ዘለላ ዘለላ ዱብ ዱብ በሚለው፤ ጉንጭሽን ሸርሽሮ ቁልቁል በሚፈሰው፤ ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤ በ’ንባሽ እያጠቀስኩ ስንኝ ቋጠርኩልሽ፤ ቃል ኪዳን ነውና አንብቢው አደራሽ:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ዕንባሽ ተናገረ!
Archives for November 2013
ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው … [Read more...] about ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ
ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ። በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል። አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ … [Read more...] about ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ
በቃ ብለን በጋራ እንነሳ
አኛ ኢትዮጵያዉያን በዚህ ዘመን በተለያዩ ሀገራት በስደት ተበትነን ለዚህ ታላቅ {ብሄራዊ} ዉርደት ለመብቃት የቻልነዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለእኛ ለልጆችዋ የምታንስ ሆና ሳይሆን የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዕጦት የፈጠረዉ ችግር መሆኑን የምታዉቁት ይመስለኛል ። ኢትዮጵያ ሀገራችን ብዙ የሰዉ ጉልበት፣ የተለያየ የዐየር ፀባይ የአለዉ መልክዐ ምድር የሚገኝባት በመሆኗ በህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲየዊ መንግስት ተመስርቶ መልካም አስተዳደር ቢሰፍን በአጭር ጊዜ ዉሰጥ አለምን የሚያስደምም የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ እንኳን ለእራሷ ዜጎች ስራ መፍጠር ቀርቶ የሌላ ሀገር ዜጎችንም መርዳት የሚያስችል አቅም መገንባት እንደምትችል ኢትዮጵያን ተዘዋዉሮ ያያትና የሚያዉቃት ይመሰክራል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በቃ ብለን በጋራ እንነሳ
የወገኔ ቅኔ
እንዲህ እንዲያ ብለው አሙን ፤ ተጠይቀው ሲመልሱ የወገኖቻችንን ደም ፤ በእብደት ግፍ ያፈሰሱ የኢትዮጵያ ስደተኞች ፤ ባሕላችንን ተቃረኑ ንጽሐችንን አረከሱ ፤ ነፍሳችንን አስኮነኑ መጠጥ በማዘዋወር ፤ በስርቆት ወንጀል በምኑ አንተ አረመኔ እንስሳ ፤ ምኑን ብየ ላውጣልህ ስም መጠጥ ምንህ ነውና ፤ ስካርህ የአንተ በሰው ደም አስገድዳ አልደፈረችህ ፤ ደፈርካት እንጅ በማደም መድፈርህ ሳያንስ ሳይበቃ ፤ አርደህ በላሃት ርጉም አንተ ውሉደ አጋንንት ፤ አረመኔ ዘረ ሰዶም ፡፡ ሌቦች ነበረ ያልካቸው ? እሰይ እንኳንም ሰረቁ ፈልገውት እንዳይመስልህ ፤ ምንም ነገር አይደል ድንቁ እባክህ ለከት ይኑርህ ፤ በዚህ አይታማም ወገኔ ነቢይህ ያውራህ ታሪኩን ፤ ያበሻን ማንነት ብያኔ የፍትሕ ደግነት ባለቤት ፤ ሕዝብ … [Read more...] about የወገኔ ቅኔ
በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጐሜዝ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው
በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ምርጫውን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ ውዝግብ አካል የነበሩት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ አና ጐሜዝ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ በአውሮፓ ኅብረት ተወክለው ምርጫውን በዋና ታዛቢነት የመሩትና የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጐሜዝ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት ኢሕአዴግ ከሚመራው መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በምርጫው ሳቢያ ውዝግብ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ የኢሕአዴግን ፖለቲካ በተለይም የሰብዓዊ መብት አያያዙን ከመተቸት ተቆጥበው አያውቁም፡፡ ይሁን እንጂ ከምርጫው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አያውቁም፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ፣ … [Read more...] about በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጐሜዝ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው
የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት እያነጋገረ ነው
አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች ከመገናኛ ብዙኃንና ከሕዝብ እይታ ከራቁ ከአንድ ወር በላይ የሆናቸው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ አስማሪኖ የተባለውና መቀመጫውን በካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደረገው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ድረ ገጽ እንደጻፈው፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወትሮው በተለየ ከመገናኛ ብዙኃን ርቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለመጨረሻ ጊዜ በሚዲያ የታዩት ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የአንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 58ኛ ጉባዔ ላይ መሆኑን ድረ ገጹ ጽፏል፡፡ ከዚያም በጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በጉበት ሕመም ምክንያት አስመራ በሚገኘው የአየር ኃይል ሐኪም ቤት ለስድስት ሰዓታት ያህል ሕክምና ተደርጐላቸው ወደ ቤተ መንግሥት መመለሳቸውን ጽፏል፡፡ በመቀጠልም ወደ … [Read more...] about የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት እያነጋገረ ነው
Open Letter to Ethiopian Foreign Minister
Re: Abuse of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) is concerned about the recent abuse of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia, especially the reported torture, abuse and rape of Ethiopian women. CREW is a non-government, non-profit, non-partisan, human rights and peace organization established to promote the social, economic and legal rights of Ethiopian women in Ethiopia and worldwide. One of the objectives of the organization is to … [Read more...] about Open Letter to Ethiopian Foreign Minister
እንደማያልፍ የለም
አዎ፤ የኔም እምባ ፈሷል እምነቴ ደፍርሷል ሰበዕናየ አንሷል ምክንያት ፍለጋ - መፍትሄ ፍለጋ ቀኑ እስከሚጨልም - ሌሊቱ እስቲነጋ ብቆርጥ ብቀጥል - ባነሳ ብጥለው ዘላለም ሆነብኝ - ማለቂያ የሌለው ሕመምሽ አሞኛል ድካምሽ ደክሞኛል እምባሽን ለመጥረግ - አቅም በማጣቴ ሕሊናየ ቆስሏል - ተቃጥሏል አንጀቴ እና….ጠንክሪ እህት ዓለም ይሄም ቀን ይረሳል - እንደማያልፍ የለም … [Read more...] about እንደማያልፍ የለም
ቀናችሁ አትርሳኝ!
ያልታየን አሟሟት- ባንተ አይቼ ሞትህን በቁሜ ሞቼ ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ እስካሁን አልጠገነም ህመሜ ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ ይህንን የናንተን አበሳ ልጽፈው ብዬ ብነሳ ሀዘን ዘልቆ ከገባ- አጥንት ድረስ ለካስ ቃላትም- የአንጀት አያደርስ እዬዬም ሲዳላ ነው ይባላል እንባም ስቃይ ሲከብደው- ለካስ ይደርቃል ደርቆ ይቅር- ድሮስ ምን ሊጠቅም እንባ ቃላትም በኖ ይጥፋ- ያሻው ቦታ ሄዶ ይግባ ሁለቱስ ምን አባታቸው ሊያደርጉልኝ ሞታችሁን ብረሳ ግን- ያቺ ቀናችሁ አትርሳኝ። ************** በሳውዲ ዐረቢያ አለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ይሁን … [Read more...] about ቀናችሁ አትርሳኝ!