
ኢህአዴግ በ“አሸባሪነት” የከሰሳቸውና ከየመን ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ የወሰዳቸው የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ቅዳሜ በኦስሎ ኖርዌይ ተከብሯል፡፡
በሥፍራው የተገኘው ዳንኤል አለባቸው ለጎልጉል በኢሜይል በላከው መረጃና ፎቶ እንደገለጸው ዝግጅቱ የተደረገው እዚያው ኖርዌይ በሚገኝ “የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት” ነበር፡፡ በበዓሉ ወቅት የአቶ አንዳርጋቸውን ህይወት ታሪክና የትግል ዓመታት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ፎቶ (ስላይድ) የቀረበ ሲሆን ከኬክ መቁረሱ ሥነስርዓት በተጨማሪ ግጥምና የልደት መዝሙር ለበዓሉ ማድመቂያነት ቀርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
Leave a Reply