ለሕዝቦች አርነት — ላገርህ አንድነት፣ አርቀህ ማለምህ — አሕዛብን ማንቃትህ፣ “..ጠጣሩ እንዲላላ..” ምክር መለገስህ፣ “በረከት” አድርገህ “ርግማን” ማውረድህ..፣ አቤት! “ለነሱማ” እጅግ ማስፈራትህ! እነ-ኮሎኒያሊስት — ደግሞ እነ-እምፔሪያሊስት...፣ ያገርህ ደመኞች፟- ህሊና የለሾች፣ የሞራል፣ የባህል፣ የታሪክ አልቦዎች፣ አጠገብህ መቆም ከቶ ሲሳናቸው፣ እሚያረጉት ሲያጡ — ወኔ ሲከዳቸው፣ ሃቅን ስለሚሸሹ፟- መበለጥን ስለማይሹ፣ ምኑ ነው እሚደንቅህ? “ዕብድ” ነውስ ቢሉህ! ለኛ እንጂ ጥበብህ — ባለቅኔነትህ፣ የታሪክ፣ የባህል፣..መምህርነትህ፣ የፍትህ፣ ያንድነት.. ዓርማ ቤዛነትህ..፣ “ለነሱማ” አስፈሪ — ልክ-ልኩን ነጋር፣ ቆጥቋጭ የግር-እሳት — ቀሳፊ የጎን ውጋት፣ ሾተላይ ጸሐፊ — ታሪክ አሳላፊ...፤ ጌታቸው አበራ ኅዳር 2007 … [Read more...] about “ለነሱማ…”
Archives for November 2014
ዓለም በቃኝ አለ!
ግጥሙን በPDF ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ዓለም በቃኝ አለ!
ብርቱካን በሊባኖስ ተረፈች፣ አልማዝ በኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ቀረች !
የተረፈችው የእህት ብርቱካን ጉዳይ ... በሃገረ ሊባኖሰ ቤሩት ከ4ኛ ፎቅ ወድቃ የተረፈችው እህት ብርቱካን ጤንነት የተስተካከለና ከድካም ህመሟ ሙሉ በሙሉ እያገገመች መሆኑን መረጃዎች ማምሻውን ደርሰውኛል። የቆንስል ሃላፊዎች አልማዝን ሲያነጋግሯት በሊባኖስ ቆይታ ስራ መስራት እንጅ ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደማትፈልግ እንደገለጸችላቸው አምባሳደር ሐሊማ ሙሃመድ አጫውተውኛል። በቀጣይ ቀናትም ህክምና እየወሰደች ያለችበትን መካስድ ሆስፒታልን ለቃ እንደምትወጣ ፣ በቤሩት የቆንስል መጠለያ ሆና ህክምናና ጉዳይዋን እንደምትከታተል ተረድቻለሁ ! ተስፋ የቆረጡት ኢትዮጵያውያን አስተያየት ... በብርቱካን ጉዳይ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ብዙ ነዋሪዎች የቆንስል ተዋካዮች ላይ እምነት እንደሌላቸው ይገልጻሉ። እንደ አማራጭም የብርቱካንን ጉዳይ በጠበቃ አስይዘው ለመከራከር የሚቻልበትን ንገድ … [Read more...] about ብርቱካን በሊባኖስ ተረፈች፣ አልማዝ በኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ቀረች !
የልጆቻችን ሀገር
አያቶቻችን የልጆቻችን መሬት ነች ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሀገራችንን ከወራሪ ፋሽት ታደጉልን አባቶቻችን በውርስ እርስ በእርስ ሲጣሉ ሳይኖሩበት ሳያኖሩበት ይኸው አሉ ። ልጆች የሚሆነው ሳይገባቸው ውሉ የጠፋባቸውን አባቶቻቸው እያዩ ነው፤ ግራ መጋባታቸውን እየወረሱ ግራ እየተጋቡ ነው ፤ ወይ በሽሽት ላይ ናቸው፤ ነገር ግን እትብታቸው የተቀበረባትን ቀዬ ከማዶ ሆነው እያዪ የጨው አምድ ሆነው ቆመዋል፤ ብቻ ልቦቻቸው ያነባሉ። እንዲህ እያሉ:- የአያቶቻችን ቀዬ - የአባቶቻችን የጦር አውድማ፣ ለኛማ ህልም ብቻነች -ያልተጨበጠች ከተማ፤ ቆመንባት የምትፋጅ- ስንርቃት የምትናፍቅ፣ የሆነች -ነች የቅርብ ሩቅ፤ እንዳንተዋት ማረፊችን፣ እንዳይዛት ማን ፈቅዶልን?፣ አያስነካን - የማይጠግበው አባታችን፣ ብቻ እዛ ማዶ ተገትርን፣ እዚህም ከግለቱ ላይ ተጥደን ፣ ለልጆቻችን አስቀሩልን … [Read more...] about የልጆቻችን ሀገር
“ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ የወረርሽኝ ኢንቨስትመንት!?
በተለያዩ ወቅቶች የሰውን ልጅ ከእንስሳ በማሳነስ የተፈጸሙ ወንጀሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች ይወጣሉ። በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚፈበረኩትና ሆን ተብለው እንዲሰራጩ የሚደረጉት የበሽታ መነሻዎች የክቡር ሰው ልጆችን ህይወት በሚዘገንን ሁኔታ አራግፈውታል። አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ አልፎ ተርፎ ትውልድ … የሰው ልጅ በሽታ ኢንቨስት ተደርጎበት፣ የሕዝብ ብዛት መቀነሻና የባዮሎጂካል ጦር መሣሪያ መመራመሪያ ተደርጓል፣ አሁንም እየተደረገ ነው፤ የበሽታ ማምከኛ መሞከሪያና ማፈላለጊያ ሆኖ ኖሯል። ዛሬም እየኖረ ነው። የሌላውን አገር ሕዝብ ከህይወት በታች፤ የራሳቸውን ግን ድርብ ህይወት እንዳላቸው አድርገው የሚቆጥሩት ምዕራባውያን እንደመልካቸው ለማሳመር የሚሞክሩት ታሪካቸው ለማመን የሚያስቸግር እና ለመቀበል የሚከብድ ፍትሕ ያልተሰጠባቸው “ወንጀሎች” አካሂደዋል፤ አሁንም በረቀቀ መንገድ እያካሄዱ … [Read more...] about “ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ የወረርሽኝ ኢንቨስትመንት!?
THE BRUSSELS ETHIOPIAN HISTORICAL MARCH!
The Woyyane (The TPLF) is a terrorist organisation that is holding Ethiopia at ransom. Since the these criminals came to power, nothing changed in their wild behaviour. They were terrorists yesterday, they are terrorists today and unless they are stopped now, they wouldn’t change their behaviour in the future. The worsening brutality of the ethno-apartheid Woyyane (i.e. ethnic based black on black apartheid) regime has left Ethiopians with no option but to come together and resist tyranny of the … [Read more...] about THE BRUSSELS ETHIOPIAN HISTORICAL MARCH!
እርም (ሐራም)
በባህላችን የሰው ስም በትርጉም አልባነት እንደማይለጠፍ፤ ከሰውነታችን ጋራ የሚገናኙ ነገሮችም ስማቸው ከመነሻቸው ጋራ የተያያዘ ነው። “እንጀራ” ከምድራዊ ህይወታችን ጋራ ከተገናኙት መሠረታውያን ነገሮች አንዱ ነው። እንጀራ እስካሁን ድረስ የተነሳበትን የታሪክ ትዝታ ተሸክሞ ብዙ ዘመን ተጉዟል። እንጀራ ከወላጅ እናቱ ከጤፍ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ሩቅና ጥልቅ ትስስር እንዳለው ሁሉ፤ ከመብላት ስሜትና ሱስ ጋራ ተዋህዶ በሰውነታችን ስለጋባ፤ ዝንት ዓለም የኖረ ይህን ጥብቅ ግንኙነት የሚያስለቅቅ፤ ጥብቅ ምክንያት መቅረብ ያለበት ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ እየተጫነ የሚመጣውን እንጀራ አትብሉ ወደሚለው ሀሳብ ምን እንደወሰደን በግልጽ ለማቅረብና፤ እንዴትስ እናቁም ወደ ሚለው ውይይት ለመግባት፤ ከጉባዔ ትምህርት ቤት መምህራን የሰማሁትን ለውይይታችን መንደርደሪያ … [Read more...] about እርም (ሐራም)
“እኛ”!! እናንተ እነማን ናችሁ? ደረጃ ምደባ!!
ደረጃ ምደባ ለሸቀጥ ወይም ለአንድ ምርት የሚወጣ ማነጻጸሪያ፣ መለያ፣ መተመኛ፣ የጥራት መጠን መለኪያ … ነው። የደረጃ ምደባ ሲከናወን እንደ አቅሚቲም ቢሆን አስፈላጊ የሚባሉ የመመርመሪያ መሳሪያዎች፣ ቤተ መመርመሪያ፣ መርማሪ ባለሙያና ተመርማሪው ሸቀጥ አስፈላጊ ናቸው። የወጉ አሰራር ካለ ማለት ነው። “እኛ” ሲባል ባጭሩ ከአንድ በላይ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር አንድ ብቻውን “እኛ” ሊባልም ሆነ እኛ ብሎ ራሱን ሊጠራ አይቻለውም። ስለዚህ “እኛ” የወል፣ የስብስብ ወይም የጋራነት መለያ ከሆነ፣ አንድ ሆኖ “እኛ” የሚል ተቀባይነት የለውም። አሁንም ባጭሩ የከሸፈ አስተሳሰብ ነው። የከሸፈ ብቻ ሳይሆን የሚያከሽፍም ነው። በነጠላነት ውስጥ ያለው “እኛ” ነት በርካቶችን አክሽፏል፤ አሸማቋል። አሁን ባለው አያያዝ ጉዳቱ ወደ “ውድቀት ህዳሴ” እያንደረደረ ነው። ግን ፍሬን ሊያዝበትና … [Read more...] about “እኛ”!! እናንተ እነማን ናችሁ? ደረጃ ምደባ!!
የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ
ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ነጭ … [Read more...] about የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ
“ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር "ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ" በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡ "ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ" እንዳዘጋጀ ያሳወቀው ትብብሩ የትግሉ ዓላማ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጾአል፡፡ "ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል" ያለው መግለጫው በመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ፕሮግራሙ 6 ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈጸም ዝርዝር እቅዶችን አውጥቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን … [Read more...] about “ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ