የታዋቂው ባለቅኔና የሥነ ጽሑፍ ሰው የጋሼ ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) አስከሬን ኖቬምበር 30፤2014 በእስቶክሆልም ከተማ በብዙ መቶዎች በሚቆጠሩ ያገር ልጆች፣ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ጓደኞቹ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት በአቡነ ኤልያስ የሚመራ ፍትሃት የተደረለት ሲሆን፣ ቤተሰቦቹና ተጋባዥ እንግዶች የመሸኛ ንግግርና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥሞችን (Lament) ለለቀስተኞች አቅርበዋል፡፡ በዕለቱ የተገኙት ደራሲ አበራ ለማ ከተጋባዥ ተናጋሪዎችና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥም አቅራቢዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን “የባለቅኔው ዝምታ” በተሰኝ ግጥም ስንብታቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህንኑ በማስመልከት አበራ ለማ የላኩልንን ግጥም እንዲሁም ፎቶ አቅርበናል፡፡ የባለቅኔው ዝምታ መጣልሽ እምዬ፣ ገሞራው ልጅሽ ቅኔ ባኩፋዳ፣ ስንቁን ይዞልሽ፤ መጣልሽ … [Read more...] about የባለቅኔው ዝምታ
Archives for November 2014
ጸረ- ወያኔው ትግል ይፋፋም!
የወያኔን ጸረ-ዴሞከረሲያዊንት ለማስረገጥ ሐቁ ሞልቶ መፍስስ ከጀመረ ብዙ ዓመታትን አስቆጠረ። ወያኔ ለህግ የበላይነት ይገዛል ብሎ ማስብ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመመኘት ይሆናል ብንል ማጋነን አይሆነብንም። ወያኔ ክፍጥረቱ ጀምሮ እሰክዛሬ ድረስ ከሐቅ ተጣልቶ፣ ሀሰተን አንግሶ፣ ጥላቻን ተላብሶ በማደናገርና በማወናበድ ፓሊሲ የተመራ በመሆኑ አሁንም እድሜውን ጨርሶ በማብቂያው አዝማሚያ ያላደገበትን፣ ያልለመደውን ፍትህና ዴሞከርሲያዊ ባህሪ እንዲያሳይ ልንጥብቅ ከቶ አይግባም። (ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጸረ- ወያኔው ትግል ይፋፋም!
“ለመተማመን እንነጋገር!”
በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአገራችን ውስጥ ስላለው ችግር መፍትሔ ለማምጣት ይጠቅማል በሚል በጠራው ውይይት ላይ ኢትዮጵያውያን ከአውሮጳ፣ ከአሜሪካና ከካናዳ ተጠራርተው በመምጣት በዓይነቱ ለየት ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡ “ሰላም፣ ፍትሕ፣ ዕርቅና መከባበር የሰፈነበት ማኅበረሰብ ለመመሥረት” አንዳችን ስለሌላችን በመናገር ሳይሆን እርስበርስ ስለችግራችን መወያየት አለብን በሚል መሪ ሃሳብ ኢትዮጵያውያኑ ግልጽና በቅንነት ላይ የተመሰረተ ውይይት አካሂደዋል፡፡ “ከዘረኝነት ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” የመስጠት አስፈላጊነትም በስፋት ውይይት የተደረገበት ጉዳይ ነበር፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ኤምባሲ የስብሰባው አካል እንዲሆን ለአምባሳደር ግርማ ብሩ የንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ የላኩ ቢሆንም ከኤምባሲው በኩል የተሰጠ ምላሽም ሆነ … [Read more...] about “ለመተማመን እንነጋገር!”
“Breaking the Cycle of Dysfunction in Ethiopians Institutions forum”
November 18, 2014. Washington, DC--. At the recent Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) Forum in Washington D.C. on November 15, it was quite evident that Ethiopia does not lack for gifted people who possess the essential capabilities, virtue, and experience needed to build a New Ethiopia. It was inspiring to hear from a wide array of speakers who portrayed the qualities of courage, strength, faith, wisdom, integrity, and an attitude of respect towards others, even when some … [Read more...] about “Breaking the Cycle of Dysfunction in Ethiopians Institutions forum”
“የደም ከፈን!”
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ለታዋቂው የስዊድን ጨርቃጨርቅ ዓለምአቀፍ ቸርቻሪ H&M Hennes & Mauritz AB (H&M) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራአስኪያጅ ካርል ዮሐን ፔርሶን ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር ስለሚያደርገው የንግድ ውል ኩባንያቸው ሊገጥመው ስለሚችል አደጋ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡ ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሥነስርዓት ሚ/ር ፔርሶን የ2014 በንግድ የማያዳላ ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልክተው በላኩት ደብዳቤ ላይ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ሊጀምር ያለው የንግድ ስምምነት ፍጹም አድሏዊነት የተሞላበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እንደተመለከተው H&M ኩባንያ ከኢህአዴግ ጋር ለሚያደርገው ውል ለሸሪክነት የተመረጡት አምስት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ሶስቱ የህወሃት የግል ሃብት የሆነው የኤፈርት አባል … [Read more...] about “የደም ከፈን!”
ጎሞራው ሄደ አሉ ሳይሰናበተን
በገንዘብ ሲኮራ - ሰው በወርቅ ሲያጌጥ፤ ጎሞራው በቅኔ - ነበር ይንቆጠቆጥ፤ ኩታው ነበር ቃላት - ካባው ነበር ስንኝ፤ ጎሞራው ሲቋጥር - ለወገኑ ሲቀኝ:: ሄደ አሉ ጎሞራው - ሁሉን ነገር ንቆ፤ ሊቀኝ ቅኔ ሊዘርፍ - ከዚች ዓለም ርቆ:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጎሞራው ሄደ አሉ ሳይሰናበተን
Moresh open letter to the United Nations Security Council
This letter is written to file a formal complaint regarding the report ‘SEMG S/2014/727’ dated 13 October 2014. I would like to bring to your attention specifically to the content and implications of the text stated on page 31, paragraph 78, which states “Ginbot Sebat is a banned opposition group formed in 2005 by Amhara political elites committed to regime change in Ethiopia through armed struggle.” We are utterly baffled by the motive behind this false information and data contained in the … [Read more...] about Moresh open letter to the United Nations Security Council
አባት አቶ ላላንጎ እና እናቷ ወ/ሮ ትርፌ ስለ ሃና ተናገሩ!
እህት ሃና በሰው አራዊቶች ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተደፍራ ወድቃ ያገኟት አባት ልጃቸው ህክምና ታገኝ ዘንድ ከሆስፒታል ሆስፒታል ስለተንከራተቱበት፣ የህክምና እርዳታ ስለተነፈጉበት አሳዛኝ ሂደት ሀገር ቤት በሚተላለፈው ኤፍ ኤም ራዲዮ ተናግረዋል። አባት ሲናገሩ ለሃና ህክምና ማድረግ ያልቻሉት የመንግስት ህክምና ተቋማት ሳያንስ ፖሊስ ጉዳዩን እንዲመረምር በልመና ካሳኩ በኋላ ህክምና ማግኘት ባለመቻላቸው የሚረዳቸው አጥተው ተጎጅ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ወስደው ስላሳደሩበት እንግልት ሰምተናል፣ ይህም ያማል፡፡ እንደ አባት አቶ ላላንጎ ገለጻ ልጃቸው እህት ሃና ከጋንዲ ጥቁር አንበሳ ከጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ ግልጋሎት ተነፍገው ተንከራተዋል። ወደ መጨረሻም በዘውዲቱ ሆስፒታል አልጋ ተሰጥቷን መታከም መጀመሯንና በህክምና እያለች የምስክርነት ቃሏን በደል አድራሽ ያለቻቸውን ሶስቱ በፖሊስ … [Read more...] about አባት አቶ ላላንጎ እና እናቷ ወ/ሮ ትርፌ ስለ ሃና ተናገሩ!
አባ ፋኑኤል ራሳቸውን ወጉ
መግቢያ አቡነ ፋኑኤል በዜና ቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲሰፍር ያደረጉት ሸፍጥ፤ ቢጤያቸውን ለመጋረድና የዘረጉትን የጥፋት መረብ ለማዳን ያደረጉት ሙከራ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። በዚህ ሸፍጥ ቢጤያቸውን ጋርደው ማዳን ይቅርና፤ ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያናችን አውጥተው መጣላቸውን ለማሳየት የምእመናኑን ውግዘት በቅዱሳት መጻህፍት መዝነው ካወጁት ቀሳውስት፦ ፩ኛ፦ ከሊቀ ማእምራን ዶክተር አማረ ካሣየ ፪ኛ፦ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ፫ኛ፦ ከአባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ ተክለ ሃይማኖት የተሰጠ መግለጫ እዚህ ላይ ይገኛል። … [Read more...] about አባ ፋኑኤል ራሳቸውን ወጉ
የማህበረሰብ ውይይት በኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ሰላምና ትብብር
በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት (ኅዳር 6/Nov. 15) በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር። በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር። ቅዳሜለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኘው አርሊንግተን ቨርጂኒያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገራቸው ተቋማዊ አስተዳድር ባልተጠናከረበት መልኩ፤ ማህበረሰቦች ሊጫወቱት የሚገባቸው ሚና፣ እንዲሁም እርስ በርስ የመተባበር ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነው። የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን … [Read more...] about የማህበረሰብ ውይይት በኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ሰላምና ትብብር