
ዛሬ ጠዋት ታክሲ የምጠብቅበት ቦታ መንገድ ላይ ዕቃ ዘርግተው ከሚሸጡ ነጋዴዎች መካከል አንዱ፤ ጆሮ ገብ ማስታወቂያ ሲሰራ ሰምቼ ዞር ብዬ አየሁት፡፡
‹‹የሴቶች ፓንት ከነቂጡ በ20 ብር ብቻ!››
በበእውቀቱ ስዩም አባባል ‹‹ማቄጥ ለተሳናቸው›› ሴቶች የተሰራውን እንዲህ ያለውን ‹‹ግልገል ሱሪ›› ካየሁት ሰነባብቻለሁ፡፡ እንዲህ ሲሸጥ ግን ሰምቼ አላውቅምና ሳቅሁ፡፡
የግዜያችን ሴቶች፤ ፀጉራችን፣ ጡታችን፣ አሁን አሁን ደግሞ መቀመጫችን ሳይቀር ከመንገድ ላይ የሚገዛ መሆኑ አስገራሚ ነው፡፡
ስለእነዚህ ነገሮች የምናወራው ወሬም የዚያኑ ያህል ግራ የሚያገባ እየሆነ ነው፡፡
ለምሳሌ አስቧት አንዷን ከባሏ ጋር እንዲህ ስትባባል…
‹‹የኔ ቆንጆ እንውጣ፤ ረፈደ›› ይላታል እሱ፡፡
‹‹እሺ..እስቲ ከዚያ …ከኮመዲናው ላይ ፀጉሬን አቀብለኝ››
ይሰጣታል፡፡
‹‹ባለስፖንጁን ጡት መያዣዬን አይተኸዋል?››
ያቀብልና፤ ‹‹አረ በናትሽ እንውጣ በቃ!›› ይላል፡፡
‹‹ጨረስኩ እኮ…አንዴ ብቻ ይሄን ቂጤን ላስተካክለው! ተቀምጬበት ተጨማዷል! ››
አጃኢብ ነው!
ድሮ ድሮ፤ ‹‹እገሊትማ ቂጧን የጣለች ዱርዬ ናት››› ይባል ነበር፡፡ በዚህ አያያዛችን አሁን አሁን ሴቱ ሁሉ ቂጡን እየጣለ ሊተኛም አይደል?
Leave a Reply