• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት

February 14, 2015 08:44 am by Editor Leave a Comment

እጅግ ለተከበሩ ለብፁዕ አቡነ ብርሃነ-ኢየሱስ ደምረው ሱራፌል
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት፤
የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንትና
የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ቤ/ክ ማሕበር ሊቀ መንበር፤

አዲስ አበባ፤
ኢትዮጵያ።

በመጀመሪያ፤ ለብፁዕነትዎ የሚገባ እጅግ ከፍ ያለ የአክብሮት ሰላምታ አቀርባለሁ። በተጨማሪም፤ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደህና፤ በክብርና በሞገስ አደረሰዎ በማለት መልካም ምኞቴን በትሕትና እገልጻለሁ።

በመቀጠልም፤ ሰሞኑን የ1.228 ቢሊዮን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ባላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፤ እጅግ የተከበሩ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳት (ካርዲናል) ሆነው በመሾምዎ፤ እንኳን ደስ አለዎ በማለት፤ ለዓለም ሰላምና ለክርስቲያን አንድነት የሚያደርጉት ጥረት በቸሩ አምላክ ተራዳኢነት እንዲሳካልዎ ልባዊ ጸሎታችንን በትሕትና እናቀርባለን።

የብፁዕነትዎ በዚህ ከፍ ባለ ደረጃ መሾም፤ ታሪካዊ ክስተት በመሆኑ፤ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ የሚያኮራ መሆኑንም እንገነዘባለን። ለሐገራችንም ስለሚያስፈልጋት ፍትሕና ክብር እጅግ ጠቃሚ የሆነ ሚና እንደሚኖረው እናምናለን።

የተጨፈጨፉ የኢትዮጵያ አርበኞች
የተጨፈጨፉ የኢትዮጵያ አርበኞች

ብፁዕነትዎ እንደሚያውቀው፤ ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ዘመን አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈው ነበር። ከነዚሁ ውስጥ፤ በሶስት ቀኖች ብቻ፤ አዲስ አበባ ከተማ፤ 30 000 ሰዎች ተገድለው ነበር። በተጨማሪም፤ 2 000 ቤተ ክርስቲያኖችና 524 000 ቤቶች እንዲሁም 14 ሚሊዮን እንስሳት እንደ ወደሙና እጅግ ብዙ የሐገራችን ንብረቶች እንደ ተዘረፉ የታወቀ ነው። ከተዘረፉት ንብረቶች ውስጥ አሁንም በኢጣልያና በቫቲካን መንግሥቶች ይዞታዎች የሚገኙ አሉ። በቫቲካን ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ከ500 በላይ በፋሺሽቱ በቸሩሊ ጭምር የተዘረፉ የኢትዮጵያ ሰነዶች እንደሚገኙ የታወቀ ነው።

ፋሺሽቶች የኢትዮጵያዊውን ራስ ቆርጠው ሲያሳዩ
ፋሺሽቶች የኢትዮጵያዊውን ራስ ቆርጠው ሲያሳዩ

በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው የጦር ወንጀል፤ በጊዜው በነበሩት ፖፕ ፓየስ 11ኛ ትመረ የነበረው ቫቲካን ከሙሶሊኒና ከፋሺሽቱ አገዛዝ ጋር ተባባሪ የነበረች መሆኑ በታሪክ የተረጋገጠ የማይካድ ሐቅ ነው። ለዚሁም ተጨባጭ ከሆነው ብዙ ማስረጃ ውስጥ፤ በቫቲካንና በሙሶሊኒ መሀል የተፈረመው፤ “ላተራን” የተሰኘው ውል፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ የኢጣልያንን ንጉሣዊ መሪ፤ የኢጣልያ ንጉሥና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በማለት ፖፕ ፓየስ 11ኛ መባረካቸው፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ለፋሺሽቶች የበላይነት እውቅና እንዲሰጡ አንድ ሚሊዮን ስተርሊንግ ፓውንድ ጉቦ ለመስጠት መሞከሩ፤ የቫቲካን ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ካሕናት የፋሺሽቱን የኢትዮጵያ ወረራ ለመርዳት ያላቸውን ጌጣ-ጌጥ ማበርከታቸው፤ ወዘተ. ሊጠቀስ ይቻላል። ሌላም ዝርዝር ማስረጃ ስላለ ያንን ማቅረብ ይቻላል።

ስለዚህ፤ አይሑዶች በናዚ ጀርመኖች ሲጨፈጨፉ፤ ቫቲካን ተቃውሞ ባለማሰማቷ ብቻ በመደጋገም ይቅርታ የጠየቀች መሆኑ ስለሚታወቅ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው ግን ቫቲካንና ሙሶሊኒ እጅና ጓንት ሆነው የሠሩ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ክርስቲያናዊ ተግባር መሆኑ የታወቀ ነው።

የቫቲካን ቄስ የፋሺሽቱን ጦር ሲባርኩ
የቫቲካን ቄስ የፋሺሽቱን ጦር ሲባርኩ

በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው የጦር ወንጀል ተገቢው ካሣ ሳይከፈል መቅረቱ ለማንኛውም በፍትሕ ለሚያምን ሰው ሁሉ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ የታወቀ ነው። ስለዚህ ድርጅታችን፤ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause) ለሚከተሉት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ ነው፤

(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት ተገቢውን ካሣ ለኢትዮጵያ እንድትከፍል፤

(ለ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤

(ሐ) ኢጣልያና ቫቲካን ከኢትዮጵያ የተዘረፉትን ንብረቶች እንዲመልሱ፤

(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን የጦር ወንጀል እንዲመዘግብ፤ እና

(ሠ) በቅርቡ በኢጣልያ፤ አፊሌ በምትሰኝ ከተማ፤ ለፋሺሽቱ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት የተመረቀው መታሰቢያና መናፈሻ እንዲወገድ።

ስለዚህ፤ ቫቲካን፤ በክርስቲያናዊ አስተሳሰቧና ተግባሯ፤ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ የተዘረፈውንም ንብረት በመመለስ ለዘመናት የቆየው ቅሬታ እንዲወገድ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በመማጸን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፍራንሲስ 1ኛ፤ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ የጻፍነውን የአቤቱታ ደብዳቤ ከዚህ ጋር አያይዘን አቅርበንልዎታለን። እጅግ የተከበረ ብፁዕነትዎም ለሐገር የሚገባው ክብር እንዲገኝ እንዲረዱ፤ በተሰዉት ኢትዮጵያውያን ስም፤ በታላቅ አክብሮት እናመለክታለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፤

ኪዳኔ ዓለማየሁ
ዋና ሥራ አስኪያጅ።


ለተከበራችሁ በአውሮፓ አንድነት አባላት ሐገሮች ውስጥ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤

ጉዳዩ፤ ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ፤

በመጀመሪያ፤ በድርጅታችን ስም የማክበር ሰላምታ አቀርባለሁ።

እንደሚታወቀው፤ ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ በብዙ አውሮፕላኖች በተነሰነሰ የመርዝ ጋዝ፤ በቦምብ፤ በጥይት፤ በስቅላት፤ በአካፋ፤ በዶማ፤ ከአውሮፕላን በመወርወር፤ ወዘተ፤ በመጠቀም አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል። ከነዚህ ውስጥ በሶስት ቀኖች ውስጥ፤ በየካቲት 12-14 ቀኖች 1929 ዓ/ም፤ በአዲስ አበባ ብቻ 30 000 ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። ከዚህም በላይ 2000 ቤተ ክርስቲያኖች፤ 525000 ቤቶችና 14 ሚሊዮን ያህል እንስሶች ወድመዋል። በጠጨማሪም፤ እጅግ ብዙ ንብረት በፋሺሽቶቹ ተዘርፎ ኢጣልያ ተወስዷል። ከዚሁ ውስጥ 500 የኢትዮጵያ ሰነዶች በቫቲካን ቤተ መጻሕፍት ይገኛሉ። አንድ “ፀሀይ” የተሰኘች አውሮፕላን በኢጣልያ አየር ኃይል ቤተ መዘክር እየታየች ነው።

ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ከባድ የጦር ወንጀል በቂ ካሣ አልከፈለችም። እስካሁን የፈጸመችው ክፍያ፤ ቆቃ ግድብ የተሠራበት $25 ሚሊዮን ብቻ ነው። ለሌሎች ሐገሮች ከከፈለችውና ከፈጸመችው አሰቃቂ የጦር ወንጀል ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛና ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ግልጽ ነው። በቅርቡ ኢጣልያ ለሊቢያ $5 ቢሊዮን ካሣ ለመክፈል ተስማምታለች። ቀደም ሲልም፤ ለዩጎዝላቪያ $125 ሚሊዮን፤ ለግሪክ ሐገር $105 ሚሊዮን፤ ለሶቭየት ሕብረት $100 ሚሊዮን ለመክፈል ተስማምታ ነበር። ንብረትን በተመለከተ፤ የአክሱምን ሐውልት ከመመለስ ሌላ በኢጣልያኖችም ሆነ በቫቲካን የተከናወነ ጉዳይ የለም። እንዲያውም፤ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፤ በቅርቡ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለሚባለው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ መታሰቢያና መናፈሻ ተሠርቶለት፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ተመርቆለታል።

ስለዚህ፤ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ አምስት መሠረታዊ ዓላማዎችን ይዞ፤ በኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ነው። እነዚህም፤ (ሀ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ በቂ ካሣ እንዲከፍል፤ (ለ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤ (ሐ) የተዘረፈው ንብረት ለኢትዮጵያ እንዲመለስ፤ (መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢጣልያኖች የተፈጸመውን የጦር ወንጀል መዝግቦ እውቅና እንዲሰጥ፤ እና (ሠ) ለግራዚያኒ የተሠራው መታሰቢያ እንዲወገድ፤ ናቸው።

ድርጅታችን ካከናወናቸው ተግባሮች ውስጥ፤ ለኢጣልያ ፕሬዚዳንት፤ ጠቅላይ ሚኒስትርና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ለአውሮፓ ምክር ቤት፤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት፤ ለእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ወዘተ የአቤቱታ ደብዳቤ ጽፏል። በተጨማሪም፤ በድረ-ገጹ  ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ የቀረበ አቤቱታ እየተፈረመ ነው። ከ4200 በላይ የሆኑ የ30 ሐገሮች ነዋሪዎች፤ ኢጣልያኖች ጭምር፤ ፈርመውታል። ተጨማሪ ፊርማም እንዲገኝ ጥረት እየተደረገ ነው። ለዚሁ ተግባር የሚረዳም አንድ ቅጽ ተያይዞ ቀርቧል። እንዲሁም በየዓመቱ፤ የየካቲት 12 ክብረ በዓል በዓለም አቀፍ ዙሪያ እየተዘከረ ነው። በዚህም ዓመት፤ አውሮፓ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጸሎት፤ በስብሰባ እና/ወይም በሰላማዊ ሰልፍ እንደሚታሰብ ፅኑ ተስፋ አለን።

እስካሁን ከተገኙት መልካም ውጤቶች ውስጥ፤ የግራዚያኒ ኃውልት ለጊዜውም ቢሆን መዘጋቱና የከተማውም ከንቲባ እንዲከሰስ መወሰኑ ሲሆን፤ ይህ ውሳኔ ግን በይግባኝ ክርክር ላይ ስለ ሆነ ጉዳዩ ተቋጨ ማለት አይቻልም። ሌላው አስደሳች ክስተት አንዳንድ የኢጣልያ ዜጎች ለኢትዮጵያ ፍትሕ ጉዳይ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ነው። ለምሳሌ፤ እነቫሌሪዮ ቺሪያቺ ስለ ፋሺሽቱ ግፍ በራሳቸው ወጪ አንድ ፊልም በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው እና እነካርሜሎ ክሬሴንቲ ደግሞ ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው በፋሺሽቶች የተገደሉት ሰዎች መቃብር ተገቢ የሆነ እንክብካቤ እንዲያገኝ በማከናወን ላይ ስላሉት ተግባር ነው። ሮም ከተማ የሚገኘው ግብረ-ኃይል ላለፈው የካቲት 12 የሰማእታት ቀን መታሰቢያ ዝግጅት ያሰራጨውን መግለጫ ከዚህ ጋር አያይዘን አቅርበናል።

የዚህ ደብዳቤ ዋና ዓላማም፤ ለሐገራችን የሚያስፈልገው ፍትሕ እንዲገኝ ጠንክረን እንድንታገል ለማሳሰብ ሲሆን፤ በተለይ አውሮፓ የሚኖረው ወገን ከዚህ ጋር የተያያዘውን ለአውሮፓ ምክር ቤት ያቀረብነውን የአቤቱታ ደብዳቤና ያገኝነውን መልስ በመመልከትና ጉዳዩ እንዲቋጭ ክትትል የሚያስፈልገው መሆኑን በመገንዘብ፤ በተቻለ መጠን፤ የምክር ቤቱን አባሎች በማነጋገር ተጨባጭ ውጤት እንዲገኝ ያላሰለሰ ጥረት እንዲደረግ እናሳስባለን።

ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ ጠቅለል ባለ ሁኔታ የተዘጋጀ አንድ የአቤቱታ ደብዳቤም ከዚህ ጋር ተያይዞ ቀርቧል።

ስለዚህ በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የየካቲት 12ን ክብረ በዓል በሚገባ በመዘከርና የአውሮፓ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በትጋት እንዲጥሩ በትሕትና እናሳስባለን።

ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ለውድ ሐገራችን ለኢትዮጵያ ክብርና ፍትሕ ተግተን እንደንሠራ ያበርታን!

ከማክበር ሰላምታ ጋር፤

ኪዳኔ ዓለማየሁ
ዋና ሥራ አስኪያጅ።


ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Tel: (214)703 9022
www.globalallianceforethiopia.org; E-mail: info@globalallianceforethiopia.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule