እንደው ባለፈው አመት ህወሓት 40ዋን ስታወጣ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ እንዳደረገች የምታስታውሱት ነው።
የዲያስፖራ ቀን በትግራይ ሲከበር 200 ሚሊዮን ብር ወጪ፣ የአርቲስቶች ጉብኝት፣ የከተሞች ቀለሞች መቀባት፣ የዜሮ አምፑል መብራቶች (ህዝቡ ዜሮ አምፑል መንግስት ያለው)፣ የካኪ ልብሶች፣ ድግሶችና ግዢዎች ወጪ ከ2 ቢሊዮን እንዳወጣች በወቅቱ የተገለፀ ነው።
በወቅቱ የ38 ሚሊዮን ኩንታል ከክረምት፣ 75 ሚሊዮን ኩንታል ደግሞ ከመስኖ እርሻ እህል ተመረተ ብለው የተተረተሩበት ዓመት ነበር።
እያንዳንዷ ካድሬ፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ የሊግ፣ የማህበራትና የአንድ ለ አምስት ኔትወርክ መሪ ሁላ አካኪ ዘራፍ እያለች የመለስ ራዕይ ተሳካ እያለች ስታሽካካ ነበር።
እውነት እንኳን ድሃ ድህነት የሚል ቃልም ድራሹ የጠፋ አስመስለውት ነበር። ዳሩ ግን ያሁሉ ፕሮፖጋንዳ 4 ወር ሳይቆይ ለአለም ማህበረሰብ በድርቅ ለተጠቃ ህዝብ እርዳታ በመለመን አስደነገጡን።
የየካቲት 11 በዓልና ያጋጠመው ድርቅ ኢህአዴግ ልክ እንደ ሃይለስላሴና ደርግ ስርዓቶች የህዝብ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ሞት የማይሰማው ግኡዝ መንግስት መሆኑ ያጋለጡበት አጋጣሚ ፈጥሮ አልፏል።
1) የጃንሆይ ልደትና የ67 ድርቅ
2) የደርግ ኢሠፖአኮ ልደትና የ77 ድርቅ
3) ህወሓት ልደት የየካቲት 11ና ድርቅ 2007/8 በተመሳሳይ ምድብ ያጋልጣቸዋል።
ህወሓት ከ30 ዓመት በፊት ያኔ የሽምቅ ተዋጊ በነበረችበት ግዜ ራስዋ ወደ ማሌሊት ስታሸጋግር ለትግራይ ህዝብ እንድታከፋፍል የተሰጣት እርዳታ 95% ለመመስረቻ በአል ድግስና ለጦር መሳርያ መግዣ እንዳዋለችው BBC እንደዘገበው የአሁኑ የእርዳታ እህል “ለአባይ ግድብ፣ መጋዘን ሞላ” እየተባለ እየተሸጠ እንዳለ እየተነገረ ነው። ህወሓት በበረኻም በቤተ መንግስትም ሁና የህዝብ እርዳታ የመቀማት ልማዷ እንዳልተወች ነው።
ህወሓት ለአርባዋ ብዙ ሽርጉድ ብላለች። ከዝግጅቱ ትልቅ ንብ ቀርፀው ተሽከርካሪ ነገር ሰርተው በቲዮታ መኪና እየጎተቱ በማዞር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አንዱ ነበር።
ታድያ ንቧ የጉዞዋን ግማሽ ከሄደች በኋላ ንግድ ባንክ አለፍ ብላ ሑመራ ሆቴል አጠገብ እኔ ወደ ነበርኩበት ስትደርስ ንቧ በአፍ ጢሟ ድፍት አለች።
ንቧ ፊትለፊቴ ድፍት ስትል እኔን የሚል አንድም ሰው አልነበረም። አንዷ ተለቅ ያሉ ሴትዮ “እንዴ ምን ነክቷት ነው አሁን በአፍጢሟ የተደፋችው …?” ይላሉ። ሌላኛዋ ደግሞ “አታዮ ክንደየን ዳ ኖአኻ ትኾኖ” (እናንተዬ እንዴት አባትዋ ታክላለች) ሲሉ ነበር።
ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት “እቺስ አውራዋ ሙሰኛዋ ናት። እንዲህ የወፈረችው ሙስና በልታ በልታ መሆን አለባት” ሲል ቀለደባት።
ንቧ ፊትለፊቴ መጥታ ድፍት አለችና ተጎትታ ወደጎን ተወሰደች።
በመኪና የመጣችው ንቢቱ ሰው ድሃ ይሁን ሃብታም ሲሞት በሶስት ሜትር አቡጀዲድ እንደሚገነዝ ጋሪ ላይ ወጥታ ተገንዛ ተጭና ሄደች። እኔም ወደ ጋሪዋ ሲጭንዋት አገዝኳቸው። ምክንያቱም በባህላችን ሬሳ ሲሸኝ የማታውቀው ቢሆን’ኳ ተሸክመህ መሸኘት ግዴታ ነው።
ቦታው ላይ የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ነበረና ድፍት ያለችው ንብ ፎቶ ሲያነሳ ነበረ።
የንቧ ፊት ለፊቴ መጥታ በአፍ ጢሟ ድፍት ማለት ግን አይገርምም…?
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO…!!!!
(ምንጭ: ፎቶና ጽሁፍ ከAmdom Gebreslasie ፌስቡክ ገጽ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
በለው ! says
“ንብ ከተደፋች ከእግርህ ሥር
ልታቆም ነወይ መቅሰሟን ልትበላ ሳር
ሁሉ መረረ ጠፋ የማር አንጀራ በሀገር
ከተደፉ ይቅር በላቸው አትጨክን ማር”
በለው!