ምዕራባዊያኑ በኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው? በእርግጥም ጽሑፉን ካነበባቹህ በኋላ እንደኔ ሁሉ እናንተም “ምዕራባዊያኑ በእኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው?” እንደምትሉ አልጠራጠርም፡፡ ይሄንን እንድል ያስገደደኝ ጉዳይ አንድ ህክምና ላይ አተኩሮ ጽሑፎችን የሚያትም መካነድር ላይ አንድ ይዝ (ሊንክ) ተጠቁሞ አገኘሁና ከፈትኩት ከዚያ እላቹህ ፈጽሞ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት እጅግ ደግሞ የገረመኝን ነገር አገኘሁ፡፡ ምዕራባዊያኑን ስናውቃቸው ብዙ ነገሮችን እያወሩ የሴት ልጅ ግርዛትን ከእኛና እኛን ከመሰሉ ሀገራት ሁሉ “ጎጂ ባሕል” በማሰኘት ለማስቀረት ምንያህል እንደደከሙና እያስቀሩትም እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንን አየሁት ያልኳቹህን ይዝ (ሊንክ) ካየሁት በኋላ ግን እነዚህ ሰዎች ወይ ስለኛ ግርዛት ምንም በማያውቁት ነገር ላይ ነው የሚዘባርቁት ወይ ደግሞ ከሚሉን ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የተደበቀ ዓላማ አላቸው ለማለት ተገደድኩ፡፡ ያየኋቸው ተመሳሳይ ይዞች (ሊንኮች) ሌቢያፕላስቲ (Labiaplasty) ስለ ሚባል የህክምና ዓይነት ህክምናውን ለማድረግ ከሚያስገድዱ ምክንያቶች እስከ የህክምናው አፈጻጸም ከዚያም ስለ አመርቂ ውጤቱ በሚገባ ይገልጻሉ ያሳያሉ፡፡
ይህ የህክምና ዓይነት የሴት ልጅን የመራቢያ አካል የሚመለከት “ህክምና” ነው፡፡ ህክምና ስላቹህ ከህመም ጋር እንዳታያይዙት ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ሌቢያፕላስቲ የሚባለውን ቃል ወደኛ ቋንቋ ቃል በቃል እንተርጉመው ካልን ትርጉሙ የሴት ልጅ ግርዛት ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ ያልኩት የሴት ልጅ ግርዛት (Woman’s Circumcision) ነው እንጅ የብልት ትልተላ (Genital Mutilation) አይደለም::
እናም ሌቢያፕላስቲ (የሴት ልጅ ግርዛት) በሠለጠነው ዓለም በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ወደድ የሚል ህክምና ሆኗል ብላቹህ አይደንቃቹህም? ይህንን ህክምና የሠለጠነው ዓለም ሴቶች የሚያደርጉት የሴትን ልጅ ብልት ታናሹን ከንፈር (Labia minora) ካለው መጠን ቀንሶ አነስተኛና በታላቁ የሴት ልጅ የብልት ከንፈር (Labia majora) ውስጥ የሚሠወር የሚቀር ማድረግ ነው፡፡ ይሄንን እንዲያደርጉ የሚገደዱት ሴቶች ደግሞ ታናሹ ከንፈር ከታላቁ ከንፈር የበለጠ የብልት ዓይነት ያላቸው ከአጠቃላይ ሴቶች 50% ያህሉን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ናቸው፡፡ በጣም ያስገረመኝና እኔ ብቻ ሳልሆን ሴቶችን ጨምሮ ሌሎቻቹህም ቢሆን የማትጠብቁት ነገር ቢኖር “ሴቶች እንደመልካቸው ሁሉ ብልቶቻቸውም ከመጠንና ቅርጽ በተጨማሪ በዋነኛነት ገጽታውም የአንደኛዋ ከሌላኛዋ የማይመሳሰል መሆኑ ነው፡፡ የሠለጠነው ዓለም ሴቶች ላቢያፕላስቲ (የሴት ልጅ ግርዛትን) የሚያደርጉበት አስገዳጅ ምክንያት ወይም ዓላማ ማለትም ይሄንን በማድረግ እንዲወገዱላቸው የሚፈልጓቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ደግሞ፡-
1. የግል ንጽሕናን ችግር (Problem of personal Hygiene)
2. ከሰውነት ጋር ጥብቅ የሚል (ቦዲ) ሱሪና የመሳሰሉት ልብሶች በሚደረግበት ወቅት የሚፈጠርን መላላጥ (Infection)
3. በወሲብ ጊዜ ያለመመቸትን ችግር (Discomfort during Sex)
4. ለዐይን የማይስብ የብልትን ቅርጽና ገጽታ ችግር (Discomfort Looking)
5. ብስክሌት በመጋለብ ወይም በእግር በሚጓዙበት ጊዜ የሚፈጥረውን ያለመመቸት ችግር (Discomfort Cycling or Walking) ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
አኃዙ እንደሚያመለክተው ሐምሳ ከመቶ ሴቶች የብልቶቻቸው ተፈጥሮ እንዲህ ዓይነት ከመሆኑ አንጻር ይሄንን ህክምና ሊያደርጉ የሚፈልጉት ሴቶች በርካቶች ቢሆኑም ህክምናው ቀላል የሚባል ሆኖ እያለ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማይታወቅ ሁኔታ የህክምናው ዋጋ ወደድ በማለቱ ምክንያት ገንዘብ ያላቸው ሴቶች ህክምና ብቻ ሊሆን ችሏል፡፡ ህክምናውን ካደረጉት ሴቶች ውስጥ እንደሚናገሩት ተቆርጦ እንዲወገድ የተደረገው የብልት አካል ማለትም ታናሹ ከንፈር (Labia minora) ተቆርጦ ከተወገደላቸው በኋላ ውጤቱ እጅግ ከጠበቁት በላይ ከመሆኑ የተነሣ ያ ተቆርጦ የተወገደው አካል ምን ያህል ምቾታቸውን ነፍጓቸው እንደነበር ያወቁት ህክምናውን ካደረጉ በኋላ ያገኙትንና የተሰማቸውን ምቾት፣ እፎይታ፣ ነጻ የመሆን ስሜት፣ በማንም ፊት ያለመሸማቀቅና በራስ የመተማመን ስሜት ካዩ በኋላ እንደሆነ ሲናገሩ ህክምናው ሥነ-ልቡናቸውን እንዳስተካከለላቸው ጭምር በመግለጽ ምን ያህል እንደጠቀማቸው በመደነቅ ይናገራሉ፡፡
በጣም የሚገርማቹህ ነገር እነሱ ገና አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደረሱበትን ይሄንን እውቀትና ሥልጣኔ እኛ ከሽዎች ዓመታት በፊት ደርሰንበት በባሕል ደረጃ ቀርጸን ስንፈጽመው የኖርነው መሆኑ ነው፡፡ ለካ የሴት ልጅ ግርዛትን ከእኛ ለማስጣል ያንን ያህል ይደክሙ የነበሩት እኛ ስንጥልላቸው ለማንሣት ኖሯል?
እነሱ ግን አሁንም ድረስ በህክምና ማዕከላቶቻቸው ሌቢያፕላስቲ በሚል ስም እየሰጡት ያለውን የህክምና አገልግሎት እኛን ጎጂ ባሕል ነው እያሉ እንደ እኛ ሁሉ ግርዛትን ባሕላቸው ያደረጉ ሀገራትን መንግሥታት እየተጫኑ ግርዛትን በሕገ ወጥነትና በወንጀል ድርጊቶች በመፈረጅ እያስቀሩት ይገኛሉ፡፡ ከአንድ ወር በፊትም ለንደን ላይ አንድ ዓለማቀፋዊ ስብሰባ ተደርጎ ጠንካራ አቋም ተይዞ እንዲወጣ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ይሄንን ሁሉ እያደረጉ ግን ግርዛትን በወንጀል እንደመፈረጃቸው ሁሉ በይፋ በየህክምና ማዕከሎቻቸው እየተፈጸሙ ያሉ የሴት ልጅ ግርዛቶችን ወንጀል አድርገው እንዲቀጡበት አላደረጉም ለምን?
ወደ እኛ ስንመጣ ግን እንደምታውቁት የሴት ልጅ ግርዛት በሀገራችን እየቀረ ነው፡፡ ይሄ የበሰለ የሠለጠነ ባሕላችን በመቅረቱና እየቀረ በመሆኑ ምን ያህል እንደተጎዳንና እየተጎዳን እንደሆነ ገና አልተስተዋለም፡፡ ይሄንን የሚያጠና ዐይናማ አስተዋይ አካል ባለመኖሩና ልብ ባለማለታችን በዚህ ምክንያት የምንከፍለው ዋጋ ገና የሚቀጥል መሆኑ ግድ ሆኗል፡፡
ምዕራባዊያኑ እኛን “ተዉ ጎጂ ባሕል ነው” ሲሉ የሚነግሩን ነገር የተገራዧን የወሲብ ፍላጎት ይጎዳል፣ በወሊድ ጊዜም ለችግር ይዳርጋታል በማለት ነበር፡፡ ይሄ የሚሉት ችግር የሚደርስ ከሆነ ታዲያ ምነዋ እነሱ ጭራሽም በህክምና ማዕከላቶቻቸው ግርዛቱን አጧጡፈው መፈጸማቸው? እነዚህ ውንጀላዎች ሐሰት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከዚህ ቀደም በዚህ ዙሪያ ባደረኩት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ለእናንተ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ይሄው ከእነሱ ከራሳቸው ማረጋገጫቹህን አገኛቹህ፡፡ ነጮቹ እኛ ግርዛትን የምናደርግበትን ምክንያቶች ጠንቅቀው ስለተረዱና በደረሱበት የህክምና ሳይንስ (መጣቅ) ስላረጋገጡ አፍ አውጥተው ማረጋገጫውን ከሚገባው አድናቆት ጋር አይስጡ ወይም አይናገሩ እንጅ ከላይ በተጠቀሱት ከፊል ምክንያቶች ሽፋን እየተገረዙ እኛ የሴት ልጅ ግርዛትን አድርገን ሴቶቻችን የሚያገኟቸውን ጥቅሞች እያገኙና ከሥጋቶቹና ችግሮቹ ሁሉ እራሳቸውን እየታደጉ እየተከላከሉ ይገኛሉ፡፡ ነገሩ አይገርማቹህም? ምናለ አምሳሉ ትሉኛላቹህ ትንሽ ቆይተው ደግሞ ሳያፍሩ ይህ ግኝት የፕሮፌሰር እከሌ ነው ይሉናል፡፡ አሁን ይሄ ብልጠት ነው ወይስ ምን ይባላል?
ታስታውሱ እንደሆነ በጥናቴ ላይ “የወንድ ልጅ ግርዛት ከኢትዮጵያ ወጥቶ የመላው ዓለም ባሕል እንደሆነ ሁሉ ጥቂቶቹ ከእኛ ወስደው ባሕላቸው እንዳደረጉት ሁሉ ወደፊት ሲገባው መላው ዓለም የሴት ልጅ ግርዛትንም እንዲሁ ከእኛ ወስዶ ባሕሉ ያደርገዋል” ብየ ተንብየ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን እንዲህ ጭራሽ እኛን ለማስጣል በኃይል እየተጫኑን ባሉበት ወቅት በቅርብ ጊዜ ይሆናል ብየ ጨርሶ አልገመትኩም ነበር፡፡
አሁን መስማት የምፈልገው የምእራባዊያኑ የገደል ማሚቶ በመሆን ያሏቸውን ከማስተጋባት ውጭ አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን የራሳቸውን ጥናትና ምርምር ሳያደርጉ የእነሱን ቃል እንደ አምላክ ቃል አድርገው ያለ ማቅማማት በመቀበል የሚያስተጋቡትን የእነዚያን ተቀጽላ ሐኪሞቻችንን ምላሽ ነው፡፡ እነሱን አሁንስ ምን ትሉ ይሆን? ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ለግርዛት ቀጠና ሀገራት መንግሥታት የሚኖረኝ መልእክትና ማሳሰቢያ ደግሞ ይህ እየሆነ ያለው ጉዳይ በምዕራባዊያን ጫና ከምታደርጉት ከተሳሳተ ድርጊታቹህ ለመንቃት መልካም አጋጣሚና የማንቂያ ደወል ነውና ንቁ! ልብ አድርጉ ልብ በሉ፡፡
ስለ ሌቢያፕላስቲ (የሴት ልጅ ግርዛት) በመካነድር ከተለቀቁ በርካታ በትእይንተ-ኩነት (በቪዲዮ) የተደገፉ መረጃዎች አሉና የእነሱን ይዞች (ሊንኮች) እንድትመለከቱ ልጋብዛቹህና ልቋጭ፡፡ በቅድሚያ እንድታዩት የምፈልገው ይዝ (ሊንክ) ግን ከሴት ልጅ ግርዛትነትም (Woman’s Circumcision) ታናሹን ከንፈር (Labia minora) ከመቁረጥ አልፎ ታላቁን ከንፈር ማለትም ይሄ “ጉንጭ የሚመስለውን የብልትን አካል” (Labia majora) ጨምሮ በመቁረጥ ወደ ብልት ትልተላ (Genital Mutilation) ደረጃ የሄደውን ድርጊታቸውን ነው፡፡ እሱም ይሄ ነው፡-
ከዚህ ውጭ ባሉት ትዕይንተ ኩነቶች (ቪዲዮዎች) ሁሉ የሚታዩት ግን እኛ የሴት ልጅ ግርዛት ብለን የምንፈጽመው ድርጊት ነው ተመልከቱት፡፡ ማስጠንቀቂያ እነኝህን ትዕይንተ ኩነቶች (ቪዲዮዎች) መመልከት የሚችሉት ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ብቻ ናቸው ይላል እኔ ግን ከ18 ዓመት በላይ ብየ እንዳስተካክለው ፍቀዱልኝና ተመልከቱት፡፡ እድሜያቹህን ለማረጋገጥ የኢሜይል አድራሻቹህን ይጠይቃቹሀል እሱን በማድረግ ተባበሩት፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
(ከአዘጋጆቹ፡ ሠዓሊ አምሳሉ ለዚህ ጸሁፋቸው ዋቢ በማድረግ የበርካታ የሕክምና ባለሙያዎችን የቪዲዮ ማስረጃዎች ጠቅሰዋል፡፡ እነዚያን ሁሉ እዚህ ላይ ማተሙ ለአሠራር የሚያመች ሆኖ ስላላገኘነው እና በሌሎች ግብረገባዊ ምክንያቶች ትተነዋል፡፡ ሆኖም አንባቢያን youtube ላይ Labiaplasty በማለት ፍለጋ ቢያካሂዱ በርካታዎቹን ማግኘት ይችላሉ፡፡)
Jemal M. says
Tnx Amsal ! Yegnan tiru wesdew bado askerun .
aradaw says
Dear ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው:
በጣም የሚገርማቹህ ነገር እነሱ ገና አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደረሱበትን ይሄንን እውቀትና ሥልጣኔ እኛ ከሽዎች ዓመታት በፊት ደርሰንበት በባሕል ደረጃ ቀርጸን ስንፈጽመው የኖርነው መሆኑ ነው፡፡ ለካ የሴት ልጅ ግርዛትን ከእኛ ለማስጣል ያንን ያህል ይደክሙ የነበሩት እኛ ስንጥልላቸው ለማንሣት ኖሯል?
Is this a joke?
Do you really mean this?
Do we do circumcision or mutilation because of the same reasons? What we see know is rich women’s reconstructive surgery as they do to their lips, eye lid, nose. They do these including Labiaplasty for some reason they are not happy with the look of their body part . Dear Amsalu, for your information the ASPS ( American Society of Plastic Surgery) itself does not endorse these surgeries and cautions that surgery may need further scientific study to determine efficacy and success. Secondly the procedure is done by the initiation of the person who feel needs the procedure, these are mostly very rich women as the procedure not covered by insurance and very expensive.
Comparing this procedure with the brutal procedure of circumcision or trying to justify the cruel act of circumcision in Ethiopia with Labiaplasty is very irresponsible above all trying to justify a backward idea with Labiaplasty is supporting or propagating brutality against women.
I am really surprised ሠዓሊ አምሳሉ put the time and effort to write this long nonsense piece. I think the time and effort can e used for something that is useful for the web page and the readers of this web.
aradaw.