• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አባት አቶ ላላንጎ እና እናቷ ወ/ሮ ትርፌ ስለ ሃና ተናገሩ!

November 22, 2014 05:11 am by Editor 1 Comment

እህት ሃና በሰው አራዊቶች ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተደፍራ ወድቃ ያገኟት አባት ልጃቸው ህክምና ታገኝ ዘንድ ከሆስፒታል ሆስፒታል ስለተንከራተቱበት፣ የህክምና እርዳታ ስለተነፈጉበት አሳዛኝ ሂደት ሀገር ቤት በሚተላለፈው ኤፍ ኤም ራዲዮ ተናግረዋል። አባት ሲናገሩ ለሃና ህክምና ማድረግ ያልቻሉት የመንግስት ህክምና ተቋማት ሳያንስ ፖሊስ ጉዳዩን እንዲመረምር በልመና ካሳኩ በኋላ ህክምና ማግኘት ባለመቻላቸው የሚረዳቸው አጥተው ተጎጅ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ወስደው ስላሳደሩበት እንግልት ሰምተናል፣ ይህም ያማል፡፡

እንደ አባት አቶ ላላንጎ ገለጻ ልጃቸው እህት ሃና ከጋንዲ ጥቁር አንበሳ ከጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ ግልጋሎት ተነፍገው ተንከራተዋል። ወደ መጨረሻም በዘውዲቱ ሆስፒታል አልጋ ተሰጥቷን መታከም መጀመሯንና በህክምና እያለች የምስክርነት ቃሏን በደል አድራሽ ያለቻቸውን ሶስቱ በፖሊስ ተይዘው ቀርበው ለይታ ማሳየቷን አባት ተናግረዋል። ሃና በመጨረሻ ሰአቷ ከምስክርነት አልፎ በኑዛዜዋ በጉዳዩ የሉበትም ያለቻቸው እንዲለቀቁ መናገሯንና ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላት ያለቻትን ጓደኛዋን ፖሊስ “በቂ መረጃ የለም!”  በሚል እንደለቀቃት ሲናገሩ ይህም ከሃዘን በላይ ሃዘን እንደጨመረባቸው ቅሬታቸውን ተናግረዋል!

ምስኪኗ እናት ወ/ሮ ትርፌ

የሃና እናት ወሮ ትርፌ የልጃቸው የሃናን ስቃይ መመልከታቸውን፣  በማደንዘዣ  መቃጠል መንገብገቡ በረድ ሲልላት ነፍስ እየገዛች የሆነው ሁሉ መናገሯን እያነቡ እያነቡ ከአድማስ ራዲዮ ጋር የተናገሩት እናት የሃናን በደል መደበቁ ትድናለች የሚል ተስፋ ስለነበራቸው እንደነበር እያነቡ ልብን በሃዘን በሚሰብር ስሜት ተናግረዋል … በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት “በሃና ግፉ ይብቃ” ሲሉ ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ “… እኔ ያለኝ ነገር በሃና ሁሉም ነገር እንዲቀር፣ ለምን አሁንም ትውልዱ አየተበላ ነው፣ ህጻን እየተበላ ነው፣ የህጻናት መብት እንዲከበር፣ ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥ ነው የምፈልገው፣ ልጄ አትመጣልኝም በቃ ምን አደርጋለሁ?  አሁንም  እንደቀጠለ ነው … ለእኔ እንደሁ አትመጣልኝም ….ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥ ነው የማስተላልፈው!” የእኚህ እናት ህመም ህመማችን ነው! መልዕክታቸው መልዕክታችን ነው!

አዎ በርካታ ሃናዎች በአረብ ሃገራት መካከል የሁለትዮሽ ውል ባልተደረገበት ሁኔታ ለኮንትራት ስራ ወዳለሁበት አገር ተልከው ግፍ ተፈጽሞባቸው አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁ!  ምንዱባኑ ታዳጊዎች እድሜያቸውን ቆልለው በመጡ በርካታ እህቶች ባልጠነከረ ለጋ ገላቸው ተጎድቷል። ግፍን አስተናግደውየተረፉት ተርፈው በመንግስት ወኪሎች አማካኝነት ሲሸኙ በቂ ህክምናና ፍትህ አግኝተው አላየንም። ይህ ሆነና እውነቱ ግፉአኑ ተገፍተው ወደ ድሃ ጎጇቸው ለመሸኘታቸው እማኝ ነኝ። የእኒያ እናቶች ድምጽ እንደ ሃና እናት ባንሰማውም የሰቆቃ ህይወታቸውን፣ በድህነት ቤት የተረከቧቸውን ልጆቻቸውን ህይወት እናስበው!

በእህቶቻችን ደልላ የበለጸጉት ክፉዎችን ዛሬ ወደ ፍርድ የሚያቀርባቸው ቀርቶ ዝንባቸውን “እሽ” ማለት የሚቻለው የለም! ይባስ ብለው ዛሬ ዳግም ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው የኮንትራት ስራ ይጀመር ዘንድ እያጎበጎቡ ነው! ይባስ ብለው የኮንትራት ስራው የመጀመሩን ለእነሱ የሃሴት ለእኛ መርዶ የሚሆነውን ቀን መቅረብ ባለጊዜዎች ናቸውና በድፍረት እየነገሩን ነው!

ባደገች በተመነደገች ሃገራችን እየሆነ ያለውን ላሰበው ያማል … ያኔ ታዋቂው ድምጻዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ በቂ ህክምና የሚያገኝበት ሆስፒታል ጠፍቶ መንከራተቱን አስታውሰን፣ የሃናን የህክምና ተቋማት ግፍ የተፈጸመባትን እህት መታደግ አለመቻላቸውን ስናስበው ልባችን በሃዘን ይሰበራል፡፡

ዛሬ ህመማችን ጸንቷል፣ የጸናው ህመም የሚታከመው ደጋሚ ትክክለኛ ፍትህ ስናገኝ ብቻ ነውና ፍትህን ተጠምተናል፣ ፍትህን እንሻለን!

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 13 ቀን 2007 ዓም

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. dij mj says

    December 7, 2014 08:58 am at 8:58 am

    ትክክለኛ ፍትህ ይሰጥ ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule