የትግሬ ወያኔ በኃሣብ፣ በዕቅድ እና በተግባር ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ ድርጅት መሆኑን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ሠሞኑንም ከመገናኛ ብዙሃን የሚደመጠው «የትግራይ ድንበር አል-ውሃ ድረስ ነው» የሚለው ወሬ የዚሁ የሚጠበቀው የትግሬ-ወያኔ ተከታይ እርምጃ እንደሆነ አያጠያይቅም። ኢትዮጵያን የማፈራረሱ የንድፈ-ኃሣብ መሠረት የተጣለው በተለያዩ የውጭ ኃይሎች እንደሆነ ይታወቃል። ከእነዚህ መካከል ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለው የኦስትርያ-ሐንጋሪ መሥፍን (Baron Roman Prochazka) ወጥነት ባለው መንገድ አዘጋጅቶ ያሠራጨው መጽሐፍ ዋና ተጠቃሽ ነው። የሮማን ፕሮቻዝካ መጽሐፍ ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን በተወረረችበት በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. (1935 G.C.) በጀርመንኛ ቋንቋ «Abessinien: die schwarze Gefahr» በሚል ርዕስ፣ … [Read more...] about ምን እየጠበቅን ነው?
Archives for February 2015
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ
ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል። ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ በ 24 ዓመት የወያኔ አረመኒያዊ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉት እና በየእስር ቤቱ በግፍ ለሚስቃዮ ንጹሀን ዜጐች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጹሎት በማድረግ ስብሰባውን ያስጀመሩ ሲሆን በመቀጠልም … [Read more...] about የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ
ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት
እጅግ ለተከበሩ ለብፁዕ አቡነ ብርሃነ-ኢየሱስ ደምረው ሱራፌል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት፤ የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንትና የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ቤ/ክ ማሕበር ሊቀ መንበር፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ። በመጀመሪያ፤ ለብፁዕነትዎ የሚገባ እጅግ ከፍ ያለ የአክብሮት ሰላምታ አቀርባለሁ። በተጨማሪም፤ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደህና፤ በክብርና በሞገስ አደረሰዎ በማለት መልካም ምኞቴን በትሕትና እገልጻለሁ። በመቀጠልም፤ ሰሞኑን የ1.228 ቢሊዮን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ባላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፤ እጅግ የተከበሩ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳት (ካርዲናል) ሆነው በመሾምዎ፤ እንኳን ደስ አለዎ በማለት፤ ለዓለም ሰላምና ለክርስቲያን አንድነት የሚያደርጉት ጥረት በቸሩ አምላክ ተራዳኢነት እንዲሳካልዎ ልባዊ ጸሎታችንን በትሕትና እናቀርባለን። የብፁዕነትዎ … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት
አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
ኢህአዴግ በ“አሸባሪነት” የከሰሳቸውና ከየመን ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ቅዳሜ በኦስሎ ኖርዌይ ተከብሯል፡፡ በሥፍራው የተገኘው ዳንኤል አለባቸው ለጎልጉል በኢሜይል በላከው መረጃና ፎቶ እንደገለጸው ዝግጅቱ የተደረገው እዚያው ኖርዌይ በሚገኝ “የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት” ነበር፡፡ በበዓሉ ወቅት የአቶ አንዳርጋቸውን ህይወት ታሪክና የትግል ዓመታት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ፎቶ (ስላይድ) የቀረበ ሲሆን ከኬክ መቁረሱ ሥነስርዓት በተጨማሪ ግጥምና የልደት መዝሙር ለበዓሉ ማድመቂያነት ቀርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ … [Read more...] about አቶ አንዳርጋቸው – 60ዓመት
ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም!
አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል። ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። … [Read more...] about ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም!
“ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም የካቲት 3/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉን የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሰልፉ ወቅትም ነዋሪዎቹ መንግስት ለአካበቢው ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ 10 ከተሞች ላይ መብራት በራሳቸው ገንዘብ ማስገባታቸውን፣ ትምህርት ቤቶችን ራሳቸው እንደሰሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን የተዘረጋው በህዝቡ ወጭ መሆኑን፣ መንግስት ሰራሁት ያለው ውሃ ከሶስት ሳምንት በኋላ መበላሸቱ ሙስና እንደተበላበትና እንዳልተሰራ እንደሚያምኑ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰልፈኞቹ "ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል፣ ስራ አጥተው … [Read more...] about “ልማት ስለሌለ ልጆቻችን ስደተኞች ሆነዋል”
ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን)
ቫላንታይንስ ዴይ (ፍቅረኞች ቀን) ከወደ ምዕራቡ ከተዋስናቸው ወይም ከተጫናቸው በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በእኛ ዘንድ አሁን ያገኘውን ያህል ተቀባይነት እንዲያገኝ ከማድረግ አንጻር የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤፍ ኤም ሬዲዮዎች(ነጋሪተ ወጎች) ዐቢዩን ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የብሔራዊው የብዙኃን መገናኛውና ሌሎች የሬዲዮ (የነጋሪተ ወግ) ጣቢያዎችም እንደዚያው ቁምነገሬ ብለው ይዘውታል፡፡ የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤሌክትሮኒክሱ (በአየር ሞገድ የሚሠራጨው) በመልካም ጎንም ይሁን በመጥፎ ጎን ለሚመጣ ውጤት ታላቅ ጉልበት አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ባጠቃላይ ለደረሰብን የባሕል ወረራና ጥቃት በዚህ የብዙኃን መገናኛ ከበጣም ጥቂቶቹ በስተቀር “የመዝናኛ ዝግጅት” በሚል ሥያሜ የአየር ሰዓት የወሰዱ እንደዜጋ የሀገርንና የሕዝብን እሴት ሀብት የመጠበቅ ኃላፊነትና … [Read more...] about ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን)
በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ!
ከአንድ አመት በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ወደሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጉረፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ከነበረው ስርዓት አልበኝነት ህይወታቸውን ለመታደግ አቅሙ የቻለ ጎረምሳ ልብሶቹን በሻንጣ አጭቆ እግር አውጭኝ ሲል አይን ያልገለጹ ህጻናት ልጆቻቸውን በወጉ መሰብሰብ ያልቻሉ እናቶች ለክፉ ቀን ትሆነኛለች ብለው ገዝተው ያስቀመጡጥን ወርቅ እና የተለያዩ ጌጣጌጦቻቸውን የያዘች አነስተኛ ሻንጣ አንጠልጥለው ከቀማኞች ይታደገናል ወዳሉት በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ቅጠር ግቢ በማቅናት ለተውሰኑ ቀናቶች በመጠለል ሻንጣዎቻቸው በካርጎ ጭነት እንደሚላክ ቃል ተገብቶላቸው ብጣሽ ጨርቅ እንኳን ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገር … [Read more...] about በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ!
“ፍቅር እስከ መቃብር” በሰሜን ዋልታ
ዶክተር ሬዶልፍ ክኑት ሞልቨር (Reidulf Knut Molvær) የ77 ዓመት ኖርዌጂያዊ አዛውንት ናቸው። ዋና ሙያቸው የሥነ ጥሑፍ፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪነት ነው። በአማርኛ ሥነ ጽሁፍና ቋንቋ ጥናት ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ያገኙ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 14 ኬንያ ውስጥ ደግሞ 6 ዓመታትን ባለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በመሥራት አሳልፈዋል። የትዳር ጓደኛቸው ኬንያዊት ሲሆኑ፣ አራት ልጆችም በጋራ አፍርተዋል። ከልጆቻቸውም መካከል አንዱ የሕክምና ዶክተር፣ ሁለቱ ኢንጂነሮች ሆነዋል። ዶ/ር ሞልቨር ለፍልስፍና ማስትሬት ድግሪያቸው መመረቂያ አዘጋጅተውት የነበረው ጥናታቸው ቀዳሚውን እውቅና አስገኝቶላቸው የነበረ ነው። ይህን ጥናታቸውን “ልማድና ለውጥ በኢትዮጵያ - Tradition and Change in Ethiopia: Social and … [Read more...] about “ፍቅር እስከ መቃብር” በሰሜን ዋልታ
ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!
* ኢንቨስተሮች “የደም ከፈን” ላለመግዛት ወሰኑ በኦሞ ሸለቆ ድሆችን ከመሬታቸው በማባረር የሚያመርተውን ጥጥ ወደ ውጭ ለመላክ ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢህአዴግ ባለፈው ሰሞን ያልጠበቀው ምላሽ ደርሶታል፡፡ ምላሹን ተከትሎ የጥጥ ግብይቱ የጨነገፈው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መሆኑን በገሃድ አመነ፡፡ በኢህአዴግ ስትራቴጂክ በሆኑ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድሞ የመልስ ምት በመምታት ፈተናው ውስጥ የከተታቸው አኢጋን እና መሪው ኦባንግ ሜቶ መዋቅራቸው ሊገኝ አለመቻሉ ኢህዴግን እንዳስጨነቀው ተሰማ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በሰማሁት ተዝናንቻለሁ ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አሜሪካ መከተል የሚገባትን አካሄድ በመዘርዘር ለፕሬዚዳንት ኦባማ ፖሊሲ ሊያስቀይር የሚችል ደብዳቤ ልከዋል፡፡ ኢህአዴግ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ በቦታቸው ላይ ጥጥ … [Read more...] about ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!