• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጐሜዝ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

November 21, 2013 09:35 am by Editor 1 Comment

በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ምርጫውን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ ውዝግብ አካል የነበሩት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ አና ጐሜዝ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ በአውሮፓ ኅብረት ተወክለው ምርጫውን በዋና ታዛቢነት የመሩትና የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጐሜዝ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት ኢሕአዴግ ከሚመራው መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡

አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በምርጫው ሳቢያ ውዝግብ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ የኢሕአዴግን ፖለቲካ በተለይም የሰብዓዊ መብት አያያዙን ከመተቸት ተቆጥበው አያውቁም፡፡ ይሁን እንጂ ከምርጫው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አያውቁም፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ፣ የካረቢያንና የአውሮፓ ኅብረት አገሮች የጋራ የፓርላማ አባላት ጉባዔ ላይ ለመገኘት በአገሮቹ ከተወከሉ ግለሰቦች መካከል አና ጐሜዝ እንዳሉበት በኢትዮጵያ በኩል anaየጉባዔው አስተባባሪ ከሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምንጮቻችን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፖርቹጋላዊቷ የፓርላማ ተወካይ አና ጐሜዝ ቪዛ ሰጥቶ ይሁን ከልክሎ ለማወቅ ያደግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ግለሰቧ በቲዊተር ገጻቸው ላይ በአዲስ አበባው ጉባዔ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡ አና ጐሜዝ በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸው፣ ምርጫው ነፃና ፍትኃዊ እንዳልነበር ሪፖርት በማድረጋቸው ሪፖርቱ የውዝግቡ ምንጭ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሪፖርቱን ከማጣጣል አልፈው ግለሰቧን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መዝለፋቸው ይታወሳል፡፡

አና ጐሜዝ በበኩላቸው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የዕርዳታ ማዕቀብ እንዲጣልበት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ‹‹ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በተለይም የእንግሊዝና የአሜሪካ መንግሥታት በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ መንግሥት የሚፈጽመውን በደል እያዩ እንዳላዩ፤ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብለዋል፤›› በማለት ከዓመት በፊት የሰላ ትችት በመሰንዘር የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ የሚደረገውን ዕርዳታ እንዲያቆም ተከራክረዋል፡፡ (ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics

Reader Interactions

Comments

  1. ezra says

    November 24, 2013 02:40 am at 2:40 am

    EPRDF እኮ ፈረንጂን አምላኪና ለአረብ ተቅለስላሽ እንጅ ለኢትዮጵያውያንማ ቀጋ ነው። ለዚህ ነው እኮ ለውጭ አልጋ ለዉሰጥ ቀጋ የተባለው። ለአና ጎሜዝ ቪዛ ከሰጠም ጥሩ ነው ግን አይመስለኝም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule