንድር ነጋና ስዊድናዊ/ኤርትራዊው ዳዊት ይስሃቅ ይገኙባቸዋል፡፡ እናም ኖርዌጂያን ፔን ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን “የኤርትራ ምሽት” የተሰኘ የምሽት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ይህ ምሽት ኤርትራ ወስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና አጠቃላይ ስቃይ ሸሽተው የወጡ የኤርትራ ደራስያንን ለመታደግ ነበር፡፡ ደሳለ በረከትና ኃይሌ ቢዘን አብርሃ የተባሉት የኖርዌይ ከተሞች ጥገኛ ደራሲያንና ናታን ሐዲሽ ሞገስ የተባለው የፖለቲካ ስደተኛ ደራሲ የምሽቱ ተጋባዥ ዝግጅት አቅራቢ ደራስያን ነበሩ፡፡ (ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply