• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብርቱካን በሊባኖስ ተረፈች፣ አልማዝ በኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ቀረች !

November 14, 2014 05:31 pm by Editor Leave a Comment

የተረፈችው የእህት ብርቱካን ጉዳይ …

በሃገረ ሊባኖሰ ቤሩት ከ4ኛ ፎቅ ወድቃ የተረፈችው እህት ብርቱካን ጤንነት የተስተካከለና ከድካም ህመሟ ሙሉ በሙሉ እያገገመች መሆኑን መረጃዎች ማምሻውን ደርሰውኛል። የቆንስል ሃላፊዎች አልማዝን ሲያነጋግሯት በሊባኖስ ቆይታ ስራ መስራት እንጅ ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደማትፈልግ እንደገለጸችላቸው አምባሳደር ሐሊማ ሙሃመድ አጫውተውኛል። በቀጣይ ቀናትም ህክምና እየወሰደች ያለችበትን መካስድ ሆስፒታልን ለቃ እንደምትወጣ ፣ በቤሩት የቆንስል መጠለያ ሆና ህክምናና ጉዳይዋን እንደምትከታተል ተረድቻለሁ !

ተስፋ የቆረጡት ኢትዮጵያውያን አስተያየት …

በብርቱካን ጉዳይ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ብዙ ነዋሪዎች የቆንስል ተዋካዮች ላይ እምነት እንደሌላቸው ይገልጻሉ። እንደ አማራጭም የብርቱካንን ጉዳይ በጠበቃ አስይዘው ለመከራከር የሚቻልበትን ንገድ ለማፈላለግ ስራ መሰራት አለበት ሲሉ “የቆንስል ሃላፊዎችን ዲስኩር ማመን ትቶ የተለመደው የነዋሪውን ትብብር ማስተባበር ያሻል” ይላሉ። ለምን በመንግስት ተወካዮቻችን እምነት አጣችሁ? ማለቴ አልቀረም ፣ ምላሻቸው ዘርዘር ያለ መረጃና ማስረጃ ያለው እውነት ይመስላል። አንድ ያሉኝን ብቻ ላንሳው … በሃገራ ባንዴራ ስር፣ በቆንስሏ በር በጥጋበኛ “ጀብራሬ” አረብ እየተጎተተች ስትደበደብ የቆንስል ሀላፊዎች ምንም አለማድረጋቸው ፣ ከዚያም ሃኪም ቤት በገባች በቀናት ልዩነት “ራሷን በራሷ ገደለች!” መርዶ ነጋሪና ሬሳ ተቀባይና ላኪ ከመሆን ያለፈ ስራ የመብት ማስጠበቅ ስራ በቆንስል መስሪያ ቤቱ አለመሰራቱን ያጣቅሳሉ። ከዚሁ ጋር በተዛማጅ ከአንድ ወር በፊት እዚያው ሊባኖስ “የአሰሪዋን ህጻን ልጅ አፍና ገድላለች!” በሚል በፍርድ ውሳኔ ያልተሰጠው ጉዳይ በመገናኛ ብዙሃን ቀርቦ ነበር። በቀረበው መረጃ ስማችን ጎደፈ። ዳሩ ግን የቀረበው መረጃ ኢትዮጵያዊቷ ወንጀለኛ አለመሆኗ ፍንጭ ሰጠ፣ የራሳቸው ዜጎች ከሳሽ ባቀረበው መረጃና ማስረጃ ተመርኩዘው የተገላቢጦሹን አሳዩት። ይህ ሁሉ ሲሆን የመንግስት ተወካዮቻችን ከሳሽን ወደ ተከሳሽነት የሚያሸጋግረውን መረጃ እንኳ ይዘው ታሳሪዋ ኢትዮጵያዊት እህት በዋስ መብቷ ተጠብቆ በውጭ ሆና እንድትከራከር አለማድረጋቸው በቆንስሉ የብርቱካን ክትትል ላይ የረባ ውጤት የማምጣት አቅም እንደሌላቸው ማሳያ ነው በማለት የሰላ ሂስና ወቀሳ ያቀርባሉ ።

የተስፈኞቹ ኢትዮጵያውያን አስተያየት …

birtukan and almaz“በቤሩት የቆንስል መ/ቤት ከበፊቱ የተሻለ ለውጥ ይታያል!” ያሉኝ ወገኖች፣ ለውጥ ለመምጣቱና ለመታየቱ የሚያቀርቧቸው ጥቃቅን የቆንስል ግልጋሎት አሰጣጥ መረጃዎች ናቸው። ያም ሆኖ የመስራት አቅሙ የላቸውም ያሉኝ የሚያነሱትን “…የከዚህ በፊቱን የአለም ደቻሳና ሌላው ሌላው አሳዛኝ የመብት ጥበቃ ጉድለት “ያለፈው አለፈ ፣ ይሁን !” ቢባል አሁን ድረስ እንዳልተሻሻሉ ብዙ ማሳያ አለ። ከወር በፊት በነፍስ ግድያ ወንጀል ያለ ተጨባጭ መረጃ የታሰረችውን እህት ቆንስሉ አያማክሯትም ። ለዋስ መብቷን አላስጠበቁላትም። “በማለት “የቀረበውን የሰላ ሂስ ” ለውጥ አለ! ” ባዮች በተጨበጠ መከራከሪያ መላሽ ለመስጠት አልተቻላቸውም ። ብቻ የቀረበውን ወቀሳ ሳያስተባብሉ “በለውጥ ተስፋ ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም!” በማለት የቆንሰል መ/ቤቱ የብርቱካንን ጉዳይ በቅርብ ተካታትሎ ውል እንደሚያስይዘው ያላቸውን ተስፋ አጋርተውኛል! …ቀጣዩ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ቢቸግርም ዛሬ የእህት ብርቱካንን በአሰቃቂ ሁኔታ መውደቅና ከከፋ አደጋ መትረፏ በሊባኖስ ቤሩት ካሉት ባለፈ በአለም ዙሪያ ሆነን ጉዳዩን በቅርብ ለተከታተልን ሁሉ እፎይታ ሆኗል … ተመስገን ነው! እናም “ያገባናል” ባዮች በእህት ብርቱካን ሰናይ ዜና ተደስተን ፊታችን ወደ ሌላዋ ግፉዕ ማዞር ግድ ብሎን ወደ “አልማዝን እንርዳ ” ዘመቻችን ፊታችን መዞራችን እውነት ነው!

የአካል ጉዳተኛዋ የአልማዝ ጉዳይ …

ህዳር 2 ቀን 2007 ምሽት በሊባኖስ የብርቱካንን ከፎቅ መውደቅ አሳዛኝ ዜና ስሰማ በሌላኛው አረብ ሀገር በኦማን የመኪና አደጋ ደርሶባት የአካል ጉዳተኛ በሆነችው በእህት አልማዝ ጉዳይ ተወጥሬ ነበር። ከተለያዩ አረብ ሃገራት እና በሃገር ቤት በማህበራዊ መገናኛዎች ተገናኝተን የተውጣጣን ወደ ስድስት የምንደርስ ወንድምና እህቶች ባንድ እየመከርን ነው። አላማችን ከመረጃ ልውውጡ ባለፈ የወገናችን እንባ በተግባር መጥረጉም “ያገባናል !” ብለን ነው። የእህት አልማዝን እርዳታ ለማሳካት ማድረግ ስላለብን ጉዳይ እየመከርን ባለበት ወቅት ከቤሩት የብርቱካን አደጋና “አትተርፍም!” የተባለ መረጃ ደረሰኝ … ሌላዋን የአረብ ሃገር ኦማን ጉስቁል እህት አልማዝን አሰብኳት …

እህት አልማዝ የአረብ ሃገሩ ስደት ሲነሳ ከመንግስት ጀምሮ እስከ ግለሰብ የእኛ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ እህቶቻችን አደጋ ላይ ጥሏቸዋል።በህግ ሽፋን ተሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ወሮበላ ህግ ይጣሳል ፣ ለህዝብ ቆመናል በሚሉ የመንግስት ተቋማት ህግ ይጣሳል ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት ፣ በሙስና ህይወታችን ከፍቷል ፣ በተለያያየ መንገድ በአረበወ ሃገራት ለገነነው “ዘመናዊ ባርነት ” ድጋፍ እያደረግን እያበረታታን ነው ። ይህን ማለቴ ያለነገር አይደለም ፣ በአረቡ ሃገር በኦማን አካሏ ተሰናክሎ የእኛን እርዳታ ጠባቂ የሆነችውን እህት አልማዝ አበሳ አስታውሼ ብዙውን አውጥቸ አወረድኩት …

…አልማዝ አንድ ፍሬ ጉብል ሳለች ካላቻ ጋብቻ ትዳርን ሳታውቀው መስርታ ልጅ ወልዳ ነበር ፣ ብዙም ሳይቆይ ጉብሏ እናት ሆነች ፣ ኑሮ አልሞላ አልሳካ ብሏት ወደ አረብ ሀገር ወደ ኦማን ተሰደደች … ሙሉ አካሏን ይዛ ለስራ ብላ በራ ከሄደችበት ኦማን ሞስካት ብዙም ሳትቆይ ለመኪና አደጋ ተጋለጠች ፣ ሆስፒታል ገባች ፣ ለወራት በህክምና ስትረዳ ብትቆይም አዕምሮዋ ፣ እግሯና እጇ ብሎም መላ አካሏ የከፋ ጉዳት ደረሰባቸው ፣ አይሆኑ ሆነች: ( ከሃገር ቤት ጀምሮ በአረብ ሀገራት ብርቱ መረብ ያላቸው ደላሎች እህት አልማዝ ሆስፒታል ከገባች በኋላም በጉዳቷ ለመጠቀም መስገብገባቸውን ጠልቆ መረጃ መሰብሰብ አሞኛል ፣ ዛሬ ወደ ክፉዎች ባለ ጊዜ ደላላ ባለጸጎች መሰሪ ምግባር ዳሰሳ አልገባም ! … እህት አልማዝ በተስፋ አቢሲኒያ በጎ አድራጊ ቡድን አባላት ፣ በተለይም በመስራቹ ብርቱ ወንድም በወዳጀ በመሳይ አክሊሉ ( በኑቢያ ኩሽ ቀዳማዊ ) እና በወዳጆቹ ብርታት በአሳር በመከራ ሃገር ቤት ገብታለች ። መቄዶንያ የአረጋውያን ደጋፊ በጎ አድራጊ ቡድን ትብብርም መጠለያም ተሰጥቷታል ። … እህት አልማዝ እዚህ ላይ ደርሳለች … ይህም ተመስገን ነው!

ይህም ሁሉ ሆኖ የአልጋ ቁራኛ የሆነችው አልማዝ ” ከህመም ጉዳቷ የምታገግምበት ተስፋ አለ ” በመባሉ የእርዳታ ስራ ተጀምሯል ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተጀመረው እርዳታ እዚህ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያለውን እርዳታ ለማስተባበር ሃላፊነት ከወሰድኩ ቀናት ወዲህ ወገኖች አልማዝን ለመርዳት ያሳዪት መነቃቃት እጅግ በጣም አበረታች ሆኖ ቀጥሏል። በኮንትራት ስራ በየአረቡ ቤት የሚሰሩ እህቶቸ የ “ነግ በኔ ” ብለው በሰብአዊነት እያደረጉት ያለው መተባበር ውስጥን ስሜት የሚያረካ ለመሆኑ እማኝ ለመሆን ታድያለሁ! የቤት ቆሻሻ ለመጣል መውጫ ቀዳዳውን ፈልገው ያላቸውን ለአልማዝ ለማካፈል ያሳዩት ቅንነት ፍጹም በቃላት ልገለጽ የማይቻለኝን ኩራት፣ በእህቶቼ እንድጎናጸፈው ዘንድ ምክንያት ሆኖኛል! ድምጻዊ ጆሲ ያን ሰሞን እርዳታ ለማሰባሰብ ሲሞክር በገጠመውና በሆነው በግኖ ይመስለኛል “ለመስጠት መሰጠት ያስፈልጋል!” ማለቱ በእኔም ላይ ደርሶ እውነት ነው ብያለሁ! ለእኔ እርዳታ ማድረግ ትርጉሙ ገንዘብ መስጠት ብቻ አይደለም፣ ቀና ማሰብ ፣ መረጃ መለዋወጥ፣ ሌላ ተዛማች ተጎጅውን የሚደግፍ ስራ መስራት ፣ የሚረዳን አለመቃወም፣ ገንዘብ ከመስጠት ባለፈ ለተጎጅው ወገን ወገናዊ አብሮነት ፍቅር መግለጫ ነው… ባይ ነኝ!

ለማንኛውም ብርቱካን በሊባኖስ ተረፈች፣ እሰየው ነው! እህት አልማዝ በኦማን ተሰናክላ እንዳትቀር ወገናዊ ትብብራችን ትሻለችና እናስብበት ! በዚህ የበጎነት መንገድ በመጓዝ በጠና የተጎዱ ወገኖቻችን በመደገፍ ልንታደጋቸው ካልቻልን ከንፈር መምጠጡ ብቻ እንዳላዋጣን ከእኛ በላይ የሚያውቀው የለም! እናም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር መንግስትን ስንወተውት የዝሆን ጀሮ ሰጥቶ አልሰማን ቢልም ጩኸት በደላችን እስኪሰማ እየጮህንም ቢሆን በመደጋገፉ የተጎዱትን እየነቀስን በማውጣት የቻልነውን መስራት የዜግነት ውዴታ ግዴታ ነው ባይ ነኝ!

ሁሉም ለበጎ ነው !
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 5 ቀን 2007 ዓም

_____________________________________________________________________________________

ቃለ ምልልስ: በሊባኖስ ከ4ኛ ፎቅ ከወደቀችው ከእህት ብርቱካን ጋር

አንዲት እህት ከአራተኛ ፎቅ የመውደቋ መረጃ በሊባኖስ መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ ከነሰቅጣጭ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ነበር፣ ኢትዮጵያዊቷ እህት ብርቱካን ነበረች! ለኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ሃገር ቤት የገባችው በአልማዝ ጉዳት ስንቆሰዝምና “የረጅ የደጋፊ ያለህ!” በማለት እርዳታ ስናሰባስን ከወደ ሊባኖስ ቤሩት በእህት ብርቱካን ላይ ሆኖ አይተነው የሰቀጠጠን ፣ ሰምተነው ያመመን አደጋ ልባችን ሰበረው።

ብዙም ሳይቆይ በብርቱካን ዙሪያ አወዛጋቢ ሪፖርቶች መቅረብ ጀመሩ ፣ እድሜ ለሥነ ቴክኖሎጂ ውሎ አድሮ ነገሩ እየጠራ መጣ! በሊባኖስ ከሚገኙ ለሰብዕና ባደሩ ቅን ወዳጆቸ ትብበር የብርቱካንን ጉዳይ በቅረብ በመከታየል ብርቱካን ያለችበት ሁኔታ በአንደበቷ እንድታስረዳን ያደረግነው ጥረት ተሳክቷል! ከብርቱካን በተጨማሪ ጉዳዩ ሚመለከታቸውን ሃላፊዎችና ሃኪሞች በጉዳቷ ዙሪያ አነጋግሬያቸውም ነበር። የህክምና ባለሙያዎችና በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ሃላፊዎች እንዳሉት ከሆነ ብርቱካን የደረሰባት ጉዳት ለከፋ አደጋ ስላልዳረጋት በቀጣይ ቀናት ከሀኪም ቤት በመውጣትና በተዘጋጀላት ማረፊያ ሆና ህክምናና ጉዳይዋን በፍርድ ቤት እንደምትከታተል ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ያስረዳሉ።

ከዚህ በማስከተል በትናንት ሃሙስ ህዳር 3 ቀን 2007 ከቀትር በኋላና አመበሻሹ ላይ እኔ ከሳወዲ ጅዳ ብርቱካንን ከሊባኖስ ቤሩት ሆስፒታል በመሆን በስልክ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ትከታተሉት ዘንድ ግብዣየ ነው!
ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 4 ቀን 2007 ዓም
Watch “Birtukan Libanos Nebiyu Sirak 2014” on YouTube

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule