• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ፍቅር እስከ መቃብር” በሰሜን ዋልታ

February 9, 2015 07:07 am by Editor 1 Comment

ዶክተር ሬዶልፍ ክኑት ሞልቨር (Reidulf Knut Molvær) የ77 ዓመት ኖርዌጂያዊ አዛውንት ናቸው። ዋና ሙያቸው የሥነ ጥሑፍ፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪነት ነው። በአማርኛ ሥነ ጽሁፍና ቋንቋ ጥናት ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ያገኙ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 14 ኬንያ ውስጥ ደግሞ 6 ዓመታትን ባለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በመሥራት አሳልፈዋል። የትዳር ጓደኛቸው ኬንያዊት ሲሆኑ፣ አራት ልጆችም በጋራ አፍርተዋል። ከልጆቻቸውም መካከል አንዱ የሕክምና ዶክተር፣ ሁለቱ ኢንጂነሮች ሆነዋል።

ዶ/ር ሞልቨር ለፍልስፍና ማስትሬት ድግሪያቸው መመረቂያ  አዘጋጅተውት የነበረው ጥናታቸው ቀዳሚውን እውቅና አስገኝቶላቸው የነበረ ነው። ይህን ጥናታቸውን “ልማድና ለውጥ በኢትዮጵያ – Tradition and Change in Ethiopia: Social and Cultural Life as Reflected in Amharic Fictional Literature ca. 1930-1974” በሚል አቢይ ርእስ ስር አስቀምጠው ባለ 365 ገጽ መጽሐፍ እ.አ.አ. በ1980 ዓ.ም- አሳትመው አውጥተዋል። ይህ የበኩር ሥራቸው የብዙ አንባቢያንንና ተመራማሪዎችን ቀልብ የሳበ ሆኖ እስከዛሬ ድረስ ዘልቋል። ለጥቀውም ”ማኅበራዊነትና ማኅበራዊ ቁጥጥር በኢትዮጵያ – Socialization and Social Control in Ethiopia” እ.አ.አ. በ1995 ዓ.ም. አንድ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል።

ከዚህ ሥራቸው ቀጥለውም በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Black Lions – The Creative Lives of Modern Ethiopia’s Literary Giants and Pioneers” በሚል ርእስ የመጀመሪያውን የ33 ኢትዮጵያውያን ደራስያንን ሥራና የሕይወት ታሪክ ያካተተ መጽሐፍ እ.አ.አ. በ1997 ዓ.ም. ላይነ ንባብ አብቅተዋል። ይህም ድንቅ ሥራቸው በዚህ ረገድ የነበረውን የመረጃ እጥረት ክፍተት ለመሸፈን ከፍተኛ እገዛ አድርጓል። ከብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደ ሥላሴ እስከ እኔ ትውልድ ያሉትን ተጠቃሽ ጸሐፍት አካተውበታል።

ሰንበት ብለውም በዚሁ መድበላቸው ውስጥ ያልተካተቱትነ የሁለት እውቅ ኢትዮጵያውያን የሕይወት ታሪኮችና ሥራዎቻቸውን ”የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ ጥናት- Northeast African Studies” በተሰኘ ታዋቂ  ጁርናል ላይ አቅርበው አስነብበዋል። እኒህም ሁለት እውቅ ደራስያን ሻምበል  አፈወርቅ ዮሐንስና ደራሲ ደበበ ሰይፉ ናቸው።

ቀጥለውም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በኢትዮጵያ ሥነ ጥሑፍ፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ማህበራዊ ሳይንስ ዙሪያ እያዘጋጁ በተለያዩ ጉባዔዎችና ጁርናሎች ላይ አቅርበዋል። አሁን በቅርቡ በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም. ደግሞ የክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁን ዝነኛውን ያገራችንን ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ ”ፍቅር እስከ መቃብር”ን ወደ ኖርዌጂያንኛ ቋንቋ “Kjærlighet til graven” በሚል ርእስ ተርጉመው፣ ለንባብ አብቅተዋል። ይህ ወደ ኖርዌጂያን ቋንቋ የተተረጎመው ሥራቸው 607 ገጾች ያለው ሲሆን፣ በኖርዌጂያን አንባቢያን ዘንድ ትልቅ ተነባቢነትንና ተቀባይነትንአግኝቶላቸዋል።

ዶ/ር ሞልቨር ለዚህ ድንቅ ሥራቸው ክብርና ሞገስ ሊሰጣቸው የሚገባችው ታታሪ ሰው ናቸው። ”ፍቅር አስከ መቃብር” ከዚህ ቀደም ወደ ራሽያንና ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋዎች መተርጎሙ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ወደ ኖርዌጂያን ቋንቋ መተርጎሙ፣ በሰሜን ዋልታ የእስካንዲኔቪያን አገሮች ቋንቋዎች የመተርጎም እድሉን ከፍ ያድርገዋል። ይሄውም ወደ እስዊድንኛ፣ ዳንማርኪኛ፣ ፊንማርኪኛና ሳሚኛ ቋንቋዎች የመተርጎም እድሉ ሰፊ ነው። ዶ/ር ሞልቨርን ሳወያያቸው በቀጣይነት ስላሰቧቸው የትርጉም ሥራዎቻቸው ጠይቄያቸው ነበር። ከአማርኛ ሥነ ጽሑፎች ውስጥ የብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀልን “እንቅልፍ ለምኔ” ፣ የአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስን ”ጦቢያ”፣ የደጃዝማች ግርማቸው ተክለ ሐዋሪያትን ”አርአያ”፣ ከኬንያ ሥነ ጽሑፍ ደግሞ የንጉጊ ዋቲያንጎን “Grain of Wheat” ለመተርጎም ከጀመሯቸውና በእቅድ ከያዟቸው ሥራዎች መካከል እንዳሉ አጫውተውኛል። የታዋቂውን ኬንያዊ ደራሲ የንጉጊን መጽሐፍ እንዲተረጉሙ የግድ ሰበብ የሆናቸውም ለሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት እጩ ሆኖ እንዲቀርብ ስለታሰበ፣ ከወዲሁ በኖርዌጂያን አንባቢያን ዘንድ እውቅናውን ለማጠንከርና መንገዱንም ለመጥረግ እንዲያመች እንደሁ ዶ/ር ሞልቨር አልሸሸጉኝም። እኒህ ይበልጡኑ በኢትዮጵያ ሥነ ጥሑፍ፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ማህበራዊ ሳይንስ ዙሪያ ጥብቅ ምርምር ሲያደርጉ የኖሩ ሰው፣ ከዚህ ቀደምም አንድ በኪስዋህሊ ቋንቋ የተጻፈ የኬንያ ሥነ ጽሑፍ ወደ ኖርዌጂያን ቋንቋ መተርጎማቸውም ይታወቃል።

ከዶ/ር ሞልቨር ተጨማሪ ሥራዎች መካከል እነዚህም ይገኙባቸዋል

ዶ/ር ሞልቨር ለኢትዮጵያውያን ደራስያንና የቀለም ሰዎች ታላቅ አክብሮትና ፍቅር ያለቸው ሰው መሆናቸውም የሚሰመርበት ጉዳይ ነው። እ.አ.አ. በ2005 ዓ.ም. ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅንን ለኖርዌይ ደራስያን ማኅበር “ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ሽልማት” እጩ ተወዳዳሪ አድርጌ ባቀረብኩበት ሰዓት ከጎኔ ከሞቆማቸውም በላይ፣ በቀጣዩ ዓመት ሎሬት ጸጋዬን ለኖቤል ሽልማት እጩ አድርጎ ለማቅረብ፤ ከእኔና ከጋሼ ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) ጎን ለመሰለፍ ቃል ገበተውልን የነበሩ ናቸው። በሎሬት ጸጋዬ እረፍት ምክንያት ያሰብነው ሳይተገበር በውጥን ቀርቷል።

ዶ/ር ሞልቨር በጅምር የያዙዋቸውን ሥራዎች ጨርሰው ለኖርዌጂያን አንባቢያን አቅርበው ለማስነበብ እንዲያበቃቸው ምኞቴ ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. BELIYU BERHANU says

    October 13, 2017 01:01 pm at 1:01 pm

    IT IS VARY GOOD

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule