አያቶቻችን የልጆቻችን መሬት ነች ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሀገራችንን ከወራሪ ፋሽት ታደጉልን አባቶቻችን በውርስ እርስ በእርስ ሲጣሉ ሳይኖሩበት ሳያኖሩበት ይኸው አሉ ። ልጆች የሚሆነው ሳይገባቸው ውሉ የጠፋባቸውን አባቶቻቸው እያዩ ነው፤ ግራ መጋባታቸውን እየወረሱ ግራ እየተጋቡ ነው ፤ ወይ በሽሽት ላይ ናቸው፤ ነገር ግን እትብታቸው የተቀበረባትን ቀዬ ከማዶ ሆነው እያዪ የጨው አምድ ሆነው ቆመዋል፤ ብቻ ልቦቻቸው ያነባሉ። እንዲህ እያሉ:-
የአያቶቻችን ቀዬ –
የአባቶቻችን የጦር አውድማ፣
ለኛማ ህልም ብቻነች -ያልተጨበጠች ከተማ፤
ቆመንባት የምትፋጅ- ስንርቃት የምትናፍቅ፣
የሆነች -ነች የቅርብ ሩቅ፤
እንዳንተዋት ማረፊችን፣
እንዳይዛት ማን ፈቅዶልን?፣
አያስነካን – የማይጠግበው አባታችን፣
ብቻ እዛ ማዶ ተገትርን፣
እዚህም ከግለቱ ላይ ተጥደን ፣
ለልጆቻችን አስቀሩልን እንላላን።
ቲታ አብ ራሴ
Leave a Reply