አኛ ኢትዮጵያዉያን በዚህ ዘመን በተለያዩ ሀገራት በስደት ተበትነን ለዚህ ታላቅ {ብሄራዊ} ዉርደት ለመብቃት የቻልነዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለእኛ ለልጆችዋ የምታንስ ሆና ሳይሆን የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዕጦት የፈጠረዉ ችግር መሆኑን የምታዉቁት ይመስለኛል ።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ብዙ የሰዉ ጉልበት፣ የተለያየ የዐየር ፀባይ የአለዉ መልክዐ ምድር የሚገኝባት በመሆኗ በህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲየዊ መንግስት ተመስርቶ መልካም አስተዳደር ቢሰፍን በአጭር ጊዜ ዉሰጥ አለምን የሚያስደምም የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ እንኳን ለእራሷ ዜጎች ስራ መፍጠር ቀርቶ የሌላ ሀገር ዜጎችንም መርዳት የሚያስችል አቅም መገንባት እንደምትችል ኢትዮጵያን ተዘዋዉሮ ያያትና የሚያዉቃት ይመሰክራል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply