• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”

February 22, 2015 05:32 am by Editor 1 Comment

ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤

… ሰማንያ አንድ ዜሮ ዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣

አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። …. 8100 …. 8100 …. 8100-A A A

የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም።

አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ።  በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ ‘A’ ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው።  እናት መለሱ “ሁሉም ነገር አለኝ። ዲግሪ ግን የለኝም። በዚህ እድሜየም  በአቋራጭ ካልሆነ ላገኘው አልችልም።” ሲሉ የማስትሬት ዲግሪው እጣ እንዳጓጓቸው ነገሩት።

8100ሶስት ብር ከፍሎ ‘8100-A’ አጭር መልዕክት የላከ ሰው ሁሉ እጣ ይወጣለታል። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ እድሉ የቀናው ሰው የመኖርያ ቤት፣ መኪና፣… እንዲሁም ዶክትሬትና ማስትሬት ዲግሪ ይደርሰዋል።

ማስትሬት እና ዶክትሬት ዲግሪ በእጣ እንዴት ነው ለህዝብ ሊቀርብ የሚችለው? መሰረታዊ ትምህርት የሌለው  አንድ አርሶ-አደር አልያም አንዲት የቤት እመቤት የዶክትሬት ዲግሪ እጣ ቢደርሳቸው ዩኒቨርሲቲ ገብተው ዲግሪያቸውን ሊጭኑ ነው? ብቻ ምን ችግር አለ? ለመዕተ-ዓመቱ እቅድ ማሟያ ተብለው የተሰሩት ፴ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ። ምሁራንን ሳይሆን ‘ድንጋይ ማምረቻ’ እየተባሉ የሚተቹ ዩኒቨርሲቲዎች። የኮሌጅን መስፈርት በአምስት በመቶ እንኳን የማያሟሉ ባዶ ህንጻዎች። ከነዚህ ኮሌጆች እየተመረቁ የሚወጡት ተማሪዋች ስማቸውን እንኳን በቅጡ መጻፍ አይችሉም የሚባሉበት ኮሌጆች።

ለነገሩ በስልጣን ላይ ያሉትም ሁሉ ዛሬ የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤቶች ሆነዋል። ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና ይግባውና እነ አባዱላ ገመዳም ማስትሬት ዲግሪ ገዝተዋል። ጀነራል ባጫ ደበሌም ሁለት ዲግሪ ጭነዋል።

ያልተጠና እና ግብታዊ በመሆኑ ይመስላል የ 8100-A ዘመቻ መቀለጃ እየሆነ መምጣቱ። ኢሳያስ አፈወርቂም የዚህ እጣ እድል ደርሷቸዋል አሉ። ባለፈው ሰሞን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባ የነበረው ካፒቴን የህወሃትን ስርዓት በመቃወም ይዞት የጠፋውን ሚግ 23 አውሮፕላን ለአስመራው መንግስት እንዳስረከበ ነበር ይህ ቀልድ የተነገረው።

የዚህ ጽሁፍ ዋናው ጉዳይ የትምህርት ማሽቆልቆል ነገር አይደለም። የ 8100-A ዜማ እንዳበቃ  ባናቱ ላይ የሚነገር አንድ መልእክት ላይ እንጂ። የሰማንያ አንድ ዜሮ-ዜሮ ቁልፍ በእዚህ መልእክት ላይ ይገኛል።

“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን?”

ምን ማለት ነው? ላይጨርሱት ኖሯል እንዴ የጀመሩት? አባባሉ የጀመሩትን የመጨረስ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳሉ ፍንጭ ይሰጠናል። ፍጹም በግብታዊ በሆነ፣ በዕውቀት እና ዕቅድ ላይ ያልተመረኮዘ፣  የባለሙያ ክህሎት ያልነበረው ጅምር መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።

“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!” መፈክር ሆነ። እድገት የሚመጣው በመፈክር ሳይሆን በስራ ነው። ስራ ደግሞ በእውቀትና በእቅድ እንጂ በስሜት አይከወንም።

ሃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ስልጣን ላይ ጉብ ያሉ ሰሞን ደጋግመው የሚሉት ነገር ነበር። “እዚህ የተቀመጥቁት መለስ የጀመረውን እቅድ ሁሉ ለመጨረስ ነው።”

ይህን ካሉን ሶስት አመታት አለፉ። ሃይለማርያም ደሳለኝ የጨረሷቸውን ፕሮጀክቶች ስንፈትሽ አንድ ነገር ብቻ አገኘን። እሱም የጸረ-ሽብር አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ የህሊና እስረኞችን ቁጥር መጨመር ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ በገዢው ፓርቲ ተጀምረው የተጨረሱ ነገሮች የሉም። ሌሎቹን ለግዜው ተወት አድርገን የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ብቻ እንቃኝ።  አስራ አንድ ግድቦች ተጀምረዋል። ግን ሁሉም አላለቁም። ለምን? በዚህ ላይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ።

ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የተጀመሩት የመስኖ እርሻ እና የሃይድሮ-ኤሌክትሪክ ልማት ፕሮጀክቶች በርካታ ናቸው። የተንዳሆ ግድብ፣ የከሰም ግድብ፣ የርብ ግድብ፣ የጊዳቦ ግድብ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብ፣ የራያ አዘቦ ግድብ፣ የቆቦ ጌራ ግድብ፣  አድአ በቾጠ ግድብ፣ የቆጋ ግድብ፣ የመገጭ ግድብ፣ እንዲሁም የጉደር እና ዳቡስ ግድቦች ናቸው። በ፩፱፱፯ ዓ.ም  በአፋር የተጀመረው የከሰምና የተንዳሆ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ  አመታት አለፉት። የታቀደለት ጊዜ ከ ፭ አመት በፊት ቢያልፍም ስራው ገና አልጀመረም። በ፪፻፪ ዓ.ም የተጀመረው የርብ ግድብ ግንባታ፣  የጊዳቦ ግድብ ግንባታ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብና መስኖ ልማት፣ የራያ አዘቦ መስኖ ልማት፣ የቆቦ ጊራ መስኖ ልማት፣ አድአ በቾጠ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ ግዚያቸውን በልተው የኤሊ ጉዞ ላይ ናቸው።  ግንባታው በ፪፻፬ የተጀመረው የቆጋ መስኖ ልማት፣ የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ላይኛው ጉደር መስኖ ልማት፣ ዳቡስ መስኖ ልማት … ተጀምረው ቆመዋል።…እነዚህ እንግዲህ “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!”  ያልተባሉ ፕሮጀክቶች ናችው። ምክንያቱም የፖለቲካ ጠቀሜታቸው ይህን ያህል ስላልሆነ።

እርግጥ ነው። በመጀመሪያው “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ውስጥ የአባይ ግድብ ፕሮጀክት አልነበረም። ከበጀቱም ውጭ ነው። ስለሆነም አጀማመሩ ድንገት ነበር። ጥናት ሳይጠና፣ ሳይመከር፣  በጀት ሳይያዝ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው።  አባይ በባዶ ተጀመረ። የቦንድ ሽያጭ ተሞከረ።…እንዲህ እያለ ሎተሪ ላይ ደረሰ… ይህ ብዙ እንዳላስኬደ በግልጽ ይታያል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር በስሜት እና በግብታዊነት ስለሚሰራ የአጭር ጊዜን እንጅ ረጅሙን አያዩትም። በመጨረሻ ግን ግዜው ደርሶ ማጠፊያው ሲያጥራቸው ይታያሉ።  የዚህ ፕሮጀክት አጀማመር በእርግጠኝነት አባይን ገድቦ ልማት ላይ ለማዋል ተብሎ ሳይሆን ከወቅታዊው የስልጣን ችግር ለማምለጥ የተወጠነ  እቅድ ነበር። ለግዚያዊ ጥቅም ተብሎ እንደቀልድ የተጀመረው ነገር አሁን የህዝብ እምሮ ውስጥ ስለገባ ይመስላል ቅኝቱን ያስተካከሉት። … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!

የአባይ ጉዳይ ለገዥው ፓርቲ  ህልውና ወሳኝ ነገር ተደርጎ ተወስዷል። ከኢኮኖሚው ይልቅ የፖለቲካ ጠቀሜታው ቀላል አይደለምና።  የኢኮኖሚውን ጠቀሜታ ቢመለከቱ ኖሮ አባይን መገደብ እንደሚያወሩት ከባድ አልነበረም። ገዥው ፓርቲ ለሃገር ካሰበ ገንዘቡም ቅርብ ነው። የዜጎች ደሞዝ ሳይቆረጥ፣ ቦንድ ሳይሸጥ፣  ህዝብ ሳይቸገር፣ ቀረርቶ ሳይነፋ… አባይን መገደብ ይቻላል። የኤፈርት ገንዘብ ብቻ አንድ ሳይሆን ሃምሳ አባይን ይገድበዋል። በግል ከተዘረፈው 16ቱ ቢሊየን ዶላር ሳይነካ ማለት ነው።

አባይ ተገድቦ አገልግሎት ቢሰጥ መልካም ነገር ነው። ይህ ጎስቋላ ህዝባችንም ከድህነት አረንቆ ሲወጣ ብናይ ሁላችንም ደስታችን ነው።ዲያስፖራውም አባይ ተገድቦ ማየት ይፈልጋል።  ችግሩ ያለው ግልጽነት እና ቅንነት በጎደለው በዚህ መልኩ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ብቻ በመከናወኑ ነው። ችግሩ ያለው በልማት ስም በሚደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ነው። አባይን ከመገደቡ በፊት የመብት ረገጣው ቢገደብ ዲያስፖራውም በዚህ ላይ በተረባረበ ነበር።

“እድገትና ትራንስፎርሜሽን” የተባለው “ቅኝት” አምስቱን አመት እንደዋዛ ዘልቆታል። የተባለው ለውጥ ግን አልታየም። ሃይለማፘም ደሳለኝ ፓርላማ ላይ ጉብ ብለው በእቅዱ አፈፃፀም የነበሩ ተግዳሮቶችን ዘርዝረውልናል። አፈጻጸም አሉን እንጂ ነገሩ ሌላ ነው። ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ህዝብ የሚተዳደርበትን የግብርናውን ዘርፍ  ለማሻሻል የታቀዱ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ አልሆኑም። የገጠር መንገዶች ሰባ በመቶ እንደሚሰሩ ቅኝቱ ላይ ነበር። ይህም ፈጽሞ ሊሆን አልቻለም። አሁን ያለውን አስር በመቶ የኤሌትርክ ሃይል ተጠቃሚ በሰማንያ አምስት በመቶ ለማሳደግ ቃል ገብተው ነበር። ወጤቱን ስናየው ግን የነበረው አስር በመቶም ወደ ፈረቃ አሽቆልቁሎ መሄዱን ነው።

በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ታምቦ ምቤኪ የሚመራው የጥናት ቡድን ባለፈው ወር ከሂልተን ሆቴል የለቀቀው ዘገባ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ስለዘረፋው አስደንጋጭም አስረጋጭም ነበር። ከኢትዮጵያ ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 16.5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አረጋግጦልናል።  ይህ አስደንጋጭ ዘገባ ከዚህ ቀደም Global Financial Integrity (GFI) አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ዘገባ ላይም ወጥቷል።  የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽባል ዘገባ እንደሚለው ከሆነ ከተዘረፈው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከሃገር የወጣው በእድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ ዘመን ነው።

ሌላም አስደንጋጭ ነገር አለ። ኢትዮጵያ በዘመነ ህወሃት በዋስትናም ሆነ ያለዋስትና የተበደረችው እዳ 40 ቢሊየን ዩ.ኤስ.ዶላር ደርሷል። ይህን የዘገበው ላሙዲ የተባለው አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ነው። ይህ እዳ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሰላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ባለ እዳ እንደሆነ ይጠቁመናል። ይህ ገንዘብ ለልማት መዋል ሲኖርበት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሀገር እየወጣ መሆኑን ነው እንዚህ አለም አቀፍ ተቋማት እየነገሩን ያለው።

በዚህ በኩል የ”ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ” ዘመቻ፣ በዚያ በኩል ደግሞ ዘረፋው ሊጣጣሙ አልቻሉም። የሚወጣው ከገቢው አልተስተካከለም። ዘረፋው ግዙፍ ነው። በዚህ ሁኔታ ነው መፈክር እየተሰማ ያለው። “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!”

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ከኬን ኦሃሺ ስለ መፈክሩ ቅኝት የተናገሩት የሚያስደምም ነው።

“ኢትዮጵያ … ተዓምራዊ በሆነ መልኩ የነዳጅ ክምችት ጉድጓድ ካላገኘች ወይንም ያልተጠበቀ – ነፋስ አመጣሽ የሆነ ገንዘብ ከሰማይ እንደ መና ካልወረደ በስተቀር (እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ) በምንም ዓይነት መልኩ ቀጣይነት ያለው መሆኑ አይታየኝም… እንደዚህ ያለውን በኃይል እና በመፈክር የተሞላ እና የውስጥ ችግሩን በጥልቅ ያልተመለከተ ዕቅድ እንዴት ሊያስቀጥሉት እንደሚችሉ የሚታየኝ ነገር የለም። እንደ ሀገር በቂ የሆነ ጥሪት መቆጠብ እስካልተቻለ ድረስ ምንጊዜም ቢሆን ጥገኛ የሚሆነው በውጭ መዋዕለ ንዋይ፤ አልያም ደግሞ ጤናማ እና ቀጣይነት በሌለው የመዋዕለ ንዋይ መሰብሰቢያ መንገድ ነው… እንደዚህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ነው ተወጥረው ያሉት…

“ዕዳ ካለ አደጋ አለ … ይህ የመንግስት-መራሹ ኢንቨስትመንት ዕድገት አንድ ቦታ ላይ ቢቆም ወይም ለጥቂት ጊዜ መንቀሳቀስ ባይችል እና ቢንገዳገድ እነዚህ ሁሉ የብድር ዕዳዎች ይመሰቃቀላሉ … የግል ዘርፉን ባላሳተፈ እና ጠንካራ ሆኖ ባልተስፋፋበት መልኩ የሚመጣ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት ዘለቄታ እንደማይኖረው እና፤  ይህ ከሆነ እነዚህ በጊዜ ሂደት የሚደረጉ የብድር ዕዳዎች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸው እጅጉን ያሳስበኛል።”

ሲሉ ለገዥው ፓርቲ ዱብዳ የሆነ ይህን እውነታ አፍረጥርጠውታል። እውነታው ይህ ነው። ሳይጨመርና ሳይቀነስ የቀረበ የገለልተኛ አካል ምልከታ።

ሁላችንም በአንድነት እንዲህ እንበል። አባይ ይገደባል። ከአባይ በፊት ግን የመብት ረገጣው ይገደብ!

በሰሞኑ ቀልድ ልሰናበት። ጎተራ አካባቢ ነው። መብራት ፈረቃውን ተከትሎ ጠፍቷል። የሰፈሩ ማጅራት መቺ ምሽቱን ተገን በማድረግ ፍተሻ ጀምሯል። ጸዳ ያለ መኪና አቁሞ ወደ ቅምጥ ቤቱ እየነካ ያለውን ስውዬ አስቆመው።

“ቁም! ሳተበላሽ ገንዘብህን በሙሉ አስረክብ!”

“ምን ነካህ!  እኔ’ኮ ባለስልጣን ነኝ።  ምንስቴር!” ባለስልጣኑ መለሰ።

“አሃ!  ክቡር ሚኒስቴር እንግዲያውስ ገንዘቤን አምጣ!”

***

ለዛሬ በዚህ እነሰነባበት። በሚቀጥለው ጽሁፌ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ የምለው አለኝ። የነገ ሰው ይበለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Kebede says

    February 23, 2015 12:35 pm at 12:35 pm

    ክንፉ የተባልክ ጸሃፊ፤ ለመሆኑ ምን አይነት የተጣመመ አመለካከት ነው ያለህ ጃል!! የ8100 ዕጣ የማስትሬት ወይም የዶክትሬት ዲግሪ ዕጣ መኖሩ የሚኖረውን ዕድል እንጂ ሰዎች ማስትሬት ወይም ዶክትሬት ዲግሪ ያገኛሉ ማለት አይደለም፡፡ በተጣመመ አእምሮህና ባለህ የተሳሳተ አመለካከት መርዝህን ዝም ብለህ ትረጫለህ፡፡ ለመሆኑ የአባይ ግድብ የሚገነባው ለገዢው ፓርቲ ነው ብለህ ታስባለህ? በርግጥ የአመለካከት ብቻ ሳይሆን የትምህርትም ድሃ መሆንህን ስለ ዕዳው ክፍፍል ባስቀመጥከው ቀመር ተረድቼዋለሁ፡፡ “ኢትዮጵያ በዘመነ ህወሃት በዋስትናም ሆነ ያለዋስትና የተበደረችው እዳ 40 ቢሊየን ዩ.ኤስ.ዶላር ደርሷል። ይህ እዳ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሰላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ባለ እዳ እንደሆነ ይጠቁመናል። “ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ስንት ነው ልጄ? በምንስ ቀመር ይሄ ብር ተካፍሎ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ለእያንዳንዳችን አደረስከን? ፅፈህ ሞተሃል!! ይልቅ የተበላሸ አዕምሮህን በጠበል ወይም በፀሎት ወይም በዱዓ መፍትሄ ብታገኝለት ጥሩ ነው፡፡ በዚሁ ከቀጠልክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአእምሮ በሽተኛ መሆንህ ነው፡፡ዶማ፤ ከብት፤ ቁራንቁሪ ነገር ነህ!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule