በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በሌሙና- ቢልቢሎ ወረዳ ሌሊት ላይ መኖሪያ ቤት የገባ አንድ ጅብ በሰውና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ጎሳ አማን እንደገለጹት፥ ጅቡ በሰውና እንስሳት ላይ ጥቃት ያደረሰው በሌሙዲማና ሁላሃሳ የገጠር ቀበሌ ነው። የካቲት 10 ቀን 2007 ከሌሊቱ 10 እስከ 11 ሰዓት በሁለት አርሶ አደሮች የእንስሳት በረትና መኖሪያ ግቢ በመግባት በሁለት አባወራና ስምንት የቤት እንስሳት ላይ ንክሻ መፈጸሙን ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የቤት እንስሳቱን ከጅቡ ለማስጣል በገጠሙት ግብ ግብ የተደናገጠው ጅብ ወደ ጭላሎ ተራራ ሊያመልጥ መቻሉን አስታውቀዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል አንደኛው ብልታቸው ላይ ሌላው አርሶ አደር ደግሞ በሆዳቸውና ሌላ አካላቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት አሰላ … [Read more...] about በአርሲ ጅብ በሰውና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ
Archives for February 2015
“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤ ... ሰማንያ አንድ ዜሮ ዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣ አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። .... 8100 .... 8100 .... 8100-A A A የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም። አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ። በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ 'A' ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው። … [Read more...] about “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
የኢትዮጵያ ጉዳይ
ግልፅ ደብዳቤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገር ማለት ባሕርዳር ዛሬም ስለልጆቿ አነባች የአምባገነኖች አከርካሪ በተባበረ የሕዝብ ክንድ ይሰበራል በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደልና ጾታዊ ጥቃት ይቁም ኢትዮጵያዊነት በዘር ማንነት አይደበዝዝም ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ትግል በቀላሉ አይቀለበስም ፖሊስና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ መጽሔቷ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ታተማለች፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ
ህወሃት ምንድን ነው?
በቅርቡ የህወሃት ኣርባኛ ዓመት ለየት ባለ መንገድ መከበሩ ገርሞኛል። በየዓመቱ እንደሚከበር ሁላችን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የዓርባኛ ዓመቱ በዓል እንዲህ ለምን እንደተወራለት ለምን የሌላ ኣገር መሪ ሳይቀር እንደተጋበዘበት ኣልገባኝም። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ለየት ያለ ድግስ የሚደረገው የኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር ነው። የሆነው ሆኖ የመነሻ ኣሳቤ ይሄ ኣይደለም። ህወሃት ኣርባኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር እኔ በህወሃት ተፈጥሮ ስደመም ነበር። በርግጥ ኢትዮጵያ ኣሁን ላለችበት የተመሰቃቀለ ህይወት ሲንከባለሉ የመጡ ኣንዳንድ ችግሮች ኣስተዋጾ ቢያደርጉም የችግሩ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድራጊ ግን ህወሃት ነው። በየክልሉ የህወሃት ተከታዮች ኣስተዋጾኣቸው እንዳለ ሆኖ የህወሃት ድርሻ ግን በጣም ገዝፎ ይታያል። ግን …ግን ለምንድነው በህወሃት መራሹ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ኣስከፊ … [Read more...] about ህወሃት ምንድን ነው?
“የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ”
ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት ሴቶችን በሚመለከቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን ችግሮች በተለይም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በአረብ አገራት ተሰደው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብትን አስመልክቶ በየጉባኤዎቹ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ውይይቶች አካሂዷል። ዘንድሮም የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ለ፬ኛ ጊዜ የሚካሄድ ዓመታዊ ጉባኤ … [Read more...] about “የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ”
“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል
“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለው ጥሬ ንባብ፤ ስለ ጅብና ስለ ቁርበት መልእክት ለማስተላለፍ አይደለም። ጅቡ የሚወክለው አካል አለ። ቁርበቱ የሚወክለው ነገር አለ። በቁርበቱና በጅቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ሳያውቁ ቁርበቱን ለጅቡ ያነጠፉለትም የሚወክሉት አለ። ይህ አገላለጽ በኢትዮጵያዊው ቅኔ ትምህርት፣ ቀመር፣ ስልት ሲመዘን፤ ጅቡ ሰም ነው። ቆርበቱም ሰም ነው። ሁሉም ሰም ነው። ወርቁ ከሰሙ ጋራ ጎን ለጎን ባለመቀመጡ፤ ወርቅ የጎደለው ‘ሰማ-ሰም’ ይባላል። ወደ ጠቅላላ ይዘቱ ስንገባ፤ በጅብና በቁርበት መካከል ያለው ግንኙነት፤ በተበይና በበይ መካከል ባለው ግንኙነት ብቻ ሳይወሰን፤ የተደራረበ ሰይጣናዊ የአጠቃቀምን ዘዴ ይጠቁማል። ጅብ ቁርበቷን እንደሚበላት በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበቷን ‘አንጥፉልኝ ’ እንደሚል፤ አንዳንድ ሰዎችም በሚታወቁበት … [Read more...] about “ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል
እውን ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚደነቅ የሚከበር ነገር አለውን?
በእስካሁኑ ግፍ ያልጠፋኸው ነገር ግን ለማይቀርልህ ወገኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እንኳን ለአጥፊህ ለወያኔ ሐርነት ትግራይ 40ኛ ዓመት የልደት በዓል አደረሰህ! የዚህች ሀገር ነቀርሳ በውስጧ የበቀለበት 40ኛ ዓመት እነሆ ከነገ ወዲያ እሮብ የካቲት 11 2007ዓ.ም. ይከበራል፡፡ ግን ወያኔ ማን ነው? እውን የሚከበር የሚያኮራ ማንነት አለው? ነው ወይስ የሚረገምና የሚያሳፍር? ከዚህ ቡድን ውስጣዊ ታሪክ እንደምንረዳው ይህ ቡድን በርዕዮተ ዓለምና በአስተሳሰብ ልዩነት በግል ጥቅምና በሥልጣን ሽኩቻ አንዱ ሌላውን እየበላ አንዱ በሌላው እየተበላ እርስ በእርስ እንደ አውሬ እየተባላ እየተጠፋፋ በመጨረሻ በአውሬነቱ የበረታው የበረታው አስከፊው አስከፊው ቀርቶና ተቧድኖ ለዚህ የደረሰ እኩይ ሰይጣናዊ ቡድን ነው፡፡ የወያኔን የትግል ታሪክ ስናይ ከቀደምቶቹ የሕወሀት አባላት ጥለው ከወጡትም … [Read more...] about እውን ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚደነቅ የሚከበር ነገር አለውን?
ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ። በዚህ በለንደን የፍርድ ቤት ችሎት የቤተ ክርስቲያኗን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤትን በሕገ ወጥ መንገድ በመያዝ ከስልጣናችን አንለቅም በሚል መንገታገት በቤተ ክርስቲያኗም ሆነ በአባላቱ ላይ ከፍተኛ ምስቅልቅልን ያመጡ ግለሰቦች በሚወክላቸው ጠበቃ አማካኝነት 1) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለመግዛትም ሆነ ቤተ ክርስቲያኗን በሃብትና በንብረት ለማደርጀት ያፈሰሱት ሃብትና ጉልበታቸው በስጦታ መልክ የተደረገ ስለሆነ ከልገሳ ባለፈ የቤተ ክርስቲያኗ ሃብትና ንብረት ተጋሪ (Beneficiaries) ስላልሆኑ የመወሰንም ሆነ ይህ ይደረግ የማለት መብት አይኖራቸውም፤ 2) የቤተ ክርስቲያኗ … [Read more...] about ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ
ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት ዲፕሎማቶች ምንም ዓይነት መረጃ የላቸውም፡፡ አደጋው የደረሰባት ወጣት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኗን የሚናገሩ የዜናው አቀባዮች ወጣቷ እንደተራራ የገዘፈውን ህይወት በመጋፈጥ ቤተስቦቿን ከችግር ለመታደግ በወቅቱ ከነበሩ የኤጀንሲ ደላላዎች ጋር ተዋውላ ሳውዲ አረቢያ ለስራ መምጣቷን ይናገራሉ። በተጠቀሰው ውል መስረት ወጣቷ አሰሪዋ የወር ደሞዝዋን በየወቅቱ እንዲከፍላት ለማስረዳት ብትሞክረም ከኢትዮጵያ ከመጣች ጀምሮ ላለፉት ሁለት አመት ያለደሞዝ ለመቆየት መገደዷን ለመረዳት ተችሏል። ሰሞኑን ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ … [Read more...] about በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ
ዘጸአት ለኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ምድር፥ ምኒልክን (ዮሴፍን) 'ማያውቅ፥ አዲስ ንጉሥ መ'ቶ፣ "ለነፃነት" ብሎ፥ የነፃነትን ጧፍ፥ ረጋግጦ አጥፍቶ፣ "ከኔ ወዲያ ላሳር!"፥ አለን አፉን ሞልቶ፣ ያ'ባቶችን ክብር፥ አፈር መሬት ከ'ቶ። ያገሬ ፈርዖን፥ ልቡ እጅግ ደንድኖ፣ የፈጣሪን ፈቃድ፥ እንዳይሰማ ሆኖ፣ "እንደ'ኔ ያለ ንጉሥ!"፥ እያለ ይጽናናል፣ የበትሩን ምሬት፥ በጠገበ ጉልበት፥ ከተማን ያጸናል። ስንት አሮን ተላከ? ስንት ሙሴ መጣ? "የሠራዊት ጌታ፥ 'ህዝቤን ልቀቅ' ይላል!"፥ የሚል ቃል ሊያወጣ፣ ስንት ምርጫ ሆነ፥ ስንት ምርጫ ሄደ፣ ደንዳናው ፈርዖን፥ በህዝብና ፍትህ፥ እንደተጓደደ። ምልክቶች ታዩ፥ ታምራትም መጡ፣ ፈተናው ጸና እንጂ፥ የእብሪተኞችን ልብ፥ ቅንጣት አ'ለወጡ። የባሰው መጣና፥ የ'እብራውያን' በኩር፥ እየተሰደደ፣ መልአከ ሞት ጥላ ፥ 'የፈርኦንን በኩር'፥ … [Read more...] about ዘጸአት ለኢትዮጵያ