• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእኔ፣ ያንተ፣ የእናንተ፣ የእኛ ተጠቂዎች!

November 1, 2015 05:09 pm by Editor Leave a Comment

የብላቴናው መሀመድን እናት እርዳታ አድራጊ ወገኖቸ የቻልኩትን እርዳታ ለመሰብሰብ ወጣ ባልኩበት አጋጣሚ ስልክ ተደወለልኝ። አነሳሁት፣ ከሰላምታ በኋላ “ጠፋህ? የት ነው ያለህ?”  ከሚለው አጭር የተለመደ የሰላምታ ማጀቢያ በኋላ ወዳጀ ወደ መልዕክታቸው  ገቡ …

“አንተ ነብዩ የት ጠፋህ?” ሲሉ ደገሙና ስመለጥፋቴ ጠይቀውኝ ሲቀጥሉ “ናና አንድ እህት ከጅዳ ቆንስል በር ወድቃለች፣ ጸሀይ እየደበደበ አድክሟታል! እነሱ (የቆንስል ሰዎች ማለታቸው ነው) ቢነግሯቸው አይሰሙም። ሌላም ሶስት እህቶች ከቆንስሉ አጠገብ ካለው ንጉድ ፉአድ ሆስፒታል ያለ ጠያቂ ተኝተዋል። ጎብኟቸውና ችግራቸውን ተረዱ ወይ መፍትሄ ፈልጉ ወይ ወደ ሀገር  ስደዷቸው ብል የሚሰማ የለም! አንተን ከሰሙህ ናና እያቸው!” ብለው ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት አስተላለፈውልኝ ተጣድፈው ስልኩን ዘጉት … ! የእኒህ ወንድም መረጃ ሲያቀብሉኝ በስጨት ማለት ምክንያቱ ገብቶኛልና አልተከፋሁም፣ ይልቁንም ስለሰጡኝ መረጃ አመሰገንኳቸው። …

አሁን አሁን በኮንትራት መጥተው ጠፍተው ሲሰሩ የነበሩት፣ በባህርም ሆነ በቀድሞው ሃጅና ኡምራ  መጥተው በአሰሪዎቻቸው መደፈር መደብደብን ጨምሮ ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት  የተለያየ ጥቃትም ሆነ ህመም ሲያጠቃቸው መጥተው የሚወድቁት በዚሁ በጅዳ ቆንሰል በር ነው። ለምን ቢባል ዘንድሮ  ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ማስጠጋት አደጋ አለውና ነው፣ አደጋው ደግሞ ቤተሰብን ጠቅልሎ ከሀገር መባረር ነውና ያስፈራል። ይህ የከፋ ችግር የተጋረጠበት የጨነቀው ነዋሪ እየፈራ እየተባ ያስጠጋው ነዋሪ ወደ ሀገር ይገባ ዘንድ ከቆንሰል መስሪያ ቤቱ ጋር ሞግቶ አልሳካለት ሲል ከቀጣዩ አደጋ ራሱን ለመከላከል የስጋ ዘመዱን ሳይቀር በጠራራው ጸሀይ ጨክኖ አምጥቶ የሚጥለው በቆንስሉ በር ላይ ነው!eth

ያን ሰሞን አንድ ወዳጀ “በቆንስሉ በር የወደቀች ልጅ አለች እያት ታሳዝናለች!” የሚል መረጃ አደረሰኝና ወደ ዚያው አቀናሁ፣ ሙቀት ያደከማት፣ ውሃ ጥም ያደረቃትን እህት አገኘኋት፣ ከመኪናየ ውስጥ የነበረውን ውሃ ስሰጣት ተንሰፍስፋ ስትጠታው የተሰማኝን ህመም ሳስበው እታመማለሁ … ልጅቱ በዥጉርጉሩ ፎቴ ተዘርራ የምታዮዋትን ናት፣ ውሃው ድካሟን አልመለሰውም፣ ተንፈስ ማለት ችላለች … ያም ቢሆን የዋለባት ሙቀቱ አድክሟት ያዝ ለቀቅ እያደረገች ያጫወተችኝ የቅርብ ዘመዶችዋ በቆንስል መስሪያ ቤቱ በኩል ወደ ሀገር የመጓጓዣ ሰነድ አውጥተው ለመስደድ ሞክረው አልሆን ሲላቸው አምጥተው እንደጣሏት ነበር  … ስሜቴ በጣሙን ተነክቶ ወደ አምባሳደር ውብሸት በላኩት መልዕክት ቦታውን ሳልለቅ ወደ መጠለያው ለመግባት ፈቃድ በማግኘቷ ቆንስሉ ልትሞት የነበረቸውን እህትን የታደጋትን ያህል ተደሰትኩ …

ዛሬ ከሰዓታት በፊት ያየኋት እህት በጠራራው ጸሃይ በቆንስሉ በር ተዘርራ ተኝታ ነበር፣ አትሰማም አትናገር ። ብዙዎቻችን ከንፈራችን እየመጠጥን ስናልፋት በመኪና የሚተላለፉት አረቦች ሲያዩዋት መኪናቸውን አቁመው “ለምን ወደ ግቢ  አታስገቧትም? ለምን አንቡላንስ አትጠሩም?” እያለ እያዘኑ “ፈጣሪ ይድረስልሽ ፣ ምስኪን!” እያሉ  ይሄዳሉ … እያየን ወደ ሀላፊዎች ስልክ ደውለን ለማሳወቅ እንኳ “ተቃዋሚ ምንቴስ ” እንባላለን ብለን ከምንፈራው ብዙዎች የተሻሉ የምላቸው የሳውዲ መንግስት የቆንስሉ ጠባቂዎች ደጋግመው ወደ ቀይ ጨረቃ ደውለው አምቡላንስ አልመጣ ቢልም ጉዳዩን ወደ አንድ ጉምቱ ባለስልጣን በመድረሱ አምቡላንሱ ፈጥኖ ሳይመጣ አይቀርም! እኔም እንደ አልፎ ሂያጁ አረብ “ምስኪን! ፈጣሪ ይድረስልሽ!” ከማለት ውጭ የምለው የለም… !

እኛ ቅንጡዎች “ራሳችን፣ ሆድ እቃ፣ እግር እጅ፣ አይናችን አመመን!” ብለን አገር ይያዝ ብለን በምንቀውጥበት ሰማይ ስር ያየሁት የማይታመን አይደለም፣ ይህችና ይህችን መሰል እህቶች በሀገራችን የመንግስት ተወካይ፣ የማህበረሰብና የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮችና የደላ የሞላልን ሳይሆን ሳይደላን በሽፍንፍን ህይዎት አሸሸ ገዳሜ በምንልበት አዳራሽና ቆንስል በር በተደጋጋሚ ይጣላሉ፣ ያለላቸው ተርፈው ያላለላቸው “ሰርታ ታሻሽለኛለች!” ብሎ ለላከላቸው ወላጅ የህይዎት እንቆቅልሽ ይሆኑ ዘንድ  ማንነታቸው ሳይታወቅ ወደ ማይቀረው አለም ይሸኛሉ (… የሳውዲ መንግስት በነጻ የሚሰጠው  ህክምና አይደለም ቀዝቃዛ ውሃ ናፍቋቸው፣ ይህችን አለም ሲሰናበቱ ማየት በእርግጥ ያማል … (ይህን አይቶ ዝም ማለቱም ለእኔ ሌላ እዳ ነውና ያማችሁ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸው መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ እነግራችኋለሁ!

ደረቁ እውነት ይህ ነው … እኒህ በየሜዳው ተጥለው የሚጠፉት እህቶች ከወላጅ ጀምሮ፣ የመንግስት፣ የነዋሪው፣  የማህበረሰብ ተወካዮች፣ ይህ መከራ መቋጫ እንዲመጣ ያልተጉት ፖለቲከኞችን  ጨምሮ በግል የእኔ፣ ያንተ፣ ያንችም የሁላችንም ተጠቂዎች ናቸው! በጅዳ ቆንስልና በሪያ ኢምባሲ በር የሚጣሉ ወገኖች … ተጠቂዎች ናቸው!

ቸር ያሰማን ስል ለብላቴናው መሀመድ እናት ለእናት ሀሊማ የምታደርጉትን እርዳታ እንዳትረሱ በማስታወስ ነው! የመሀመድ ቤተሰብ ፍትህ እስኪያገኙ ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ የከበደውን አንግልትና ወጫቸው ለመሸፈን ቢገድ ለቤት ኪራይና ትራንስፖርት የቻልነውን በማድረግ መከራውን ልንጋራ ይገባል። አነሰ በዛ አትበሉ፣ ብርቱዋን እናት ሃሊማን ቢያንስ ለማረፊያና ለትራንስፖርት ለመርዳት ፈቃደኛ የሆናችሁ በስልክ ቁጥር 0505682531 ደውሉ ካላችሁበት ድረስ መጥቸ እርዳታውን እቀበላለሁ!

ሰላም!

ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule