ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤ የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤ ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣ ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣ ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣ ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ...፣ “ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣ አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ...”፣ እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ እስኪያጥር፣ ሰምቼህ ሳበቃ፣ የግርምት ጥያቄ እስኪማ ልሰንዝር፤ በልበ-ሙሉነት “ጠግብን በላን” ያልከው፣ ሕዝቡን ቆጥረህ ይሆን? ወይስ የቤትህን ያንተኑ ግሳት ነው?! ስርህ ተግተርትሮ፣ ላብ እያሰመጠህ፣ ያቀረብከው ‘ሪፖርት‘ እንዲያ ተውረግርገህ፣ የራስህን በጀት፣ የጓዳህን ወሬ፣ ወይስ የምስኪኗን … [Read more...] about ጎተራው ወዴት ነው?¡
Archives for November 2014
መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (circular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡ በመሆኑም አሁን ላይ ዜጎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ "በተለየ ሁኔታ የሚሸጥላቸው ሰዎች ከጉዞ ወኪላቸውና ከበላይ አካል ይዘውት በሚመጡት ደብዳቤ መሰረት ብቻ ነው ምንዛሬ ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ግን እንደበፊቱ ማንም የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይችልም" ሲል አንድ የንግድ ባንክ ሰራተኛ … [Read more...] about መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል
በአንድነት ተሰባስበን መታገሉ ግዴታችን ነው
ውድ ኢትዮጵያዊ ድረገጽ፤ ከታች ያለውን ደብዳቤ ለግለሰቦች መላክ ፈለግሁና፤ ለማን ልላክ ብዬ ካወጣሁ ካወረድኩ በኋላ፤ የተወሰኑ ስሞችን ሰበሰብኩ። እኒህን ለይቶ ማውጣቱና፤ እኒህ ብቻ ናቸው ብሎ መለየቱ አሳሰበኝ። ማን ማንን ይወክላል? ሌላውስ ላለመወከሉ ምን መከላከያ አለኝ? እኒህን ለመሰሉ ጥያቄዎች፤ አመርቂ አልስ መሥጠት አልቻልኩም። ለምን በጠቅላላው በትግሉ ላይ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ ይኼ ኃላፊነት አለብን በማለት አልልክላቸውም? የሚለው ውሳኔ አስታራቂ ሆነልኝ። በየቦታው ኢትዮጵያዊያን እየታገሉ ነው። ይኼን ትግል ወደ አንድ ማዕከል ማምጣቱ ነው የዕለቱ ጥያቄ። በሃይማኖት ተከታዮች በኩል የሚደርሰው በደል፣ በትውልድ ሐረጋቸው የተነሳ የሚደርስባቸው በደል፣ በተሰማሩበት የንግድ መስክ የተነሳ የሚደርስባቸው በደል፣ በመኖሪያ አካባቢያቸው፣ ለንግድ ተብሎ ከቦታቸው በሚፈናቀሉት … [Read more...] about በአንድነት ተሰባስበን መታገሉ ግዴታችን ነው
“እግዚአብሔር ያሳየዎ: ክርስቶስ ያመልክተዎ!”
እግዚአብሔር በሚያሳየው ክርስቶስ በሚያመለክተው መስመር የማይሰለፍ፤ በቡድንና በጥቅም በተራቆተ ስሜት ተሳስሮና ተለባብሶ የሚኖር ህብረተሰብ፤ ከራሱ በሚፈልቅ ስሜት ወይም ከውጭ በሚመጣ ግፊት ከመጠፋፋት ቢያመልጥም፣ ከመለያየት ማምለጥ ፈጽሞ አይችልም። ክርስቶስም “እርስ በርስዋ የምትለያይ አገር ሁሉ ትጠፋለች። እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት አይቆምም” (ማቴ 12።5)በማለት አስጠንቅቋል። ፍረዱብን እያሉ ተቆራኝተው ሰሞኑን ወደኛ በቀረቡት በማህበረ ቅዱሳንና በአባማትያስ መካከል የተከሰተው ይህ ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “እግዚአብሔር ያሳየዎ: ክርስቶስ ያመልክተዎ!”
የምዕራባዊያን የሕክምና ማዕከላት የሴት ልጅ ግርዛትን ተቀበሉ በስፋትም እየፈጸሙ ነው!
ምዕራባዊያኑ በኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው? በእርግጥም ጽሑፉን ካነበባቹህ በኋላ እንደኔ ሁሉ እናንተም “ምዕራባዊያኑ በእኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው?” እንደምትሉ አልጠራጠርም፡፡ ይሄንን እንድል ያስገደደኝ ጉዳይ አንድ ህክምና ላይ አተኩሮ ጽሑፎችን የሚያትም መካነድር ላይ አንድ ይዝ (ሊንክ) ተጠቁሞ አገኘሁና ከፈትኩት ከዚያ እላቹህ ፈጽሞ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት እጅግ ደግሞ የገረመኝን ነገር አገኘሁ፡፡ ምዕራባዊያኑን ስናውቃቸው ብዙ ነገሮችን እያወሩ የሴት ልጅ ግርዛትን ከእኛና እኛን ከመሰሉ ሀገራት ሁሉ “ጎጂ ባሕል” በማሰኘት ለማስቀረት ምንያህል እንደደከሙና እያስቀሩትም እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንን አየሁት ያልኳቹህን ይዝ (ሊንክ) ካየሁት በኋላ ግን እነዚህ ሰዎች ወይ ስለኛ ግርዛት ምንም በማያውቁት ነገር ላይ ነው የሚዘባርቁት ወይ ደግሞ ከሚሉን ነገር … [Read more...] about የምዕራባዊያን የሕክምና ማዕከላት የሴት ልጅ ግርዛትን ተቀበሉ በስፋትም እየፈጸሙ ነው!