
ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ እንዲሁም በUK እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ።
በዚህ በለንደን የፍርድ ቤት ችሎት የቤተ ክርስቲያኗን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤትን በሕገ ወጥ መንገድ በመያዝ ከስልጣናችን አንለቅም በሚል መንገታገት በቤተ ክርስቲያኗም ሆነ በአባላቱ ላይ ከፍተኛ ምስቅልቅልን ያመጡ ግለሰቦች በሚወክላቸው ጠበቃ አማካኝነት
1) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለመግዛትም ሆነ ቤተ ክርስቲያኗን በሃብትና በንብረት ለማደርጀት ያፈሰሱት ሃብትና ጉልበታቸው በስጦታ መልክ የተደረገ ስለሆነ ከልገሳ ባለፈ የቤተ ክርስቲያኗ ሃብትና ንብረት ተጋሪ (Beneficiaries) ስላልሆኑ የመወሰንም ሆነ ይህ ይደረግ የማለት መብት አይኖራቸውም፤
2) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት መብታችን ይከበርልን በማለት አሁን በጽ/ቤት የሚገኙትን ትረስቲዎች (የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት) ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት የላቸውም፤
3) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጠውን አገልግሎት ከመቀበል ውጪ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የመብት ጥያቄ ማንሳት አይችሉም፤
4) በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደርም ሆነ ሃብትና ንብረት ወሳኙና አዛዡ ኢትዮጵያ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው፤
5) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ቤተ ክርስቲያኗ ከተከፈተች ጀምሮ የአባልነት መዋጮአቸውን ስላልከፈሉና አባላት መሆናቸውንም ማረጋገጫ ሰለሌላቸው አናውቃቸውም፤
6) የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በ2013 ተሰብስበው የመረጧቸውን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት (Trustees) ትክክለኛ ትረስቲ ስላልሆኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት የላቸውም የሚሉና በአጠቃላይ ከአባላት መብት ጥያቄ ጀምሮ የጉዳዩ በፍርድ ቤት መሰማት ድረስ ያለውን ሁሉ በመቃወም አቅርቧል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply