• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት እያነጋገረ ነው

November 21, 2013 08:26 am by Editor Leave a Comment

አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

ከመገናኛ ብዙኃንና ከሕዝብ እይታ ከራቁ ከአንድ ወር በላይ የሆናቸው  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡

አስማሪኖ የተባለውና መቀመጫውን በካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደረገው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ድረ ገጽ እንደጻፈው፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወትሮው በተለየ ከመገናኛ ብዙኃን ርቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለመጨረሻ ጊዜ በሚዲያ የታዩት ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የአንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 58ኛ ጉባዔ ላይ መሆኑን ድረ ገጹ ጽፏል፡፡

ከዚያም በጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በጉበት ሕመም ምክንያት አስመራ በሚገኘው የአየር ኃይል ሐኪም ቤት ለስድስት ሰዓታት ያህል ሕክምና ተደርጐላቸው  ወደ ቤተ መንግሥት መመለሳቸውን ጽፏል፡፡ በመቀጠልም ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ወይም ኳታር ለተጨማሪ ሕክምና መሄዳቸው እንዳልቀረ አትቷል፡፡

ስለ ጉዳዩ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ የማነ ገብረመስቀልን በትዊተር ገጻቸው ለሪፖርተር ማብራሪያ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ «አስቂኝ ቅዠት ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

«ፕሬዚዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው፤» በማለት መሠረተ ቢስ የሆነ ወሬ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ «ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ አስማሪኖ ውሸት ማውራት ስለፈለገ ነው፡፡ ማንኛውንም የአስመራ ነዋሪ መጠየቅ ይቻላል፤ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮአቸው ሲገቡ ያዩአቸዋል፤» ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከሚያዝያ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ ከመገናኛ ብዙኃን መጥፋታቸው መነጋገሪያ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በተያያዘ ዜናም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የቆንስላ ጉዳዮች ቢሮ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኤርትራ ምንም ዓይነት ጉዞ እንዳያደርጉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ በአገሪቷ ላይ የሚታየውን የፀጥታ ችግር እንደ ምክንያት በመግለጽ ከአሁን በፊት በግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ያወጣውን የጉዞ ማዕቀብ ማስጠንቀቂያ አጠናክሯል፡፡

ስቴት ዲፓርትመንት በመግለጫው እንዳስታወቀው፣ የአሜሪካና የኤርትራ ድርብ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ያለምንም ምክንያት እየታሠሩ ነው፡፡ በተጨማሪም በመርከብ የሚጓዙ የአሜሪካ ዜጎች በኤርትራ የባህር ዳርቻ እንዳይጓዙና መልህቆቻቸውን እንዳይጥሉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡

የኤርትራ መንግሥት መቀመጫው ሶማሊያ ለሆነው የአልሸባብ አክራሪ ቡድን ድጋፍ ያደርጋል በማለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በታኅሳስ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የመሣሪያ ማዕቀብ መጣሉ ይታወቃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ኮሚቴ ግን የኤርትራ መንግሥት ለአልሸባብ «ቀጥታ» ዕርዳታ እንደማያደርግ ሐምሌ 9 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡(ሪፖርተር ዜና)

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule