• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል​

February 18, 2015 08:00 am by Editor Leave a Comment

“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለው ጥሬ ንባብ፤ ስለ ጅብና ስለ ቁርበት መልእክት ለማስተላለፍ አይደለም። ጅቡ የሚወክለው አካል አለ። ቁርበቱ የሚወክለው ነገር አለ። በቁርበቱና በጅቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ሳያውቁ ቁርበቱን ለጅቡ ያነጠፉለትም የሚወክሉት አለ። ይህ አገላለጽ በኢትዮጵያዊው ቅኔ ትምህርት፣ ቀመር፣ ስልት ሲመዘን፤ ጅቡ ሰም ነው። ቆርበቱም ሰም ነው። ሁሉም ሰም ነው። ወርቁ ከሰሙ ጋራ ጎን ለጎን ባለመቀመጡ፤ ወርቅ የጎደለው ‘ሰማ-ሰም’ ይባላል።

ወደ ጠቅላላ ይዘቱ ስንገባ፤ በጅብና በቁርበት መካከል ያለው ግንኙነት፤ በተበይና በበይ መካከል ባለው ግንኙነት ብቻ ሳይወሰን፤ የተደራረበ ሰይጣናዊ የአጠቃቀምን ዘዴ ይጠቁማል። ጅብ ቁርበቷን እንደሚበላት በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበቷን ‘አንጥፉልኝ ’ እንደሚል፤ አንዳንድ ሰዎችም በሚታወቁበት አገር ቢያደርጉትና ቢሰሩት ተቀባይነት የማያገኙበትን፤ ይልቁንም የሚዋረዱበትን ነገር፤ በማይታወቁበት አገር ሄደው እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ለማስደረግ የሚጠቀሙበትን ዘዴ ይገልጻል።

ማታለልን ለመንቀፍና የመታለልንና የማታልያንንም ዘዴ ለመግለጽ “ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለውን ሰማ-ሰም ምሳሌያዊ ከእኛ በፊት የነበሩ ኢትዮጵያውያን መጠቀማቸው የጅቡ ባህርይ የሚታይበት ሰው መንቀፍ ተገቢ መሆኑን ለማሳየት ነው። የጅቡን የማታለል ባህርይ ሳያውቁ ቆዳዋን ባነጠፉ ሰዎች ምሳሌነት የሚቀርቡትም፤ አታላይ ሰው ባገሩ ውስጥ የማያገኘውን፤ ይልቁንም የሚነቀፍበትንና የማይመጥነውን ክብር ሳያውቁ በማቅረባቸው ባይነቀፉም፤ መታለላቸውን እንዲያውቁ ሊገለጽላቸው እንደሚገባ ለማስተማርም ነው።

የፊደላችን፤ የስነ ጽሑፋችንና የበጎ ባህላችን ምንጭ የሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን በሰጠችን መነጸር ይህን አባባል ስንመለከተው፤ የማታለል ባህርይ መነቀፍ እንዳለበት፤ የሚታለሉ ሰዎችም እንደተታለሉና ዳግም እንዳይታለሉ መነገራቸው አገባብነት እንዳለው እንረዳለን።

ነቀፌታ ተገቢ ባይሆን ኖሮ፤ መገኘት በማይገባው ቦታ አስመስሎ በመግባት ሲያታልል የተገኘውን ሰው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ እጅ እግሩን አስራችሁ አውጡት “ (ማቴ 22፡11-13) ባላለ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም “በውጭ ባሉ ሰዎች መፍረድ ምን አግዶኝ። በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉት እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡ ” (1ኛ ቆሮ 5፡12 ) ባላለም ነበር። ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በሆነ ቡድን ወደ መንፈሳዊ አመራር የሚመጣውንም መንቀፍ ክልክል ቢሆን ኖሮ፤ የቀኖና መጽሐፋችን በምድራዊ ኃይልና ድጋፍ የሰየመውንና የተሰየመውን ምቱራን ( ህይወት አልባ ሆነው የተወለዱ ናቸው) ባላላቸውም ነበር (ፍ.ነ. ፻፸፭) ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule