• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም!

February 13, 2015 08:08 am by Editor Leave a Comment

አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።

ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። ቀደምት ተብላ እንደመጠራቷም ሀገሪቷ ከ100 አመታት በፊት በቱርክ ግዛት ስር ሆና ደማስቆን እና የቤሩትን የወደብ ከተሞች የሚያካልል ሀዲድ ተዘርግቶ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠቃሚም ሆናለች። ከዚያም በመነሳት ነጻነቷን አውጃ ራስዋን ማስተዳደር ስትጀምር የዛሬ 60 አመት በፊት 1956 እ.ኤ.አ ሞደርን ሲኤፍኤስ ፓሴንጀር ትሬን በማለት አዲስ መዋቅር አበጅታ እስከ 2012 ተገልግላበታለች። አሁን ያ ያላት መልካም ገጽታ እና ታሪኳ እንዲሁም ከሁሉ በፊት ባቡር ነጂ መሆናዋ ከመሰባበር አላዳናትም።

የሶርያ ፕሬዘዳንት ባሻር አል አሳድ በአንባገነንነት ምድሪቷን መግዛት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ከ2011 ዓ.ም ወዲህ አሁን ድረስ መልኩን ቀያይሮ እና የተለያየ ስም ይዞ ታልቅ እልቂት ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ220,000 ንጹሀን ዜጎች በላይ ለህልፈተ ሞት ያበቃ ሲሆን 11 ሺህ 420 ህጻናት መገደላቸው እና ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የሆነ ዜጋ ሀገሩን ጥሎ በየጎረቤቱ ጥገኛ እና ስደተኛ ሲሆን የፍትህ የዲሞክራሲ ረሀብ እና ናፍቆት እንጂ መንገድ፣ ፎቅ፣ ባቡርና ሀዲድማ ነበራቸው። ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ እና ስርዓት ምድሪቷን እስካልተቆጣጠራት ድረስ ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው።

Menelik trainስለ ኢትዮጵያ ደግሞ እናንሳ ። በ1895 ዓ.ም አንድ በደረት ላይ የሚንጠለጠል የምድር ባቡር ማሳሰቢያ ባጅ ነበር። በአንዱ ገጽ የአጼ ምኒልክ ምስል በሌላው ደግም 1895 የምድር ባብር ማሳሰቢያ የሚል ተቀርጻበታል። የዛሬ 112 ዓመት በፊት መሆኑ ነው። በአጼ ምኒልክ ውሳኔ የመሰረት ድንጋዩ ተቀምጦ የስዊዝ ተውላጅ በሆኑት ኢንጅነር አልፍሬድ ኢልግ እገዛ መሰረት የሀዲድ መሰመር ግንባታው እኤአ በ1893 ተጀመረ። ከ24 ዓመት በኃላ ስራው ተጠናቅቆ በ1917ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ባቡር ተነዳ። ይህም የዛሬ 98 ዓመት መሆኑ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ ምን ያህል ቀደምት የስልጣኔ ከፍታ እንዳላት ያስረዳል። በአፍሪካ ካሉት ቀደምት የባቡር ተጠቃሚዎች መሀል 1ኛ)ግብጽ በ1856 ዓ.ም 2ኛ) ደቡብ አፍሪካ በ1897 ዓ.ም 3ኛ) ሱዳን በ1898ዓ.ም 4ኛ)ኬንያ በ1901ዓ.ም 5ኛ)ታንጋኒካ በ1905 ዓ.ም 6ኛ) ሴራሊዮን 1909ዓ.ም 7ኛ) ናይጄርያ 1912 ዓ.ም 8ኛ) ኢትዮጵያ በ1917 ዓ.ም በሀገራቸው ላይ ባቡርን ለህዝብ ጥቅም ካዋሉት የመጀመሪያዎቹ ተርታ ትሰለፋለች።

የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰን ባቡር እና ሀዲዱ ብርቅ ሆኖ ባቡር! ባቡር! ባቡር! እየተባለ ጡርንበኞች ሲጮሁ መስማት ምን ያህል ከፍትህ እና ከሰላም ይልቅ ግኡዝ ነገር አእምሮአቸውን እንደጨመደደው ልብ ይሏል። በምድሪቷ ላይ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተከሰከሰው የአባቶች አጥንት ለባቡር ለፎቅ እና ለመንገድ አልነበረም። ይልቁንም ለፍትህ ለሉዐላዊነት ለነጻነት እና ለአንድነት ነበር። አሁንም ያ አጥንት ትውልዱን ይወቅሳል። ባቡርማ ብርቅ አይደለም! ኢትዮጵያም ነበራት። ሶርያም ኢራቅም ነድታለች ዳሩ የህዝብ ረሀብ ነጻነት ሆነ እንጂ። ሶርያ ያላት ህንጻ፣መንገዷ፣ባብሯ እና ሀዲዷ ከመበታተን ከመሰባበር አላዳናትም። የሀገር ሀብት ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ የሆነ እንደሆን ብቻ ሀገር ይለማል። ሀብት እና ንብረታችን ነጻነት እና አንድነታችን ነው። የድል ክንዳችን መያያዛችን እና መቀባበላችን ብቻ ነው።

በወያኔ አለንጋ ደንዛዛ እንዲሆን የተመተተብት ትውልድ አፍዝ አደንግዙን ረግጦ ስለኢትዮጵያው ሊነቃ የሚገባበት ዘመን አሁን ነው። ባቡሩና ሀዲዱ መጥፎ ነው ለማለት አይደለም ስላስፈለገም ነው ከ98 ዓመት በፊት የተገነባው። ድሮስ ወያኔ የራሱን ሆድ ሲያጭቅ ድሆች ከፍርፋሪው ባቡር እና ሀዲድ እንደቡችላ ቢወረውርላቸው ምን ይከፋል። ይህ እኮ የወያኔ ካዝና ውድቅዳቂ እና ፍርፋሪ ነው። ፍርፋሪ ደግሞ ሆድ አይሞላም እንዲያውም ቢያስርብ እንጂ።ይህ ማታለያ  ወያኔ ሀፍረቱ እንዳይታይበት የለበሰው ብጣቂና ቅዱስ የመሰለበት ማስመሰያው  ነው። ተኩላ በበግ ለምድ እንዲከለል ሰይጣንም አውሬነቱን ለመደበቅ ራሱን እንዲከልል ወያኔም ነፍሰ ገዳይነቱን ለመደበቅ አዛኝ መስሎ የማይበስል ቅቤ ያነጉታል። ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት ለሀገሪቷ ፍቅር ያለው መሪ ህዝብን ነጻ ከማድረግ እና የእኩልነት መንፈስ በምድሪቷ ላይ እንዲሰፍን ከመትጋት ይጀምራል። ነጻነት የሌለው ህዝብ ፎቅ ላይ ቢወጣ በባቡር ቢሳፈር ዳሩ እስረኞቹ ተሳፍረው እየሔዱ ነው ቢባል እንጂ ሌላ የማታለያ  መጠርያ ቢሰጠው በመጫኛ መጣል ይሆናል። እንዶሮዋ።

ዳሩ በግኡዛን ቁሳቁስ ብናምር ብንቆጠቆጥ ማን እርሱን ይጠላል። ግን እርሱ ሐብት አይደለም። አንድ ቀን ይከዳል። ምድሪቷ ድንገት ቢያስነጥሳት አሊያም ብትንጠራራ ከበላይዋ በብድር ገንዘብ ያንጋጠጠው ፎቅም በሉት ባቡር አሊያም ሌላ ግኡዝ የፍርስራሽ ቁልል ሁኖ ለመዛቅ ዕዳ ይሆናል። ስለዚህ ስለብልጽግና ስናወራ ስለ ገንዝብ ካወራን ስተናል ማለት ነው። ገንዘብ ኖሮህ ነጻነት ከሌለህ ፎቅ ገንብተህ በየደቂቃው የወያኔ አባት በጣረ ሞት መንፈስ እየመጣ ካስጨነቀህ ከዚህ በላይ ምስኪንነት የለም። ኢትዮጵያ በለጸገች አሊያም ብሩህ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሎ ወያኔ ራሱን በራሱ ቢያንቆለጳጵስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የማባበያ እና የማታለያ ባዶ ዲስኩር ፊቱን ሊመልስ እና ሊነቃ ግድ ነው።

የሀገር ሀብት ፍትህ፣አንድነት፣እኩልነት፣ እና ለአንዲት ሀገር በአንድ ክንድ ለሀገር ሉአላዊነት የቆመ አንድ ህዝብ እንጂ ብሩም ወርቁም ነጻ ባልወጣ ሀገር አያምርም! አያደምቅም! የውሸት ነው። በአዲስ አባባ ላይ ብቻ የታየው ብልጭልጭታ ህጻኑ እንዳያለቅስ የተሰጠው ማታለያ ይመስላል። ኢትዮጵያ አዲስ አባባ ብቻ አይደለችም ። ከቤት እንሰሳት ጋር የውሀ ጥሙን ለመቁረጥ ወደወንዝ የሚርደው ህዝብ፣ ዛፍ ስር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ወጉ እንዳይቀር ሀ ሁ ሂ . . . እያለ ፊደል የሚቆጥረው፣ ለቀዶ ጥገና የ2 አመት ቀጠሮ የሚጠብቁ ታማሚዎች፣ በየክፍለሀገራቱ ከልጅነት እስከ እውቀት በበጋም በክረምትም መጠለያ ሳይኖራቸው በየጥጋጥጉ ቆሼ ተራ እየተመገቡ ያደጉት ሌላም ቢተረክ ጊዜ የማይበቃው ቁርቁዝና ከሁም በላይ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ እውነቱን እንዳይናገር የታፈነ እና የተለጎመ የታሰረ አንደበት የተጠራቀመባት ምድር ናት ኢትዮጵያ የምትባለው። ይህች ናት በወያኔ የተቀረጸችው ኢትዮጵያ። ስለዚህም ነው አሁን የመንቃት ጊዜ እንደሆነ የምንናገረው። ኢትዮጵያውያንን እንደ ህጻን በብልጭልጭ ነገር የማታለል የወያኔ ዘመን ያክትም። ሀብታችን ባቡርና ፎቅ ሳይሆን አንድነት እና እኩልነታችን ነው። በመጀመሪያ ነጻነት!!!

እናቸንፋለን !!!

biniamnor@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ February 15, 2021 11:46 pm
  • የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ February 4, 2021 01:51 pm
  • ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am
  • ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ February 4, 2021 08:48 am
  • በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት የሚያጣራ ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ February 3, 2021 12:06 pm
  • ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ February 3, 2021 10:29 am
  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule