ተጠርጣሪዎቹ ሽፈራው ጃርሶ የሚመሩት ቦርድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ናቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ከእነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች 15 የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ፍለጋ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥና የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ ባልተከተለ መንገድ ኪራይ ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን፣ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባካሄደው ጥናታዊ ምርመራ በዚህ የሙስና ወንጀል መንግሥትን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዳሳጣው ለጉዳዩ ቅርበት የኮሚሽኑ ምንጮች … [Read more...] about በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
Archives for July 2013
ለፈገግታ፤ ለጨዋታ ከቁም ነገር ጋር …
ዛሬ ጠዋት ታክሲ የምጠብቅበት ቦታ መንገድ ላይ ዕቃ ዘርግተው ከሚሸጡ ነጋዴዎች መካከል አንዱ፤ ጆሮ ገብ ማስታወቂያ ሲሰራ ሰምቼ ዞር ብዬ አየሁት፡፡ ‹‹የሴቶች ፓንት ከነቂጡ በ20 ብር ብቻ!›› በበእውቀቱ ስዩም አባባል ‹‹ማቄጥ ለተሳናቸው›› ሴቶች የተሰራውን እንዲህ ያለውን ‹‹ግልገል ሱሪ›› ካየሁት ሰነባብቻለሁ፡፡ እንዲህ ሲሸጥ ግን ሰምቼ አላውቅምና ሳቅሁ፡፡ የግዜያችን ሴቶች፤ ፀጉራችን፣ ጡታችን፣ አሁን አሁን ደግሞ መቀመጫችን ሳይቀር ከመንገድ ላይ የሚገዛ መሆኑ አስገራሚ ነው፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች የምናወራው ወሬም የዚያኑ ያህል ግራ የሚያገባ እየሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ አስቧት አንዷን ከባሏ ጋር እንዲህ ስትባባል… ‹‹የኔ ቆንጆ እንውጣ፤ ረፈደ›› ይላታል እሱ፡፡ ‹‹እሺ..እስቲ ከዚያ …ከኮመዲናው ላይ ፀጉሬን … [Read more...] about ለፈገግታ፤ ለጨዋታ ከቁም ነገር ጋር …
በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለው ግብረሰዶማዊነትና ሴራው
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቀድሞ የተናቁና የተዘነጉ አንዳንድ ዘመን አመጣሽ ከባዕድ የገቡ ችግሮች እጅግ አሳሳቢ አደጋ እየጋረጡ እንደመጡ በተለይ በዚህ ወቅት በግልጽ ዕየታዩ ነው፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ቀስ እያለ የሞቀና እያላመደ የተባባሰ የመባባስም ባሕርይ ስላለው የህልውና አደጋ የመጋረጥ ደረጃ (boiling point) ሲደርስ ሁሉ እዛ ደረጃ መድረሱን ሳናስተውለው በፍላት ኃይሉ ተቀቅለን ልንፈራርስ የምንችልበት አጋጣሚ ሰፊ ሆኗል፡፡ ይሄንን አዚማም የችግሩን ባሕርይ ከወዲሁ የተረዱ ግለሰቦችና አንድ ማኅበር በሀገራችን ግብረሰዶማዊነትና የጋረጠውን አደጋ፣ የደረሰበትን አሳሳቢ ደረጃ ለሕዝብ የማሳወቅ እንቅስቃሴ በዜግነታቸው ለሀገራቸው ወይም ለሕዝባቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ማንም ምንም ሳይላቸው ለሀገርና ለሕዝብ ባላቸው ፍቅር በግል ተነሣሽነት ብቻ በመንቀሳቀስ … [Read more...] about በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለው ግብረሰዶማዊነትና ሴራው
የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ የዜጎችን ፊርማዎች ለመሰብሰብ!
የዜጎችን ፊርማዎች ማሰባሰብ የብዙ መቶ አመቶች ታሪክ ያለው ሰላማዊ ትግል ነው። የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ አንዱ ግብ በኢትዮጵያ ሽብር ህግ ላይ ዜጎች ያላቸውን አቅዋም በፊርማቸው እንዲገልጹ ማድረግ ነው። እንደሚታወቀው አንድ መንግስት ዜጎቹን በሽብር ህግ የሚገዛው ከፖለቲካ ተፎካካሪዎቹ የተሻለ አሳብ በማቅረብ የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ሲያቅተው ነው። የአዲስ አሳብ ምንጮቹ ሲደርቁበት ነው። የአሳብ ኪሳራ ሲደርስበት ፊቱን ወደ ሽብር ያዞራል። በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ይኼው ነው። በፊርማችን አቅዋማችንን እንግለጽ። አለም አቀፍ ሽብር ለመከላከል ነበር የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ የተደነገገው የሚለው ምክንያት ሃሰት ነው። የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ የተደነገገው አልቃይዳ እና ሌሎች አለም አቀፍ ሽብርተኞች ጥቃት ደርሶባቸው በሽሽት ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር። እንደ አውሮፓ … [Read more...] about የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ የዜጎችን ፊርማዎች ለመሰብሰብ!
The Secret (ሚስጢሩ…)
The Secret በሚል ረዕስ በሮዳን ቢይርን ተጽፎ በጋሻው አባተ ሚስጢሩ... በማለት ወደ አማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ በአድናቆት አነበብኩ። ሚስጢሩ... ”ወዳንተ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ወደ ሕይወትህ የምትጎትተው አንተው ነህ” ይለናል። አዎን! በእርግጥ ብዙዎች ምስክርነት ሰጥተውበታል።ይህም በመጽሐፍ ላይ ተካቶ ይገኛል። መጽሐፉ በአስራ አንድ ርዕሶች የተከፋፈለ ነው። ከዛ ውስጥ የመጀመሪያውን ዕርስ ማጠቃለያ ፍሬ ሀሳብ፤ በግጥም ስሠራው እንዲህ እንሶና ጭምቅ ብሎ ወጣልኝ። ለወገኖቼ ባካፍልስ ብዬ አሰብኩ፤ ወደናንተም ላኩት።ሁለተኛው ርዕስና ሌሎቹም ይቀጥላሉ። የተከሰተው ሚስጢር ሕይወት ለመለወጥ፤ የተገኘው ሚስጢር፤ ስበት እንደሆነ፤ አውቀህ ሕጉን ተማር። የፈለከው ነገር፤ ወደ ዓለም ተልኮ የልብህን ምኞት፤ ያመጣዋል ማርኮ። ከንግዲህ ሕይወትህን፤ ካሻህ ለመለውጥ መስመሩን … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት እና የአንድነት መሪዎች እንደ ጋንዲ!
የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነጻነት የሚለው ስትራተጂካዊ ዘመቻ ግቡ ምን እንደሆነ እና እድሜው ሶስት ወሮች እንደሚሆን አንድነት ፓርቲ ግልጽ አድርጓል። ከመግለጫው እንደተረዳሁት አንድነት ፓርቲ ጊዜ ወስዶ ብዙ አውጥቶ እና አውርዶ ያሰላው ለነፃነት እና ለዴሞክራሲ የሚደረግ ዘመቻ ነው። አንድ ነገር ግልጽ መሆን የጀመረ ይመስለኛል። ከንዋዮች መንግስት ፍንቀላ ጀምሮ ኢትዮጵያችን ለ50 አመቶች ያህል ብዙ ህይወት እየከፈለች በፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ትግል ጎዳና ስትወድቅ እና ስትነሳ ከርማ ዛሬ ትክክለኛውን ወደ ዴሞክራሲ የሚያደርሳትን ጎዳና ያገኘችው መሰለኝ። ወደፊትም መውደቅ መነሳት ሊኖር ይችላል። መንገዱም አልጋ ባልጋ አይሆንም። ይሁን እንጂ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ኢትዮጵያ ትክክለኛውን ጎዳና ማግኘቷን አብስሯል። የዚህ ዘመቻ ስሌት የፖለቲካ ትግል ባህላችንን እድገት ያመለክታል። … [Read more...] about የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት እና የአንድነት መሪዎች እንደ ጋንዲ!
ውግዘት
መግቢያ በዚህ ርዕስ ይህችን መልእክት እንዳዘጋጅ ያስገደደኝ ለኢሳት ሶስተኛ አመታዊ በዓል ላይ በተገኘሁበት ሳምንት ቬርጂኒያ ላይ የገጠመኝ ነገር ነው። ከስብሰባው በኋላ በበነጋው ዓርብ ኢሳት ስራውን የሚያካሂድበትን ቢሮ ለመጎብኘት ወደ ቬርጂኒያ ሄድኩ። ጎብኝቼ ስመለስ፤ ለዚህች መልእክት ምክንያት የሆነው ከባድና አስቸጋሪ ነገር ገጠመኝ። የገጠመኝን ችግር ከቦታው ለመግለጽ ከዚህ ላይ ገትቼ፤ ይህ ችግር የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ እንዴት ሊፈታው ይችላል? ብየ በማሰብ አዕምሮየን ወደጠመዘዝኩበት አቅጣጫ ልሻገር። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) … [Read more...] about ውግዘት
ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ላይ የጣለችው እገዳ እና አንድምታው . . .
በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . . አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና አነታራኪ ንግግር ነው። ሁለተኛው ሳውዲ ነዋሪውን የሃገሬ ሰው ግራ ያስደነገጠ ያስደሰተው ሲሆን ጉዳዩም የሳውዲ መንግስት የቤት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ እንዳይመጡ ጊዜያዊ እገዳ የጣለበት ጉዳይ ነው! ሁለቱንም ሰሞነኛ ጉዳዮች መነጋገሪያ ሆነው ሰንበተዋልና መረጥኳቸው ! ያም ቢሆንም የማተኩረው ባንዱ ርዕስ ላይ ብቻ ይሆናል ! እናም የዛሬ ወግ ትኩረቴን በአያሌው ስለሳበውና ሚዛንም ወደደፋብኝ … [Read more...] about ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ላይ የጣለችው እገዳ እና አንድምታው . . .
ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
አጠገብ ያሉ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ እንዲለቁ ተነገራቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ለማድረግ ስምምነት ሊያደርግ ነው በግዙፉ የጀሞ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች መንደር ውስጥ በአንድ በኩል በመስመጥ ላይ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሕንፃ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሕንፃው እንዲለቁ ተነገራቸው፡፡ በሁለቱ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሕንፃዎቹ እንዲለቁ የተጠየቁት በክፍለ ከተማው የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት አማካይነት መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የውሳኔው መነሻ ወደ አንድ ጐን በማዘንበል ላይ የሚገኘው ሕንፃ አጠገብ ያሉት ሁለት ሕንፃዎች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው በሚል ቢሆንም፣ በሕንፃዎቹ ላይ በዓይን የሚታይ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ሕንፃዎች ተመሳሳይ መሰነጣጠቅ በውስጥ አካላቸው … [Read more...] about ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
በዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ ተቀበለው» ነበር ያሉት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣ ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣ የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው። ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣ በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ ምን ይሻላል? » እየተባባልን ስናወራ ቆይተናል። ለዜጎቿ ሁሉ እኩል የሆነች፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ፍትህ የሰፈነባት፣ ሕዝቡ ለመሪዎች ሳይሆን መሪዎች ለሕዝብ የሚንበረክኩባት፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለማየት ትልቅ ጉጉት አለን። ማልኮም ኤክስ እንዳሉት፣ ፍትህንና እኩልነትን … [Read more...] about በዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ